ETHIO12.COM

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የፊታችን አርብ ስራውን ሙሉ በሙሉ ያቁማል

በሃገሪቱ ከአስተዳደር ወሰን እና ከማንነት ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመርመር እና የመፍትሄ ሀሳብ ለማቅረብ ከሶስት አመት በፊት የተቋቋው ኮሚሽኑ ተግባሩ እንዳበቃ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተነግሮታል፡፡

መንግሥት ኮሚሽኑን ማቋቋም የፈለገበት ዋነኛ ምክንያት በተደጋጋሚ እየተከሰቱ ላሉ የወሰን ይገባኛል እና የማንነት ጥያቄዎችን ‹ገለልተኛ በሆነ ተቋም በማያዳግም እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍትሔ ማፈላለግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ› እንደነበር ይታወሳል።

ከህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ስራው እንዳበቃ የተነገረው ኮሚሽን እስከአሁን ሲሰራቸው የነበሩ ስራዎችን በሚቀጥለው አርብ መጋቢት 2 ቀን 2014 ሪፖርት እንደሚያቀርብ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ኮሚሽኑ በሶስት አመታት ጉዞው ያካሄዳቸውን ጥናቶች እና የመፍትሄ ሀሳቦች ለተወካዮች ምክር ቤት እና ለፌደሬሽን ምክር ቤት የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በተመሳሳይ አመት የተቋቋመው የእርቀሰላም ኮሚሽንም የስራ ጊዜው አብቅቶ መፈረሱ ይታወሳል፡፡

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ይሰራቸው የነበሩ ስራዎች ሙሉ በሙሉ አሁን የተቋቋመው ብሄራዊ የምክክር ኮሚሽን የሚያከናውናቸው ይሆናል ሲሉ ጉዳይን ዋና ዳይሬክተር ሆነው እየመሩ ያሉት አቶ ጴጥሮስ ወልደ ሰንበት ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ከተቋቋ ሶስት አመታት ያለፉት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በመላ ሀገሪቱ ከአስተዳደር እና ከወሰን ማካለል ጋር የተያያዙ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ይታወቃል፡

ሔኖክ ወ\ገብርኤል

የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም

Exit mobile version