Site icon ETHIO12.COM

በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለው ግጭት ምንድነው?

ሰሞኑን በይፋ የተጀመረው የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት የአለምን አይን እና ጆሮ ከመሳብ ባሻገር፣ የምድራችንን ሁናቴ ሊቀይር ይችላል በሚል መላው የአለም ህዝብ #በንቃት እና #በስጋት እየተከታተለ ይገኛል። ለመሆኑ የጸባቸው መንስዔ ምን ይሆን? ለሚለው ጥያቄ ተከታዩ መልስ ተዘጋጅቷል።

እ.ኤ.አ. በ1991 ዩክሬን የሶቪየት ኅብረትን መፍረስ ተከትሎ ነፃ የሆነች ሀገር ሆነች። ቀደም ሲል የሩሲያ ግዛት አካል የነበረች ቢሆንም ከሶቪየት ጋር የነበራትን ሰማኒያ ቀዳ ከምዕራቡ ዓለም ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር እሽኮሎሌ ማለቷን ተያያዘች።

ሀገሪቱ ነፃነቷን ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ ሙስናን እና የውስጥ ክፍፍልን እየታገለች ጎጆዋን ቀለሰች። የሆነው ሆኖ የሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል ከምዕራቡ ዓለም ጋር ሲዋሃድ ምስራቃዊው ክልል ደግሞ ከሩሲያ ጋር እንዲዋሃድ ይፈልጋል።

ግጭቱ የጀመረው የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች ከሞስኮ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር ከአውሮፓ ህብረት ጋር የተደረገውን የማህበር ስምምነት ውድቅ ማድረጉን ተከትሎነው። የክብር አብዮት (Revolution of Dignity) እየተባለ በሚጠራው ተቋውሞ ተቃዋሚዎች ፕሬዘዳንቱን ከስልጣን አባረሩት። በምላሹ ሩሲያ የዩክሬን ክራይሚያን ባሕረ ገብ መሬት ተቀላቀለች እና የምስራቅ ዩክሬንን ተገንጣይ አመጽ መደገፉን ተያያዘችው የሚል አቤቱታ ይቀርብባታል።

ከዚህ በኋላ፣ ብዙም ሳይቆይ የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ማዕከል በሆነችው ዶንባስ ላይ ጥቃት ተሰነዘረ። በዩክሬን ጦር እና በሩሲያ በሚደገፉ ተገንጣዮች መካከል በተነሳው የትጥቅ ግጭት ከ14,000 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ይነሳል።

ዩክሬን እና ምዕራባውያን ሩሲያ ወታደሮቿን አሰማርታለች እና ለአማፅያኑ የጦር መሳሪያ ትልካለች በማለት በተደጋጋሚ ሲከሷት፣ ሩሲያ በተቃራኒው እጇ እንደሌለባት ታስተበብላች። በተቃራኒው ሩሲያ ፣አሜሪካ እና ኔቶ ዩክሬንን በጦር መሳሪያ እና በጋራ ወታደራዊ ልምምዶች እየረዱ ነው ስትል አጥብቃ ትወቅሳለች።

ፕሬዝዳንት #ፑቲንም የኔቶ አባላት በዩክሬን ወታደራዊ ማሰልጠኛ ለማቋቋም ያቀዱት እቅድ እንዳሳሰባቸው ሲገልጹ መቆየታቸው የሚታወቅ ሲሆን ጉዳዩ ከሁለቱ ሀገራት እንደሚልቅ አመላካች ነው።

ሩሲያ በፀጥታ ጥያቄዋ ዩክሬን የኔቶ አባል እንድትሆን እንደማትፈልግ እና ተጨማሪ የኔቶ ጦር በድንበሯ አቅራቢያ ያለውን ልምምዶች በሙሉ ማቆም እና የኔቶ ወታደሮችን ከመካከለኛው እና ከምስራቅ አውሮፓ መውጣት እንደምትፈልግ ትናግራለች። ምንም እንኳ ዩክሬን ወደ ኔቶ ለመግባት የ30 አባል ሀገራት በሙሉ ድምጽ ማፅደቅ የሚኖርባቸው ቢሆንም።

