ETHIO12.COM

ከሃይል ሽኩቻው በተጨማሪ የዩክሬይን! ቁልፍ ጉዳዮች

እንግሊዝና አሜሪካ ሞስኮ ላይ ስለጣሉት ማዕቀብ ተፅዕኖ ከማውራታችን በፊት ይህን እንመልከት። “ዩክሬይን ወደ ሩሲያ ተጠቃለለች ማለት ምዕራባዊያን ሩሲያ የሚኖራትን ዓለም ዓቀፍ ተፅዕኖ በአይናቸው እያዩ አምነው ይቀበላሉ።” የሚለው በበርካታ ምዕራባዊ ምሁራን የተለያዩ ጥናቶችና መፃህፍት ውስጥ የተሰጠ ድምዳሜ ነው። ዩክሬይን በምዕራባዊያን ስር መቆየቷ ደግሞ አለማቀፍ የተፅዕኖ ሚዛኑን በምዕራቦቹ ስር እንዲቆይ እንደሚያችል በመግለፅ ጭምር። ከአውሮፓ አካባቢ በቆዳ ስፋቷ ሁለተኛዋ ዩክሬይን 43 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ናት፤ እንግዲህ ከሃይል ሽኩቻው በዘለለ ስለ ዩክሬን ከርስ ቁልፍ ጉዳዮቹ

የዩክሬን ቁልፍ ደረጃዎች

በግብርና

▪️ዩክሬን ያላት ለም የእርሻ መሬት መጠን ከአውሮፓ 1ኛ ነው።

▪️የጥቁር-አፈር መሬት ሀብቷ ከአለም ሶስተኛው ሲሆን የአለምን 25% ድርሻ ይወስዳል።

▪️የሱፍ ዘይትና ራሱን ሱፍን ወደ ውጭ በመላክ ከዓለም ቁጥር አንዷ ዩክሬይን ናት።

▪️በማሽላ corn አምራችና ላኪነት ከአለም ሶስተኛ፤

▪️ዩክሬይን በድንች ምርት ከዓለም 4ኛዋ ደገኛ ሀገር ናት።

▪️በአጃ ምርት ከዓለም 5ኛ፤

▪️በንብ ማነብ ከዓለም 5ኛ ናት። አመታዊ ምርቷ 75,000 ቶን

▪️የጫጩት እንቁላል በማምረት ከዓለም 9ኛ

▪️ዩክሬን የእርሻ ምርት ለ600 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ፍላጎት ያሟላል፤

ዩክሬን በኢንዱስትሪ

▪️ከአውሮፓ 2ኛውና ከአለም 4ኛው ግዙፍ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ መሰረተ-ልማት በዩክሬን የሚገኝ ነው።

▪️በኒዩክሌር ማብላያዎቿ Installed capacity ከአውሮፓ 3ኛ ከዓለም 8ኛ

▪️ዩክሬን ያላት የባቡር ኔትወርክ ከአውሮፓ 3ኛ ሲሆን ከአለም 11ኛው ነው። ርዝመቱ 21,700 ኪ.ሜ፤

▪️የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን በማምረት ከአሜሪካና ፈረንሳይ በመቀጠል ከአለም ሶስተኛዋ፤

▪️በብረት ማዕድን እክስፖርት ከዓለም 3ኛ ትልቋ ላኪ ናት፤

▪️ለኑክሌር ኃይል ማመንጫዎች የሚሆነውን ተርባይን ኤክስፖርት በማድረግ ከአለም 4ኛዋ፤

▪️የሮኬት መተኮሻ አምርታ በመላክ ከአለም 4ኛዋ፤

▪️በሸክላ ኤክስፖርት ከአለም 4ኛ፤

▪️በቲታኒየም ኤክስፖርት ከአለም 4ኛ

▪️የመከላከያ ኢንዱስትሪ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ በዓለም 9ኛ ደረጃ

▪️በብረት ምርት ከአለም 10ኛዋ ስትሆን መጠኑም 32.4ሚሊየን ቶን ነው።

Esleman Abay የዓባይልጅ ✍️

Exit mobile version