Site icon ETHIO12.COM

ሩሲያ “የዩክሬንን የታጠቀ ሃይል ለማስተንፈስ” – ጆ ባይደን “ሩሲያ የእጇን ታገኛለች”- የዩክሬን የአየር መከላከያ ወድሟል

– በዩክሬን ለጡረተኞች ወታደሮች መሳሪያ እየታደለ ነው

– የሩሲያ ሜካናይዝድ ሃይል በቤላሩስ በኩል ወደ ዩክሬን እየገባ ነው

– ዩክሬን ዜጎቿ የአገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስከበር ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ተላለፈ

– ሞልዶዛና ሊትናው አስቸኳይ ጊዜ አወጆ

ቻይና ድርድር አስፈላጊ መሆኑንን ጠቅሳ ወረራ መባሉን ተቃውማለች።

ቱርክ ምን አለች?

የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ረሲብ ታይብ ኤርዶሃን እንዳስታወቁት ከሆነ ቱርክ ለሩስያም ሆነ ለዩክሬን እንደማትወግን አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ ከሁለቱም ጋር በጥብቅ ያስተሳሰረን ጥቅም አለን ያሉ ሲሆን ለማንኛቸውም እንደማይወግኑም ጠቁመዋል፡፡

የጥቁር ባህር ጎረቤቶቻችን ሲሉ የገለጹዋቸው ሩስያ እና ዩክሬን ሁሉንም ትተው ወደ ውይይት እንዲመለሱም ተማፅነዋል፡፡

ኤርዶሃን በአፍሪካ ሃገራት የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ሲመለሱ በሰጡት መግለጫቸው ይህንን ይበሉ እንጂ ቱርክ በቃል ኪዳኑ የታሰረችበት ኔቶ ዛሬም ዝግጅቱን እንደቀጠለ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዩክሬን ያለው ቀውስ እየተባባሰ መምጣቱ እየተዘገበ ይገኛል የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዶንባስ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን ይፋ ማድረጋቸውም እየተነገረ ነው፡፡

በዩክሬን ጀርባ ላይ ተመስርቶ ሲጦዝ የከረመው ውዝግብ ማምሻውን አዲስ መልክ ይዟል። የሩሲያ ጦር “ለሰላም ሲባል” በሚል ፑቲን ባቀረቡት ምክንያት ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ መታዘዙን ተከትሎ የዩክሬን የአየር መከላከያ መውደሙ ተሰምቷል። አሜሪካ ድርጊቱን “ወረራ” ስትል አውግዛ “ሩሲያ የእጇን ታገኛለች” ብላለች።

በአማፂያን ቁጥጥር ስር በሚገኙ ሁለት የምስራቃዊ ዩክሬን አካባቢዎችን እንዲቆጣጠር የታዘዘው የሩሲያ ጦር ዘመቻውን መጀመሩን ተከትሎ የአሜሪካ፣ የዩናይትድ ኪንግደም፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታትና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) አመራሮች ድርጊቱን አውግዘዋል።

የሩሲያ ፕሬዝደንት ብላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲካሄድ በቀጥታ ማዘዛቸው ይፋ ሳይሆን ስጋታቸውን ሲገልጹ የነበሩ፣ ይህንኑ ስጋት በመቀባበል ሲዘግቡ የነበሩ ሁሉም የዓለም ሚዲያ በቀጥታ “ዩክሬን ተወረርች” በሚል ነው። ሮይተርስ ኬቭን ጨምሮ ሶስት ከተሞች ላይ ሚሳይል መተኮሱን አመልክቷል።

በአካባቢው ያሉ አገሮች እንደ ሊተናው ያሉ የአስቸኳይ አዋጅ እያወጁ ነው። በዩክሬን ጡረተኛ ወታደሮች መሳሪያ እየታደላቸው መሆኑንን የአገሪቱ ሚዲያ አመልክቷል።

በርካታ ህዝብ ወደ ሞልዶቫ እየሸሸ እንደሆነ እየተዘገበ ነው። ጦርነቱ ያበጠውን የዩክሬን ሃይል ለማስተንፈስ እንጂ ኬቭን የመቆጣጠር እንዳልሆነ ፑቲን ገልጸዋል።

