Site icon ETHIO12.COM

በእነ ዶ/ር ደብረጺዮን የክስ መዝገብ ነዳጅ የዘረፉ ለትህነግ ምሸግ የቆፈሩ ድርጅቶች ክስ ተለዋጭ ቀጠሮ ተበጀለት

ዐቃቤ ህግ በእነ ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የክስ መዝገብ የተካተቱ የሶስት ድርጅት ተወካዮች ዛሬ በችሎት ቢቀርቡም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ አድራሻው ያልተገኘው የካሌብ ኦይል ኢትዮጵያ ተወካይን በተመለከተ አለመገኘቱን በጽሁፍ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ችሎቱን ጠየቀ ፡፡

ችሎቱ መጋቢት 01/2014 ዓ.ም በነበረው ተለዋጭ ቀጠሮ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለትራንስ ኢትዮጲያ፡ ለመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪግ ߹ለሱር ኮንስትራክሽን እና ለካሌብ ኦይል ኢትዪጲያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተወካዮች መጥሪያ እንዲደርስ የሰጠውን ትዛዝ ውጤት ለመጠባበቅ ዛሬ ተሰይሞ ነበር ።

ዛሬ መጋቢት 15/2014 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ”ከካሌብ ኦይል ኢትዮጲያ“ ውጭ ያሉት የሶስቱ ተከሳሽ ድርጅቶች ተወካዮች በችሎት ተገኝተዋል ፡፡

በእነ ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የክስ መዝገብ የተካተቱት እነዚህ አራት ድርጅቶች ከጥቅምት 26 እስከ ህዳር 17 /2013 ዓ/ም ባሉት ጊዚያት ውስጥ ከ71 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ነዳጅ በመጫን እና ነዳጅ በመዝረፍ ߹ በማጓጓዘዝ ስንቅን ጭምሮ በማቅረብ የትግራይ ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮማንድ እንዲገለገልበትና በትግራይ ክልል “ቤተሀዋርያ” በሚባል አካባቢ የሚገኝ ተራራ የጦር ምሽግ በመቆፈር በዚህ ምሽግ የትግራይ ወታደራዊ ኮማንድ ሰሜን ዕዝ 20ኛ ክፍለ ጦርን እንዲጠቃ አድርገዋል ተብለው በዐቃቤ ህግ ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል ፡፡

ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ የቀረቡት ተወካይ ከካሌብ ኦይል ኢትዮጲያ ውጪ ያሉ ሶስቱ ድርጅቶች አድራሻቸውን አፈላልገው ማቅረባቸውን ገልፀው “ካሌብ ኦይል ኢትዮጲያን” በተመለከተ ግን የተወካዩን አድራሻ ቢያፈላልጉም አዲስ አበባ አለመኖሩንና የድርጅቱ መገኛ ”መቖለ“ ከተማ መሆኑን ተከትሎ እንዳላገኙዋቸው ለችሎቱ አስረድተዋል ፡፡

ዛሬ ብችሎት የቀረቡት የድርጅት ተወካዮች የትራንስ ኢትዮጲያ ም/ል ስራ አስኪያጅ (አቶ ሙሉ ብስራት) ߹ የመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪግ ድርጅት የአዲስ አበባ ቅርጫፍ ሃላፊ (አቶ አብርሃ ሃግሎ) እና የሱር ኮንስትራክሽን ድርጅት ደግሞ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር የሆኑት ግለሰብ በተወካይነት ቀርበዋል ፡፡

ዐቃቤ ህግ “ካሌብ ኦይል ኢትዮጲያን” በተመለከተ በቅድሚያ የፌደራል ፖሊስ የድርጅቱ ተወካይ አድራሻ እንዳልተገኘ በጽሁፍ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ነገር ግን መገኘት ካልቻለ የድርጅቱ ተወካዮች በሌሉበት ጉዳዩ እንዲታይ ጠይቋል፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረሽብርና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎትም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ” ካሌብ ኦይል ኢትዮጲያ“ አድራሻ አለመገኘቱን በጽሁፍ ማረጋገጫ እንዲያቀርብና የቀረቡ ሶስት ድርጅቶችን ክስ ደግሞ በንባብ ለማሰማት በመደበኛው ቀጠሮ ለመጋቢት 30/2014 ዓ.ም እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት የችሎቱ ውሎ ተጠናቋል ፡፡

Attorney general

Exit mobile version