የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትናንት ምሽት በይፋዊ ድረ-ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ከኢሚግሬሽን ቢሮ በመጣ መመርያ መሰረት የE-Visa እና Visa on Arrival አገልግሎቶች ከአርብ እኩለ-ለሊት ጀምሮ ለግዜው አይሰጡም።
ይህ ግን የትራንዚት መንገደኞችን እንደማይመለከት አክሎ ገልጿል።
የኢሚግሬሽን ድረ-ገፅ ደግሞ የ E-Visa ድረ-ገፁ እድሳት ላይ እንዳለ ገልፆ ተገልጋዮች ለቪዛ ጉዳዮች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ኤምባሲ ወይም ቆንፅላ ቢሮ እንዲያመሩ ይመክራል።
በዚህ ዙርያ ኢሚግሬሽን ዛሬ ጥዋት ለኢትዮጵያ ቼክ በሰጠው ቃል አገልግሎቱ የተቋረጠው በድረ-ገጹ ላይ የማሻሻያ ስራ እየተከናወነ በመሆኑ ነው።
የማሻሻያ ስራው በቅርቡ ይጠናቀቃል ሲል ገልጿል።
በዚህም መሰረት የ E-Visa ያላቸው እንዲሁም Visa on Arrival የሚፈልጉ ተጓዦች ወደ ኢትዮጵያ የሚደረግ የአየር ጉዞን ማድረግ አይችሉም፣ አየር መንገዶችም አያሳፍሩም።
ይህም ማለት ፦
- ፓስፖርት፣
- ቢጫ ካርድ (የትውልደ ኢትዮጵያዊ ካርድ)
- የተለጠፈ ቪዛ ያላቸው ብቻ መጓዝ ይችላሉ።
ይህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ወደ ኢትዮጵያ በረራ የሚያደርጉ አየር መንገዶችን ይመለከታል።