Site icon ETHIO12.COM

በኢትዮጵያ አፍቃሪ ሱዳኖች የተመለሰው23 ሚሊዮን የግብፅ ዶላር

ምዕራብ ኩሩድፋን ውስጥ ፀጉራቸውን በሸረሪት ማግ ቀለም ቀብተው የቀይባህርን ጂኦ ፖለቲካ የሚመጠምጡ ቢንቢዎች አሉ። የቀድሞዋን የሱዳን የውጭ ጉዳይ መሬም ሳዲቅን ሚስጥርና ስብዕናን በየቀኑ በመግፈፍ መሬም ሱዳን በለበሰችው ቢጃማ ቱርክ ደርሳ፣ ወደ ሩሲያ ስትሄድ የለበሰችው ልብስ አንድ ቢጃማ በመሆኑ በጭንቅላቷ ውስጥ የቢንቢዎቹ ትችት መኖሩን አምኛለሁ ትላለች የአልጀዚራዋ አፈቀላጤ ጋዜጠኛ ሙና ኢብራሂም።
.
እነዚህ አፈቀላጤ ጋዜጠኞች በጋራ የሚፅፉበት ገፅ አላቸው። የት እንዳሉ በየት እንደዋሉ አይታወቅም። በአንድ ወቅት አደል ኢብራሂም፣ የአል አለሚውን ጋዜጠኛ መሀመድ ሙሳን ካርቱም ውስጥ አገኘሁት ብሎ ሲፅፍ ያገኘበትን ሁኔታ ሲናገር፣ መሀመድ ሙሳን ዛሬ ካርቱም አገኘሁት
አንድ አይኑን በካርቶን ሸፍኖል። የተቀዳደደ ነጭ ሸሚዝና ሰማያዊ ሱሪ፣ በሚስማር የተያያዘ ሸበጥ ጫማ፣ አንድ እጅግየው የተቀደደ ሸሚዝ ለብሶ አገኘሁት አለ።

ይህ ጋዜጠኛ በመንግሥት በሌለበት ለ12 አመት ተፈርዶበት የት እንዳለ እስካሁን፣ አይታወቅም ። ያለው የtwitter አካውንቱና የፌስቡክ ገፁ ነው። የሱዳን ሚስጥሮችን ሲያጋልጥ ለነገ የሚል ምህረት የለውም።

የቢቢዎቹ አለቃ የሚል ትርፍ ስም አለው። እነ መሬምና የግብፅ መንግስት፣ ሃበሻ አፍቃሪዎች የሚል ስም ይሰጧቸዋል።
ከ5 የትዳር ፍች ወደ 6ተኛው አዲስ ባል የተሸጋገረችው መሬም 75 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በግብፅ ብሔራዊ ባንካ አስቀምጣለች የሚል መረጃን ሲያወጣባት
እውር ያለውን ሰምቶ የሚያምን የለም የሚል ትችት ስሰነዝርበት ያነየ ነው መሀመድ ሙሳ ለመጀመሪያ ግዜ ገጭ ያለ ሱፍ ለብሶ ካርቱም ውስጥ የታው ።
.
ወደ ዋናው ጉዳይ ልግባ፣ የሰሞውኑን የቢቢዎቹ መጣጥፍ የግብፅን መንግስት ብቻ ሳይሆን የስለላ ድርጅቱን ጭምር ነው የነቀነቁት። 17 ቀን መሉ ከሱዳን ወደ ግብፅ የሚሄድ ምንም አይነት መኪና የለም። ሁሉም በሮች ዝግ ናቸው። 98⁰/⁰ የስጋና የቅባት የቆዳ የወርቅ ክምችቶችን ከሱዳን የምትቀበለው ግብፅ፣ የከፋች ያለህ ብላ በትማፀንም፤ ተቃሚዎቹ ንቅንቅ የለም ብለዋል። በየቀኑ 11 ሚሊየን ዶላር የንግድ ልውውጥ የሚደረግበት የቦር ሱዳን ወደብ ወደግብጽ የሚጭነው እቃ የለውም።

