Site icon ETHIO12.COM

“አፍሪካ ኒውክለር ሀይል መገንባት አለባት”

በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ ኒውከለር ሀይል መገንባት እንደሚያስፈልግ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተመራሪ የሆኑት ላውረንስ ፍሪማን ተናገሩ፡፡

አሁኑ ሰአት በናይጄርያ እና በጋና ኒውክሌር ሀይል ለመገንባት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ የተናገሩት ላውረንስ በሁሉም ሀገራት መሞከር አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአፍሪካ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተመራማሪ የሆኑት ላውረንስ ፍሪማን በተለያዩ ጊዜያቶች በአፍሪካ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳችን እያነሱ ትንተናቸው እና የመፍትሄ ሃሳባቸው ሲያቀርቡ የምናውቃቸው ምሁር ናቸው፡፡

አሁን በአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚው እድገት ያላሳየበት ዋነኛ ምክንያት የሀይል አቅርቦቱ እና አጠቃቀሙ ባለመመጣጠኑ ነው ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚያቸው እና የህዝባቸውን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ቢያንስ 1ሺህ ጊጋ ዋት የሀይል አቅርቦት ሊኖራቸው ይችላል ሲሉ ምክራቸውን አቅርበዋል፡፡

አሁን በአህጉሪቱ ካለው የሀይል አቅርቦት አንጻር ሲታይ ይህንን ማሳካት እንደማይቻል የተናገሩት ላውረንስ ፍሪማን ሀገራቱ ፊታቸውን ወደ ኒውክለር ሀይል ማዞር አለባቸው ብለዋል፡፡

በአህጉሪቱ ናይጄርያ እና ጋና የሀይል አቅርቦታቸውን ለማሳደግ የኒውክለር ሀይል ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመራቸውንም በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባወጡት ጹሁፍ አንስተዋል፡፡

በምእራብ አፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ መገንባት የቻለችው ናይጄርያ ከደህንነት እና ከሰላም ጋር በተያያዘ ብዙ ጥያቄዎች ቢነሱባትም ጉዳዩን ከዳር ማድረስ ትሻለች ተብሏል፡፡

እንደዚሁም ጎረቤቷ ጋናም ልክ እንደ ናይጄርያ ሁሉ ኒውክለር ሀይል ለመገንባት ከአሜሪካ ጋር ድርድር እያደረገች እንደምትገኝ ነው ላውረስ የተናገሩት፡፡

ቀሪዎቹ የአፍሪካ ሀገራት የነዚህን ፈለግ መከተል አለባቸው የሚሉት ላውረንስ ጉዳዩ በትኩረት ሊመለከቱት ይገባል ብለዋል፡፡

ባሁኑ ሰአት የምእራባዊያን ሀገራት አሜሪካንን ጨምሮ በተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት የኒውክሌር ሀይል ለመገንባት ደፋ ቀና እያሉ እንደሚገኙ ነው የተናገሩት፡፡

በአፍሪካ ካለው የደህንነት እና የጸጥታ እጦት ጋር በተገናኝ አፍሪካ ኒውክለር ሀይል መገንባት የለባትም የሚሉ ምእራባዊያን ሀገራት እንዳሉም ነው ላውረንስ ፍሪማን የተናገሩት፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል ethiofm 107.8
መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም

Exit mobile version