Site icon ETHIO12.COM

ኦሮሚያ ፖሊስ ምስራቅ ሸዋ ዞን የተፈጸመውን ግድያ እያጣራ መሆኑን ገለጸ-


– የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ግድያው በክልሉ ፖሊስ አባላት የተፈጸመ ነው ሲል አስታውቋል

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ የተፈፀመውን ግድያ እያጣራ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከዚህ ግድያ ጋር በተያያዘ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ግድያው የተፈጸመው በክልሉ ፖሊስ አባላት ነው ሲል አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ፖሊስ ሰፋ ያለ ምርምራ ማካሄድ ጀምሯል።

እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ ከግድያው ጋር በተያያዘ እስካሁን ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።

ከዚህ በፊት ከግድያው ጋር በተያያዘ የተሰጠው መግለጫን በተመለከተ የክልሉ ፖሊስ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ መግለጫው ከፖሊስ እውቅና ውጭ የተሰጠ ነውም ሲሉ አብራርተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ይፋ ባደረገው ሪፖርት ግድያው የተፈጸመው በክልሉ ፖሊስ አባላት አማካኝነት ነው ሲል አስታውቋል።

ይህንን በተመለከተም ምክትል ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው ላይ፤ ሰብአዊ መብት ኮሚሽኝን ጉዳዩን ለማጣራት ገለልተኛ ሆኖ የሄደበትን ርቀት እንደሚያደንቁ በመግለጽ አሁን ላይ እርግጠኛ ሆኖ ግድያው የተፈጸመው በዚህ አካል ነው ለማለት እንደማይቻል አብራርተዋል።

ፓሊስ እያካሄድ ያለው ምረመራ ሲጠናቀቅ ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

EPD

Exit mobile version