አሁን ግብፅ ከአፍሪካ ጋር ያላት የንግድ ግንኑነት ሙሉ በመሉ ተቋርጧል። አታርግብኝ ነውኮ። በዚህ ክስተት ውስጥ የስለላ ድርጅቱ ትናንት ባወጣው ዜና ላይ ከዚህ ሴራ ጀርባ ኢትዮጵያ አለችብት ብሏል።
.
የስለላ ድርጅቱን ዜና ከሰማ በኋላ ጋዜጠኛ መሀመድ ሙሳ ይችን አጠር ያለች ፁሁፍ ፅፏል።

መስር ሆይ ይልቅ ኢትዮጵያ እያልሽ እራስሽን አታታሊ። ኢትዮጵያ አፍቃሪ ሱዳኖች ብትይን” ለኛም ነሻጣ (ሞራል ይሰጠን ነበር) በነገራችን ላይ አመፀኞቹ ሰሞውኑን እኔንም ጎድተውኛል፣ ሰላም በሌላት ካርቱም ላይ ቡና የሚሸጡ የሀበሻ ልጆችን አይቼቻው አላቀም። ካርቱም ውበቷን የምትጨምረው በሃበሻ ቡናና፣ በቀጫጭን የአበሻ ልጆች ነበር። ደሞ ጀነራል ቡረሀን ይሄንን አንብቦ ለደቂቃ በአዕምሮ ውስጥ የሚመጣለትን ሀሳብ አላቅምና እዚሁ ላይ ላቁመው …!

ኢትዮጵያ በመንፈስ ነው የተበቀለቻችሁ። አፍቃሪ ኢትዮጵያ ሱዳኖች የኢትዮጵያን ብድር መልሰዋል። በነገራችን ላይ እኔ የኢትዮጵያ መንግስት ቢያደርገኝ ሰሞውኑን ወደ ሱዳን መጥቼ የተዘገ መንገዶችን እጎበኝ ነበር። ክፉ ነኝ ግን ይላል ሲሟዘዝ አቤት ለግብፅ ያለኝ ፍቅር እያለ ብዕሩን
ያሳምረዋል። እኔ ግን ኢትዮጵያን ለምን እንዲህ ጠላኋት እያለ በራሱም ሙድ ይይዛል ። መፃፉን አላቆመም። እናም መስርየ አሁን በቀየኑ ሚሊየን ዶክተር እየከሰርሽ ነው። ምቀኝነትሽ፣ ትንኮልሽ የሱዳን ያለሽ ፍቅር፣ ባደባባይ እንዲህ አይንሽ ባይንሽ እያሳየሽ ነው። መንገዱ ተዘግቷል።

መዘጋቱን ተከትሎ 23 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶባችኋል። በዚህ ከቀጠለ ካይሮ እጆቿን ወደ ሱዳን መዘርጋቷ አይቀርም። አንዳዴ እንዲህ ይሆናል። ከዛሬ አንድ አመት ከሦስት ወር በፊት ነበር፣ የናል ጠባቂ የአረብ ንስር እያላችሁ ጆቶቻችሁ ኢትዮጵያን ለማስፈራራት ወታደራዊ ትርኢት የሰሩት። ምን የቀረ አለ። ወታደራዊ ትብብር ያልተፈራረማችሁ ከቃሲም አወድ ጋር ብቻ ነው። እሱም የኔ አያት ስለሆነና ስለሞተ እንጅ እርግጠኛ ነኝ ትፈራረሙ ነበር።

ያሁሉ ጋጋታ፣ ያሁሉ የዙኝ ልቀቁኝ፣ በየትስም ቀኑ ከካይሮ ሱዳን መመላለስ የወታደራዊ ሀይልን ለማፈርጠምና ለማሳየት ነበር። ታዲያ ምን ዋጋ አለው፣ ወታደራችሁ ከአፍሪካ እንዳትገናኙ መንገዱን የቆረጠባችሁን የሱዳንን ህዝባዊ አመፅ አላስቆመም። አንዳዴ እንዲህም ይሆናል !

Suleman Abdela

Exit mobile version