Site icon ETHIO12.COM

“ነገርን ከሥሩ ውሃን ከጥሩ”

የአማራ ሕዝብ ምንም አይነት የመሰረተ ልማት ባልነበረበት፣ የግንኙነት አውታሮች እጅግ ኋላ ቀር በሆኑበት ሁኔታ አንድነቱን አስጠብቆ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ገንብቷል። የባህል መስተጋብሩና ሌሎች ማህበራዊ እውነታዎቹ ከራሱ አልፎ ኢትዮጵያን ድርና ማግ ሆኖ አስተሳስሯል። የሁለቱ ታላላቅ ኃይማኖቶች (ክርስትና እና እስልምና) መንፈሳዊ መሪዎች መፍለቂያ መሆኑ አጥር የማይበጅለት አቃፊና ተጋሪ የማንነት ባለቤት አድርጎታል። ለዚህ በርካታ ማሳያዎችን ማቅረብ የሚቻል ቢሆንም የነገረ-ፍሬየ መዳረሻ አይደለምና እዘለዋለሁ። ሊሰመርበት የሚገባው የአማራ ሕዝብ አንድነት ግን #የሰላሳ ዓመታት ሳይሆን በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታትን የተሻገረ ነው። የዳማት ዙፋን ወራሽ፣ የአክሱም ሥልጣኔ ባለቤት ነው!!

ሃሳባዊያኖቹ “መርጦ መራገም” ልክ አይደለም፤ ብለው መክረው ነበር። የእርግማኑ ጥርቅምና ሌሎች ሴራዎች ተደማምረው ያን ጥቁር ቀን ፈጥሮ አልፏል። በተራ ቁጥር አንድና ሁለት የጠቀስኳቸው ዋና ዋናዎቹን የእርግማኖች ዶፍ እንጂ በውሃ ቀጠነ ምክንያት ሳይቀር የነበሩትን ግለሰቦች ላይ ያተኮሩ ዘመቻዎችን አንዘነጋቸውም

ይህ የአማራ ያገጠጠ ሃቅ በትህነግ ዘመን ለመፍጠር ከታሰበው አማራ እና ፖለቲካዊ ስዕሉ እጅግ የተለየ ነው። አማራን ክልል በተባለ በረት መገደብ ከተጀመረበት ከ1983 ጀምሮ የውስጥና የውጭ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ተቀያይረዋል፤ አማራ የደምና የላብ ዋጋ በከፈለላት ኢትዮጵያ ማንነቱ ወንጀል ሆኖበት በጅምላ ተገድሏል፣ ተፈናቅሏል፣ ተሳ’ዷል። የአካልና የንብረት ጉዳት ደርሶበታል። በእኔ እምነት ከአይሁዳዊያንም ሆነ ከርዋንዳ ቱትሲዎች በላይ ለተራዛሚ ዓመታት የከፋ እልቂት (የዘር መጥፋት) እያስተናገደ ያለ ሕዝብ ነው። የአማራ የቁርጥ ልጅ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ከጀመሩት ሕዝብን የማንቃትና የማደራጀት ንቅናቄ ጀምሮ ለአማራ እልቂትም ሆነ መፈናቀል ተጠያቂ የሚሆነው ከፍ ሲል የሥርዓቱ ባለቤት የሆነው ትህነግ/ኢህአዴግ ዝቅ ሲል ደግሞ ብአዴን ነበር። ይህን እውነታ ይዘን የአማራ ክልል መሪዎች እነማን ነበሩ?

1) አቶ አዲሱ ለገሠ [ሐረር-] 1984-1992 (8 ዓመታት)

2) አቶ ዮሴፍ ረታ [ሸዋ] 1993-1997 (5 ዓመታት)

3 አቶ አያሌው ጎበዜ [ጎጃም] 1998-2006 ህዳር (8 ዓመታት)

4) አቶ ገዱ አንዳርጋቸው [ወሎ] ከሕዳር 2006 – የካቲት 2011 (5 ዓመታት)

5) ዶ/ር አምባቸው መኮንን [ጎንደር] ከመጋቢት 2011- ሰኔ 2011 (3 ወራት)

6) አቶ ተመስገን ጥሩነህ [ጎጃም] ከነሐሴ-2011 – ጥቅምት 2013 (1 ዓመት ከሦስት ወራት)

7) አት አገኘሁ ተሻገር [ጎንደር] ከህዳር 2013 – መስከረም 2014 (1 ዓመት ብቻ)

