Site icon ETHIO12.COM

የደላሎች ሚና በአዲሱ የንግድ ህግ

መግቢያ

ደላሎች በአገራችን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ ሚና የሚጫወቱ ሲሆኑ በተለይም በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ሻጭ እና ገዥን፤ አሰሪ እና ሰራተኛን፤ አምራች እና አከፋፋይን በማገኛኘት የንግድ እንቅስቃሴውን በማሰለጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጾ አላቸው፡፡ በሌላ በኩል በምርትና በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ በመግባት አላስፈላጊ የዋጋ ንረትን በመፍጠር የኑሮ ውድነት እንዲፈጠር በማድረግ፤ ያልተገባ ጥቅምን ለማግኘት በሻጭ እና ገዢ መሃል በመግባት ያልተገቡ ክፍያዎችን እና ጥቅሞችን በመጠየቅ እና በሻጭ እና ገዢ ላይ አላስፈላጊ ጫናን በማሰደር የንግድ እንቅስቃሴን በማወክ የተለያዩ ችግሮችን ሲፈጥሩም ይታያሉ፡፡

ደላሎች በአጠቃላይ በአገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ እና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ሚናን የሚጫወቱ በመሆኑ የሚያመጡትን ጉዳት ለመቀነስ እና የሚያበረክቱትን አስተዋጾ ለማጎልበት እንዲሁም የንግድ ሂደቱን ሰላማዊ፤ ህጋዊ እና አመቺ ለማድረግ በንግዱ ሂደት ውስጥ ደላሎች ሊጫወቱት የሚገባ ሚናን፤ ስላላቸው መብት እና ሀላፊነት በህግ መደንገግ በማስፈለጉ አዲሱ የንግድ ህግ ይህንኑ ከግምት ውስጥ በማስገባት ስለ ደላላ ምንነት፤ አሰራር፤ መብት እና ሀላፊበነት በመዘርዘር ያስቀመጠ በመሆኑ ይህም ጹፍ ባጭሩ ይህን ለመዳሰስ ይሞክራል ፡፡

የደላላ ትርጉም

አዲሱ የንግድ ህግ በአንቀጽ 54/1 ላይ ደላላ ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ያሚገልጽ ሲሆን ይህም፤
ደላሎች ማለት፡- የሚዋዋሉ ሰዎችን በተለይም እንደ ሽያጭ፤ ኪራይ፤ ኢንሹራንስ፤ የማመላለሻ ውል እንደዚህ ያሉትን ውሎች የሚዋዋለሉ ሰዎችን ፈልገው የሚያገናኙና የሚያዋውሉ፤ ራሱን የቻለ የሙያ ተግባራቸው አድርገው ጥቅም ለማግኘት የሚሠሩ ሰዎች ወይም ይህንኑ የደላላነት ሥራ የሚሠራ የንግድ ማህበር ነው በማለት ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ ከዚህም እንደምንረዳው በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ሻጭ እና ገዢን፤ አከራይ እና ተከራይን፤ አምራች እና አከፋፋይን፤ በአጠቃላይ ፈላጊ እና ተፈላጊን በማገናኘት ስራ ላይ የተሰማሩ እና ይህንንም ተግባራቸውን እንደ መደበኛ ሙያቸው እና መተደደሪቸው አድርገው የያዙ ግለሰቦች ወይም የንግድ መህበሮች ናቸው፡፡

በአዲሱ የንግድ ህግ ነጋዴ ስለ ሚባሉ ሰዎች በሚዘረዝርበት ምዕራፍ 2 አንቀጽ 5/34 ስር የድለላ ስራን የሚያከናውኑ ሰዎች የተዘረዘሩ እና እንደ ነገዴ እንደሚቆጠሩ አስቀምጦ የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም በህጉ አንቀጽ 54/2 ስርም ደላሎች አስማሚ ሆነው የሚያስፈጽሟቸው ውሎች ዓይነትና ግብ ወይም የሚያገናኟቸው ሰዎች ማንነት ወይም ሁኔታ ሳይታይ ነጋዴዎች ይባላሉ በማለት ደንግጎ ይገኛል፡፡ ይህም ማለት ደላሎች የሚያገናኛቸው ሰዎች በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ሆኑም አለሆኑም ደላሎች እንደ ነጋዴ እንደሚቆጠሩ ለመረዳት ይቻላል ፡፡

የደላላ አይነቶች

በአለማችን ላይ እንደ ሀገራት ኢኮኖሚ እድገት፤ የንግድ እንቅስቃሴዎች፤ የቴክኖሎጂ እድገት የደላሎች የስራ እንቅስቃሴ እና በንግድ ሂደት ውስጥ የሚጫወቱት ሚና እና የተለያዩ ሌሎች መስፈርቶችን መነሻ በማድረግ የተላያዩ የደላላ አይነቶች ያሉ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የደላሎች የአሰራር ሁኔታ፤ የእውቀት እና የሞያ ደረጃ እና ሚያስከፍሉትን ኮሚሽን መጠን መነሻ በማድረግ በሶስት የሚከፈሉ ሲሆን ይህም ፡-

