Site icon ETHIO12.COM

ቦይንግ 737 ማክስ ወደ በረራ ተመልሰ

በአፍሪካ ታላቁ እና የአህጉሪቱ የአቪየሽን መሪ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ ” ቦይንግ 737 ማክስ ” አውሮፕላኑን ዛሬ ጥር 24 ቀን 2014 ዓ.ም ዳግም ወደ አየር መለሰ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ፣ የአየር መንገዱ የማኔጅመንት አባላት፣ የቦይንግ የስራ ኃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ጋዜጠኞች እና የአየር መንገዱ ደንበኞች በዚህ የመጀመሪያ በረራ ላይ መታደማቸው ተገልጿል።

አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ አገልግሎት መመለስ አስመልክተው ፥ “የበረራ ደህንነት የአየር መንገዳችን ተቀዳሚና ወሳኝ ጉዳይ ነው፤ እያንዳንዷ የምንሰራት ስራና የምንወስናት ውሳኔ በበረራ ደህንነት አብይ ጉዳይ የተቃኘ ነው። በዚህ መርህ ላይ በመመስረት ነው ዛሬ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላናችንን ወደ አገልግሎት የመለስነው።” ብለዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

Exit mobile version