8) ዶ/ር ይልቃል ከፋለ [ጎጃም] ከመስከረም 2014 – …

የመሪነት ሁኔታውን ዘመን በአውራጃ ካሰላነው እንደሚከተለው ይሆናል:-

አንደኛ፦ ጎጃም 3 ዙር ጠቅላላ ድምር =10 ዓመታት
ሁለተኛ ፦ የወያኔ አማርኛ ክንፍ አዲሱ ለገሠ ከሐረር – 8 ዓመታት ሶስተኛ፦ ወሎ 1 ጊዜ ጠቅላላ ድምር 5 ዓመታት አራተኛ ፦ ሸዋ 1 ጊዜ ጠቅላላ ድምር 5 ዓመታት አምስተኛ ፦ ጎንደር 2 ጊዜ ጠቅላላ ድምር 1 ዓመት ከሦስት ወር ሁኖ እናገኘዋለን።

አሁን ግን ከባለፈው ትምርት ተቀስሞ ይሆን? አላውቅም። ወይም የአርቆ አሳቢዎቹ ምክር ሰምሮ ይሁን? አሁንም አላውቅም። ብቻ ጉዳዮቻችን እናነሳለን። እንዘረዝራለን። የትግሬው ወራሪና አሸባሪ ደሴን፣ ኮምበልቻን ተቆጣጥሮ ደብረ-ሲና ደርሶ ነበር። በአማራ ህዝብ ላይም ዘግናኝና ሁልቆ መሳፍርት ግፎችን ፈጽሟል። ነገር ግን በዚያን ወቅት እንዳለፈው ሁሉ በግለሰቦች (ፕሬዝዳንቱ) ላይ የእርግማን መአት አልወረደም። ይሰመርበት መወረድ ነበረበት እያልኩ አይደለም።

በሰላሳ ዓመታቱ የአማራ ክልል መንግሥት ውስጥ የመሪነት ድርሻው ምን እንደሚመስል ከዚህ በላይ የቀረበውን መረጃ አይቶ መፍረድ ይቻላል። እንደጎንደር ያለው አካባቢ በርካታ ዞኖችና የሕዝብ ቁጥር ቢኖረውም በ30 ዓመቱ የክልሉ ታሪክ ያለው የፕሬዝዳንትነት መጋራት ከ1 ዓመት ከ3 ወራት ያልዘለለ ነው። ይህ ማለት በመቶኛ ሲሰላ ከ2.4 % አይዘልም!

ልብ በሉ ፍሬ-ነገራችን አውራጃዊ ስሌት አይደለም። ለአማራ ሕዝብ እስከጠቀመ ድረስ አማራዊ ስነ-ልቦና ይኑረው እንጂ፣ አማራ አንድ ህዝብ እስከሆነ ድረስ ከየትኛውም አውራጃ ይምጣ ጉዳያችን አይሆንም። በፉጹም። ግን ሌላ ጥሬ ሃቅ አፍጥጦ የምንመለከተው አለ:-

ይህውም የአማራ ብሄርተኝነት ከተነሳበት 2008 ጀምሮ የፖለቲካችን አውድ ድርጅትን ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ ግለሰቦች ላይ ማጠንጠን መለያ ባህሪው ሆኗል።

የአማራ ፖለቲካ እስከ አሁንም የተንጠለጠለው በግለሰቦች ላይ ነው። ተቋም ላይ አትኩሮት አልነበረውም። ከሰሞኑ ግን የሚታይ ነገር አለ። በአማራ ፖለቲካ ዑደት የሚወደሱትም ሆነ የሚብጠለጠሉት ግለሰቦች ብቻ እየተመረጡ ነው። ይህ ብሄርተኝነቱ የፈጠረው ስሜት ነው ለማለት ይቸግራል። ግን በብሄርተኝነቱ ዘመን የተፈጠረ የጎጠኝነት ደዌ ውላጅ ባህሪ ነው። ድርጅቱን ጥሎ ግለሰቡን አንጠልጥሎ አልያም አብጠልጥሎ የመጓዝ የብልጣብልጦች መንገድ ነው። ይህ በተፍካካሪውም ሆነ በገዥው ፓርቲ የተጣባው አባዜ ነው።

በተለየ ሁኔታ ትህነግ ከአዲስ አበባ ተባርሮ መቀሌ ከመሸገና አገራዊ ለውጡ ከመጣ በኋላ (ባለፉት 4 ዓመታት) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፕሬዝዳንትነት ወንበር ላይ የተለያዩ ግለሰቦች ተቀምጠውበታል። የወንበሩ አለመርጋት ለእኔም ይደንቀኛል። ከ2010- 2014 አምስት ፕሬዝዳንቶችን ቆጥረናል:- (አቶ ገዱ፣ ዶ/ር አምባቸው፣ አቶ ተመስገን፣ አቶ አገኘሁና ዶ/ር ይልቃል) በዚህ የእብደት ጊዜ መርጦ አልቃሽነትና መርጦ አሞጋሽነትን ታዝበናል:-

1ኛ በ2011 ሚያዚያ ላይ አምቦና ከሚሴ የተካሄደውን ስብሰባ ሰበብ በማድረግ በዶ/ር አምባቸው መኮነን ላይ (ነብስ ይማር) የነበረውን እርግማንና ዘመቻ እናስታውሳለን። ጠጅ የአማራ ባህል ያልሆነ ይመስል “ጠጆ” የሚል ቅፅል ስም እስከመስጠት ተደርሶ እንደነበር አንዘነጋም!

