ከሚከሰቱ ሁነቶች ጋር ተናባቢና ተዛማጅ የሆኑ ተግባራዊ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባም አርከበ ዕቁባይ ገለጹ

“የሚወጡ ዕቅዶችና የሚቀመጡ ግቦች እንደ ዶግማና ርዕዮተ ዓለም ሳይቆጠሩ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በማገናዘብ መስራት የኢኮኖሚ ዕድገት ያመጣል” ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሙያው ዶክተር አርከበ ዕቁባይ ገለጹ።ዘለቄታዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለማስመዝገብ የረጅም ጊዜ እቅድና ሰፊ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸውም ተናግረዋል። ከሚከሰቱ ሁነቶች ጋር ተናባቢና ተዛማጅ የሆኑ ተግባራዊ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል

በአለም ባንክ አዘጋጅነት በተካሄደ “የምስራቅ ኤዢያ – አፍሪካ፡ የዌቢናር ውይይት የተሳተፉት ዶክተር አርከበ፤ “በአፍሪካ የሚፈለገውን የምጣኔ ሃብት እድገት እና ልማት ለማስመዝገብ የረጅም ጊዜ ራዕይ በማስቀመጥ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል” ብለዋል።

እቅዶቹን ከመመሪያ ባለፈ ሰፊ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማካሄድ ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚያስፈለግም ነው የጠቆሙት።“በተለይም የሚታቀዱ ዕቅዶችና የሚቀመጡ ግቦች እንደ ዶግማና ርዕዮተ ዓለም ከመቁጠር ባለፈ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችና በማገናዘብ ተግራባራዊነቱ ላይ መስራት ይገባል” ሲሉ አመላክተዋል።“ይህንንም ከቻይናና ኤዢያ አገሮች መማር እንችላለን” ነው ያሉት።

ሁሉንም አዋጭ ፖሊሲዎችና መንገዶች በመጠቀም በየጊዜው ከሚከሰቱ ሁነቶች ጋር ተናባቢና ተዛማጅ የሆኑ ተግባራዊ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባም ዶክተር አርከበ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 • ትህነግ ሲዘጋ፤ ኢትዮጵያ ትወቀሳለች- እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል?
  ኢትዮጵያዊያን ላለፉት 50 ዓመታት ስለምን በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ይሰቃያሉ? በረሃ ሆኖ ስቃይ፣ መንግስት ሆኖ መከራ፣ ሲባረር ደግሞ ” እኔ የማልመራት አገር ትፍረስ” ብሎ ዘመቻ። የኢትዮጵያ ሕዝብ የድሮው ሳይቆጠር ስለምን ግማሽ መዕተ ዓመት በትህነግ ሲጠበስ ይኖራል? መቼ ነው ይህን ሕዝብ ትህነግ የሚተወው? የሰሞኑ ክተት የሳምንቱ ኩርፊያ ውጤት አይደለም። የተጠራቀመContinue Reading
 • የተመድ የሚል ጽሁፍ ያለበት ኣወሮፕላነ ምስራቅ ሃረርጌ ወደቀ
  ዛሬ አመሻሽ ላይ በምስራቅ ሀረርጌ ስለወደቀው አውሮፕላን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ለኢትዮጵያ ቼክ የሰጠው ምላሽ! ዛሬ አመሻሽ 11 ሰዓት ተኩል አካባቢ አንድ አነስተኛ አዉሮፕላን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ መዉደቁን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል። የኮምቦልቻ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዲ ቡሽራ አራት ሰዎችን የጫነዉContinue Reading
 • በትግራይ ያለው የእርዳታ ምግብ ክምችት የፊታችን አርብ ያልቃል፤ ትህነግ 170 መክኖችን እህል ጭነው እንድይገቡ ከልክሏል
  አሸባሪው ህወሓት ከ170 በላይ እርዳታ የጫኑ ከባድ መኪናዎችን አግቶ ማቆሙን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ አስታወቁ በትግራይ ያለው የእርዳታ ምግብ ክምችት የፊታችን አርብ ያልቃል አሸባሪው ህወሓት ከ170 በላይ እርዳታ የጫኑ ከባድ መኪናዎችን አግቶ ማቆሙን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ አስታወቁ። የዓለም የምግብ ድርጅት በትግራይ ያለው የርዳታ ምግብ ክምችት አርብ ያልቃል ሲል ገልጿል። የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊትContinue Reading
 • “ አሸባሪው የህውሃት ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ ነው -“
  አሸባሪው የህወሓት ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ በመሆኑ በዓለምአቀፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሊጠየቅ እንደሚገባ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) አስታወቀ። ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪ ቡድኑ በትግራይ ክልል እያደረሰ ያለውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ በአግባቡ እንዲረዳ ማድረግ ተገቢ መሆኑም ተጠቁሟል። የትዴፓ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሙሉብርሃን ሃይሌ፤ አሸባሪው ህወሃት የትግራይን ህዝብContinue Reading
 • ኢትዮጵያ እንደገና አንድ ሆና ተሰፋች፤ ደስም አለን!
  ዛሬ ሁሉም ዜጋ ” አገሬ” አለ። ያለ ልዩነት ” ማን እንደ አገር” ብሎ ጮኸ። በራሱ ተነስቶ ” እኔም ወታደር ነኝ ” አለ። ከባህር ማዶ ያሉ ከሃጂዎች አገር ለማፍረስ ሲማማሉ፣ የስልጣን ክፍፍል ሲያደርጉ፣ ግማሾቹ በስተርጅና ሲቀሉ፣ ትርፍራፊ የሚጣልላቸው ሚድያዎች አገራቸው ላይ አድማ ሲጠሩ፣ አንዳንድ ባለሃብት ነን ባዮች ቀን ቀን ቤተ ክርስቲያን፣Continue Reading
 • “አሸባሪው ትህነግ”በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያና በአላማጣ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባታል
  የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት በአውደ ዉጊያ ዉሎው ጠላትን እያንበረከከ ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን አስታወቁ። በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያና በአላማጣ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባታል ዋና ዳይሬክተሩ በቅጥረኛ የትህነግ ተቀጣሪ አክቲቪስቶች በሀሰት እንደሚነዛው መረጃ ሳይሆን በማይጠብሪ፣Continue Reading

Leave a Reply