Site icon ETHIO12.COM

የዓለም ዋንጫ ድልድል ይፋ ሆነ – ግብጽ ወግጅ ተባለች

የ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል። ለዚሁ ውድድር የመጨረሻ ማጣሪያ ያደረገችው ግብጽ ያስገባችው “የዘርኝነት ተፈጽሞብኛል” ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።

ከሴኔጋል ጋር የሁለተኛውን የማጣሪያ ፍጻሜ ያካሄደቸው ግብጽ 120 ደቂቃ ኳስ ማየት እስኪቀፍ ድረስ ሲያጭበርብሩ፣ ሲተኙ፣ ዳኛ ሲነታረኩ፣ ሰዓት ሲገሉና የስነልቦና ጫና በማሳደር ከሆነ በግርግር ማግባት ካልሆነ የፍጹም ቅጣት ምት ላይ መድረስ ነበር ግባቸው።

የሴኔጋልን ተጫዎቾች ስሜት ውስጥ በመክተት የካርድ ሰለባ ለማድረግ ሲያደርጉት የነበረው ጫናና ትንኮሳ አሰልቺ ነበር። በተለይም ዳኛው ያንን ሁሉ ሲፈቅድ ማየቱ ማነ ነበር መክሰስ የነበረበት የሚል ጥያቄ ያስነሳል። የተገላቢጦሽ በዘረኝነት ተበድለናል በሚል የ120 ደቂቃ ስሜትን የሚፈታተን ደባቸውን ለመሸሸግ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ድልድሉ ይፋ ሆኗል። አክትሟል።

በምድብ 1 አስተጋጇ ኳታር፣ ኔዘርላንድስ፣ ሴኔጋል እና ኢኳዶር፤

በምድብ 2 ደግሞ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ኢራን እና የዌልስ/ስኮትላንድ ወይም ዩክሬን አሸናፊ፤

በምድብ 3 አርጀንቲና፣ ሜክሲኮ፣ ፖላንድ እና ሳዑዲ አረቢያ፤

በምድብ 4 ፈረንሳይ፣ ዴንማርክ፣ ቱኒዚያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች/አውስትራሊያ ወይም የፔሩ አሸናፊ፤

በምድብ 5 ስፔን፣ ጀርመን፣ ጃፓን እና የኮስታሪካ ወይም ኒውዝላንድ አሸናፊ፤

በምድብ 6 ቤልጂየም፣ ክሮሺያ፣ ሞሮኮ እና ካናዳ፤

በምድብ 7 ፖርቹጋል፣ ዑራጋይ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጋና፤

በምድብ 8 ብራዚል፣ ስዊዘርላንድ፣ ሰርቢያ እና ካሜሩን፤

የመክፈቻ ጨዋታው በአስተናጋጇ ኳታር እና በደቡብ አሜሪካዋ ተወካይ ኢኳዶር መካከል የሚደረግ ይሆናል።

Exit mobile version