1ኛ. የበይነ መረብ ደላሎች /Online brokers/

ይህ አይነቱ የድለላ ስራ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የተጀመረ ሲሆን የቴክኖሎጂ እድገት መሰረት በማድረግ የበይነ መረብን በመጠቀም በተለያዩ ድረገጾች ሻጭ እና ገዥን የማገናኘት ተግባርን ሚያከናውኑ ደላላ አይነቶች ናቸው፡፡ እንዚህም ደላሎች ቴክኖሎጂን በመጠቀም በፍጥነት በቀላሉ ከየትኛውም አለም ሚገኙ ድንበኞችን በዝቅተኛ ኮሚሽን ክፍያ የሚያገናኙ ናቸው፡፡

2ኛ. በአነስተኛ ኮሚሽን የሚሰሩ ደላሎች /Discount brokers/

በአነስተኛ ኮሚሽን የሚሰሩ ደላሎች በአነስተኛ የኮሚሽን ክፍያ የተለዩ ንብረቶችን ከደንበኞቻቸው ትዛዞችን በመቀበል መግዛት እና የመሸጥ ተግባርን ሚያከናውኑ ደላሎች ናቸው፡፡

3ኛ ጠቅላላ አገልግሎት የሚሰጡ ደላሎች /Full-service brokers/

ጠቅላላ አገልግሎት የሚሰጡ ደላሎች የተለየ ሙያ እና ክህሎት ያላቸው ሲሆኑ ያላቸውን እውቀት እና ክህሎት በመጠቀም ብዙ አገልግሎት ለደንበኞቻቸው የሚሰጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ደላሎች የንግድ ሂደትን የገበያ ሁኔታን የታክስ ጉዳይን የኢንቬስትሜንት ጉዳይን ማማከር እና መረጃዎችን መስጠትን የሚያካትት ተግባራትን የሚያከናውኑ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ደላሎች በሚያከናውኑት የድለላ ዘርፍ ላይ ብቻ በመመስረት በተለያ አይነቶች ሚከፈሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ

ጠቅላላ ደላሎች / general brokers/

ጠቅላላ ደላሎች በብዛት በተለያዩ የንግድ ተግባሮች እና የማህበረሰቡ እናቅስቃሴ ላይ ፈላጊን ከተፈላጊ ጋር የሚያገናኙ ሲሆን ከሚያከናውኑት የስራ ተግባራት መካከል ሻጭ እና ገዢን፤ ተከራይን እና አከራይን፤ አምራች እና አከፋፋይን፤ አሰሪና ሰራተኛን የማገናኘት እና የማስማማት ተግባርን ላይ የተሰማሩ ደላሎች ናቸው፡፡

የእንሹራንስ ደላሎች /Insurance brokers/

የኢንሹራንስ ደላሎች በኢንሹራንስ ገበያው ውስጥ የላቸውን እውቀት እና መረጃ በመጠቀም ለደንበኞቻቸው ተገቢውን መረጃ በመስጠት ደንበኞቻቸው አንስተኛ የእንሹራንስ ፖሊስ ከፍያን የሚያስከፍሉ የኢንሹራንስ ተቋማትን ለይቶ በማሰወቅ፤ ለደንበኞቻቸው የኢንሹራንስን ፎርሞችን እና ሌሎች ፕሮሰሶችን በመጨረስ ደንበኞቻቸው የኢንሹራንስን ፎርሞችን እና ሌሎች ፕሮሰሶችን ለሞምላት የሚያባክኑትን ጊዜ እንዲቆጥቡ ያሚያደርጉ እና ደንበኞችን በተሻለ መንገድ ተጠቃሚ ያሚያደርግ የኢንሱራንስ አይነቶችን ለይቶ የማቅረብ ተግባራትን በማከናወን ላይ የተሰማሩ ደላሎች ናቸው፡፡

የሪል እስቴት ደላሎች /Real estate brokers/

የሪል እስቴት ደላሎች ሪል እስቴቶችን፤ የመኖሪያ ቤቶችን፤ ሱቆችን፤ መጋዘኖችን እና የተለያዩ ቢሮዎችን ባለቸው እውቀት እና መረጃ በመጠቀም ሻጭ እና ገዚዎችን አፈላልጎ በማገናኘት የተወሰነ ኮሚሽን በማግኘት ስራ ላይ የተሰማሩ ደላሎች ናቸው፡፡

በአጠቃላይ እንደያ አገራት የኢኮኖሚ፤ የቴክኖሎጅ እድገት እና የንግድ እንቅስቃሴ የተላያዩ ሌሌች የድልላ ስራዎች እና የደላላ አይነቶች ይገኛሉ፡፡