2ኛ በ2013 መጋቢት የአጣዬን ውድመት ተከትሎ በአቶ አገኘሁ ተሻገር ላይ የተደረገውን ዘመቻም አንረሳውም።

ያ…ኔ ጥቂትም ቢሆኑ ጥፋት ሲጠፋ መወቀስም ካላባቸው ግለሰቦች ሳይሆኑ እንደ ድርጅት መሆን አለበት ብለው የተከራከሩ አርቆ አሳቢዎች እንደነበሩም አንዘነጋም። ሃሳባዊያኖቹ “መርጦ መራገም” ልክ አይደለም፤ ብለው መክረው ነበር። የእርግማኑ ጥርቅምና ሌሎች ሴራዎች ተደማምረው ያን ጥቁር ቀን ፈጥሮ አልፏል። በተራ ቁጥር አንድና ሁለት የጠቀስኳቸው ዋና ዋናዎቹን የእርግማኖች ዶፍ እንጂ በውሃ ቀጠነ ምክንያት ሳይቀር የነበሩትን ግለሰቦች ላይ ያተኮሩ ዘመቻዎችን አንዘነጋቸውም።

አሁን ግን ከባለፈው ትምርት ተቀስሞ ይሆን? አላውቅም። ወይም የአርቆ አሳቢዎቹ ምክር ሰምሮ ይሁን? አሁንም አላውቅም። ብቻ ጉዳዮቻችን እናነሳለን። እንዘረዝራለን። የትግሬው ወራሪና አሸባሪ ደሴን፣ ኮምበልቻን ተቆጣጥሮ ደብረ-ሲና ደርሶ ነበር። በአማራ ህዝብ ላይም ዘግናኝና ሁልቆ መሳፍርት ግፎችን ፈጽሟል። ነገር ግን በዚያን ወቅት እንዳለፈው ሁሉ በግለሰቦች (ፕሬዝዳንቱ) ላይ የእርግማን መአት አልወረደም። ይሰመርበት መወረድ ነበረበት እያልኩ አይደለም።

ይደገም

ከሰሞኑ እጅግ ሰቅጣጫ በሆነ ሁኔታ ከ168 በላይ በኦሮምያ ክልል ወለጋ “አገሬ” ብለው በኖሩ ንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ በማንነታቸው ምክንያት ተለይተው በአሸበሪው ሸኔ ሲጨፈጨፉ ከዚህ በፊት እንደ ነበረው ሁሉ በክልሉ ፕሬዝዳንት ላይ ብቻ ተለይቶ የእርግማን መአት አለመውረዱ አዲስ ነገር ነው፤ ይህ በመሆኑ እንደኔ መልካም ነው። ጥሩ ጅምር ነው። በዚህ ረገድ የወቅቱ ፕሬዝዳንትም ዕድለኛ ናቸው። እንቅልፍ ከሚነሳ ስድብ ነፃ ሆነዋልና መተኛት ይችላሉ።

እንደ ከዚህ ቀደም የነበሩት (ያሉት) ወቀሳዎችም ሆኑ እርግማኖች በገዢው ፓርቲ በተለይ የአማራን ህዝብ ወክየዋለሁ ባለው በአማራ ብልጽግና መሆኑናቸውን አስተዋል እንጂ በፕሬዝዳንቱ ላይ ብቻ ያነጣጠሩ አይደለም። እንኳንም አላነጣጠሩ። “ተቋም የግለሰቦች ስብስብ እንጂ ግለሰቦች ብቻቸውን ተቋም አይደሉምና” ለልማቱም ሆነ ለጥፋቱ ተቋሙን ይመለከታል የሚለው አመክንዮ ገዢ ሆኖ ተገኝቶ ከሆነ (?) ጥሩ ጅምር ነው እንላለን። ከዚህ ሌላ ዓላማ ተይዞ ከሆነም ከልምድ እንማራለን። እንደዛሬው ጅምር ትችታችንም ሆነ ውዳሴ’ችን ተቋም ላይ ይሁን እያልኩ ጽሁፌን መቋጨቱን መርጫለሁ።

ምንጭ ፌስ ቡክ

Exit mobile version