አውሮፓን አስጨንቆ የከረመው ፍጥጫ ዛሬ መፈንዳቱን የሚያመላክቱ ሪፖርቶች ከየአቅጣጫው በሚወጡበት በአሁኑ ሰዓት ዩክሬን ራሷን እንደምትከላከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ጎን ለጎንም ዩክሬን የሩሲያን የጦር አምስት አውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች እንደጣለችተገልጿል።

የዩክሬን መከላከያ “አትሸበሩ በዩክሬን ወታደራዊ ኃይል ተማመኑ” ሲል መገለጫ አሰራጭቷል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴርን የጠቀሰው አርቲ አውሮፕላንም ይሁን ሄሊኮፕተር በዬክሬን ተጥሏል መባሉን ሃሰት እንደሆነ መሆኑንን ገልጿል። ዩክሬን “አትሸበሩ” ብትልም Ukraine’s air defense destroyed – Russia ሩሲያ የዩክሬን የአየር መከላከል አቅም መውደሙን አመልክታለች። በተወሰደው ጥቃት የዩክሬን የአየር መከላከል አቅም መውደም “የዩክሬንን የመከላከያ አቅም አንኮታኩቶታል” ሲል የመከላከያ ሚኒስትሩን በመጥቀስ የአር ቲ ዘገባ ያስረዳል።

ከመቶ ሃምሳ ሺህ በላይ ወታደሮቿን በዩክሬን የድንበር አካባቢዎች እንዳሰማራች ተጠቅሶ ስትወገዝ የከረመችው ሩሲያ ማምሻውን የጀመረችውን ኦፕሬሽን ተከትሎ ጣልቃ የሚገቡ የውጭ ሃይሎች ካሉ ” ውርድ ከራስ” ብላለች። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮን “እንርዳ” ሲሉ ከዩክሬን ጋር ህብረት መቆም እንደሚገባ ማመልከታቸውን ተከትሎ ነው።

ኮሽታ የሚያስበረግጋቸው የአውሮፓ አገር ነዋሪዎችን ስጋት ላይ የጣለው የዩክሬን ቀውስ መባባሱን ተከትሎ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተባበሩት መንግሥታት የሩሲያን ወረራ ለመግታት “የቻለውን ሁሉ ማድረግ ይገባዋል” ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

“ወታደራዊ ዘመቻ” ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ላለፉት ሰባ ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ ተሰቅሏል። ቀውሱ ከቀጠለ ከዚህም በላይ ሊባባስ እንደሚችል እየተነገረ ነው። ከሳዑዲ አረቢያ በመቀጠል በዓለም ሁለተኛዋ የነዳጅ ዘይት አምራች የሆነችው ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ወታደራዊ ዘመቻ ምክንያት ምዕራባውያን ቁጣቸውን እያሰሙ ነው።

በተደጋጋሚ እየወጡ ባሉ ሪፖርቶች መነሻ በዩክሬን አንዳንድ ከተሞች ውስጥ ተኩስና ፍንዳታ የሚሰማ ሲሆን በዋና ከተማዋ ኪዬቭ በሚገኘው ቦሪስፒል አየር ማረፊያ አካባቢም ተኩስ እየተሰማ ስለመሆኑ ሪፖርቶች እየወጡ ነው። ሩሲያ አጭር፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የተባለ ኦፕሬሽን በማካሄድ ነጻ አገር ከሆኑት ጋር ስምምነት በማድረግ የዩክሬንን ከፊል አካል ለመጠቅለል መዘጋጀቷን ተንታኞች እየገለጹ ነው።

ጆ ባይደን ድርጊቱን አውግዘው ሩሲያ የእጇን እንደምታገኝ ቢዝቱም እንዴትና በምን መልኩ እንደሆነ አልተብራራም። የዩክሬን ፕሬዚዳንት “እርዱን” ሲሉ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን ጥየቀዋል። ይሁን እውንጂ እስካሁን ናቶም ሆነ አሜሪካ ስለሚወሰድ ወታደራዊ እርምጃ በግልጽ ያሉት ነገር የለም። ሩሲያ ግን ጣልቃ የሚገቡ ማናቸውም የውጭ አካላትን እንደማትታገዝ ፑቲን አመልክተዋል።

Exit mobile version