ደላሎች የሚሰጡት አገልግሎት እና ያለባቸው ሀላፊነቶች

ደላሎች የደንበኞቻቸውን ችግሮች ገንዘብ እያተከፈላቸው የማቃለል ተግበር የሚያከናውኑ ሲሆን በተጨማሪም የተለያዩ አገልግሎቶችን ለደንበኞችቸው ይሰጣሉ ከዚህም ውስጥ ፡-
 በደንበኞቻቸው ወጪ ደንበኞቻቸውን በመወከል በፋይናንስ ገበያ ውስጥ የንግድ ተግባራትን ማከናወን
 ስለ አጠቃላይ የገበያ ሁኔታ እና የግብይት ሂደት ጠቃሚ መራጃ ለደንበኞቻቸው መስጠት
 ስለ ሌሎች የገበያው ተዋንያኖች ለደንበኞቻቻው ጠቃሚ መረጃዎችን በመስጠት ጠቃሚ ውሳኔ እንዲያስተላልፉ ማድረግ
 የደናበኞቻቸውን መረጃ ወይም ዳታ መስቀመጥ እና መጠበቅ
 ደንበኞቻቸውን መስጠት ስላለባቸው ዋጋ ስለስምምነታቸው እና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ማማከር
 ለሻጮች የቀረበውን ዋጋ ማሳወቅ
 የንብረቶችን የገበያ ዋጋ መወሰን
 ለሽያጭ ሚቀርቡትን ንብረቶች መዘርዘር እና ማስተዋዋቅ
 ለሽያጭ የሚቀርቡትን ንብረቶች ለገዢዎች ማሳየት እና ሌሎች ተመሳሳይ ተግባሮችን ማከናወንን ያካትታል፡፡

የደላሎች መብት
 ደላላው አስማሚ ሆኖ ውሉን ካስጨረሰ ወይም ካዋዋለ በኋላ ውሉ ቢፈጸምም ባይፈጸምም አበል ሊከፈለው ይገባል፡
 በልምድ የታወቀ ካልሆነ ወይም ሌላ ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር አበሉን የሚከፍለው የደላላውን አገልግሎት የጠየቀው ወገን ብቻ ነው፡፡
 አበሉ በስምምነቱ ውስጥ ይወሰናል ወይም ባልተወሰነበት ጊዜ በልምድ መሠረት ይቆረጣል፤የተስማሙበት አበል ከባድ መስሎ ሲታየው ወይም ደላላው ከሰጠው አገልግሎት ጋር ተመዛዛኝ አለመሆኑ ሲታየው ፍርድ ቤቱ ለመቀነስ ሥሌጣን አለው፡፡

የደላሎች ሀላፊነቶች
 ደላላው ለደንበምበኛው ወይም አገልግሎቱን ለጠየቀው ወገን ያሉበትን ግዳታዎች ተላልፎና ይልቁንም የደምበኛውን ጥቅም በሚጎዲ አኳኋን ለሌላ ሦስተኛ ወገን ጥቅም የሠራ እንደ ሆነ ወይም ደምበኛው ሳያውቅ ከሦስተኛው ወገን ክፌያ የተቀበለ እንደ ሆነ አበል የማግኘት መብቱ ቀሪ ይሆናል፡፡
 ደላላው ሁለቱም ተስማሚዎች በውላቸው በግልጽ ያስቀመጡት ዴንጋጌ ከሌለ በስተቀር ሁለቱም ተስማሚዎች በመወከል እነሱን ተክቶ ገንዘብ የመቀበልም ሆነ ማንኛውንም ወደ ተግባር የሚያስገባ እንቅስቃሴ ማድረግ የለበትም፡፡
 በልምድ የታወቀ ካል ሆነ ወይም ሌላ ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር ተዋዋዮቹ በጉዲዩ ውል ለማደረግ የተስማሙ እንደ ሆነ ውሉ የሚደረግበትን ሁኔታ ለተዋዋዮች ሁሉ ወዱያውኑ ደላላው ማስታወቅ አለበት፡፡በልምድ የታወቀ ካል ሆነ ወይም ሌላ ስምምነት ካሌለ በስተቀር በዚህ ዓይነት የተዘጋጀውን ውል ባለ ጉዲዮቹ ካላጸደቁት በስተቀር በእነርሱ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
 ደላላው በሁለቱም ወገኖች ላይ ለሚያ ደርሰው ጉዲት ኃላፉ ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ አዲሱ የንግድ ህግ ደላሎች እንደ ነጋዴ እርሳቸውን ቆጥረው የሚሰጡትን አገልግሎት ሀላፊነት በተሞላበት ሁኔታ እንዲያከናውኑ፤ የድለላ ስራቸውን በሚሰሩበት ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና ምን ማድረግ እንዳ ሌለባቸው ፤ያላቸውን መበት እና ተጠያቂነት በግልጽ ያስቀመጠ ነው፡፡ በመሆኑም ከዚህ በፊት ደላሎች በንግድ ሂደቱ በግብይት ስረዓቱ እና በምርት እና አቅርቦቱ እንዲሁም በእቃዎች በዋጋ ላይ የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተጽኖ በመቀነስ ለግብያት ስረአቱ መሳለጥ ያሚያበረክቱትን አስተዋጾ ለማጉልበት በሚያስችል ሁኔታ በአዲሱ የንግድ ህግ ላይ ተደንግጎ ይገኛል ፡፡

Attorney general Fb

Exit mobile version