በተጨማሪ ሩሲያ ዩክሬንን እንደ “የተፅዕኖ መስክ” ግዛት, እንጂ ሉአላዊ ሀገር መቁጠር አለመፈለጓ የጸባቸው የተራዘመ ምክንያት እንደሆነ የዘርፉ ተንታኞች ይጠቅሳሉ።

የሆነው ሆኖ አሜሪካ እና ኔቶ የሩስያን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ምዕራባውያን ጨምሮ ዩክሬንን አይዞሽ አለንልሽ ማለታቸው የችግሩን አድማስ ያሰፋወ።

የሁለቱ ሀገራት ግጭት እንደሚፈራው የሶስተኛው የአለም ጦርነት ይቀሰቅስ ይሆን? ኢትዮጵያ ሀገራችንስ በዚሁ ጉዳይ ከማን ወገን ትሆን? የሚሉ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ይዤ የምመለስ ይሆናል።

Via – Wegayehu Muluneh Fb

ይህ ሰው እጅግ ደሃ ከሚባሉ ቤተሰቦች ነው የተወለደው! ሁለት ታላላቅ ወንድሞቹ ሞተዋል! አባቱ በጦርነት የቆሰለ ነው።

እናቱ ምስኪን የፋብሪካ ቀን ሰራተኛ ነበረች! አስፈሪ ነው። ፊቱ አይፈታም። አይደለም ለማዋራት አጠገቡ ለመቆም እንኳን ብዙ መሪዎች ይንቀጠቀጣሉ።

ለሶስት ተከታታይ አመታት በ”Forbes” ጋዜጣ የዓለማችን ተፅህኖ ፈጣሪ ሰው መሆን ችላል።ስለ ግል ህይወቱ ማንም አያውቅም! ከተፋታት ሚስቱ የወለዳቸው ሁለት ሴት ልጆቹ የት እንደሚኖሩ አይታወቅም! የኮሌጅ ትምህርታቸው ሳይቀር በ “Fake” ስም እና ማንነት ተምረው እዛው “Russia” ውስጥ ማንም ሳያውቃቸው እንደጨረሱ ይነገራል!!

ስብሰባዎች ላይ ሁሌ ከተባለው ሰዓት አርፍዶ ይመጣል! የእንግሊዟ ንግስት እና የካቶሊኩን ጳጳስ ሳይቀር ከአንድ ሰዓት በላይ አስጠብቋቸው ወደ ስብሰባ የመጣ ደፋር ሰው ነው። ሰላይ እንገናኝ የተባለበት ሰዓት አናቷ ላይ አይመጣም! በዛች ሰዓት ምን እንደተጠነሰሰለት አይታወቅማ ባሻዬ!

ሰውየው ያለውን ያደርጋል፣ ያቀደውን ያሳካል! ሃገሪቷን ከዓለማችን ዋነኛ የነዳጅ አምራች ሃገሮች ተርታ አሰልፏታል፣ 70% የሚሆነው ህዝብ መካከለኛ ገቢ ነው(የህዝቡ የነብስ ወከፍ ገቢ 28 ሺህ ዶላር በላይ ነው)፣ የሃገሪቷ ዋና ከተማ “Moscow” የዓለማችን ቁጥር አንድ ብዙ ቢልየነሮች መገኛ ነች፣ ሃገሪቱን የዓለማችን ቁጥር አንድ የ “Nuclear” ክምችት ያላት ሀገር እንድትሆን አድርጓል፣ በአውሮፓ አንደኛ እና በዓለም ሁለተኛ መሆን የቻለ የሃገር መከላከያን ገንብቷል።

Vladimir Vladimirovich Putin.

Via Fb

Exit mobile version