Site icon ETHIO12.COM

ሕወሓት ባለፉት 40 ዓመታት ከ60 ሺህ በላይ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አማራዎችን መጨፍጨፉ ታወቀ

– አሸባሪው ሕወሓት ከ60 ሺህ በላይ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ነዋሪዎችን ጨፍጭፏል፤

– በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አካባቢዎች ከ12 በላይ የጅምላ መቃብሮ መገኘታቸውን ገልጿል፤


አሸባሪው ሕወሓት ባለፉት 40 ዓመታት ከ60 ሺህ በላይ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አማራዎችን መጨፍጨፉን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ጥናት ማረጋገጡን አስታወቀ፡፡

በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አካባቢዎች ከ12 በላይ የጅምላ መቃብሮ ተገኝተዋል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህብረተሰብ ጤና መምህር፣ ተመራማሪና የጥናት ቡድኑ መሪ ረዳት ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በጥናትና ምርምር ውስጥ ዩኒቨርሲቲው ከባለፈው ዓመት ጀምሮ አሸባሪው ሕወሓት ላለፉት አርባ ዓመታት በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ላይ ያደረሰውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት በጀት በመመደብ የሚመለከታቸው ባለሙያዎችን አዋቅሮ በማሰማራት ጥናት እያካሄደ ይገኛል፡፡ እየተካሄደ ያለው ጥናት ሰፊ መሆኑን የገለጹት የጥናት ቡድን መሪው፤ ሕውሓት ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ አካባቢውን በወረራ ከያዘ ጊዜ ጀምሮ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አማራዎች ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውንና ማንነታቸውን እንዳይገልጹ መደረጉንም ሆነ አለመደረጉን ለመለየት ጥናት ተደርጓል፡፡

ከምጣኔ ሀብት ዘረፋና ወረራ፣ በጤናና ትምህርት ላይ የደረሰውን በደል የሚዲያ ሽፋን እንዳያገኙ የተደረገበት ስልት የሚዳስስ ጥናት መካሄዱን ገልጸዋል፡፡

ጥናቱ በአካባቢው ያለውን ማህበረሰብ በመሰብሰብ በቡድን ውይይት እንዲያደርጉ በመጋበዝ፣ ታሪክ አዋቂዎችን በመጠየቅ፣ በደል ደርሶብናል ብለው የሚያስቡ ሰዎችን በተለያዩ አግባቦች በማናገር፣ ከዚ በፊት በአስተዳደር የነበሩና አሁን በምረት ወደ አካባቢው የገቡ ሰዎችን በመጠየቅ አጠቃላይ የነበረውን ግፍ የመለየት ስራ ተሰርቷል፡፡ በተገኘው ጥናት መሰረት አሁን ላይ በቤት ውስጥ የቀሩ ዜጎች ላይ በተደረገ ቃለመጠይቅና በሌሎች ማስረጃዎች 19 በመቶ የሚሆኑ አባወራዎች አድራሻቸው እንዲጠፋ፣ 25 በመቶው ሕዝብ እንዲገደልና 29 በመቶ የሚሆነው ደግሞ አካባቢውን ለቆ እንዲሰደድ ተደርጓል፡፡

በአጠቃላይ 75 በመቶ የሚሆኑት የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አማራዎች እንዲገደሉ፣እንዲፈናቀሉና አደራሻቸው እንዲጠፋ መደረጉንም ሆነ አለመደረጉን ለመለየት ጥናት ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም ከምጣኔ ሀብት ዘረፋና ወረራ፣ በጤናና ትምህርት ላይ የደረሰውን በደል የሚዲያ ሽፋን እንዳያገኙ የተደረገበት ስልት የሚዳስስ ጥናት መካሄዱን ገልጸዋል፡፡

ጥናቱ በአካባቢው ያለውን ማህበረሰብ በመሰብሰብ በቡድን ውይይት እንዲያደርጉ በመጋበዝ፣ ታሪክ አዋቂዎችን በመጠየቅ፣ በደል ደርሶብናል ብለው የሚያስቡ  ሰዎችን በተለያዩ አግባቦች በማናገር፣ ከዚ በፊት በአስተዳደር የነበሩና አሁን በምረት ወደ አካባቢው የገቡ ሰዎችን በመጠየቅ አጠቃላይ የነበረውን ግፍ የመለየት ስራ ተሰርቷል፡፡   በተገኘው ጥናት መሰረት አሁን ላይ በቤት ውስጥ የቀሩ ዜጎች ላይ በተደረገ ቃለመጠይቅና በሌሎች ማስረጃዎች 19 በመቶ የሚሆኑ አባወራዎች አድራሻቸው እንዲጠፋ፣ 25 በመቶው ሕዝብ  እንዲገደልና 29 በመቶ የሚሆነው ደግሞ አካባቢውን  ለቆ እንዲሰደድ ተደርጓል፡፡ 

በአጠቃላይ 75 በመቶ የሚሆኑት የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አማራዎች እንዲገደሉ፣እንዲፈናቀሉና አደራሻቸው እንዲጠፋ መደረጉ በጥናቱ መረጋገጡን ረዳት ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል፡፡

እንደ ረዳት ፕሮፌሰሩ ገለጻ፤ አድራሻቸው የጠፋ ሰዎችን አስመልክቶ የጥናት ቡድኑ ባደረገው ምርመራ የሽብር ቡድኑ በርካታ ሰዎችን ‹‹ባዶ ስድስት›› በሚል ስያሜ በሚጠራው ስፍራ በጅምላ በማጎር ማህበረሰቡ የሚደርስበትን ግፍ መረጃ እንዳያወጣ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ 

ማህበረሰቡ በጭንቀት ውስጥ እንዲኖርና ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጥ ለአርባ ዓመታት በነበረው አገዛዝ ውስጥ የስነልቦና ጫና በማህበረሰቡ ላይ ደርሷልም ብለዋል፡፡ 

በአካባቢው  የጥናት ቡድኑ በደረሰበት ወቅት በሕወሓት የደረሰባቸውን ግፍ  ግድያ፣ መፈናቀልና ሌሎች ጫናዎች እያወቁ መናገር አይፈልጉም ነበር፡፡ ነገር ግን ቀስ በቀስ በተደረገው የማግባባት ሥራ አንድ ጅምላ መቃብር ጭምር እንደተገኘ ጠቅሰዋል፡፡ 

በወልቃይት አድኖ፣ ገሃነም፣ ተከዜ ውስጥ ያሉ የጅምላ መቃብሮች፣ ትግራይ ክልል ውስጥ ደደቢትና ሌሎች ሶስት ቦታዎች ላይ ጠለምት ውስጥ ፍየል ውሃ፣ ሰይጣን መጣያ በሚባሉ ቦታዎች የጅምላ መቃብር እንዳሉ የጥናት ቡድኑ ባደረገው ጥናት ማረጋገጥ መቻሉን ረዳት ፕሮፌሰር ጌታ ጠቅሰዋል፡፡

ሰዎች በጅምላ ሲታሰሩና ሲገደሉ እንደነበር በወቅቱ የከብት እረኞች ሳይቀር ያውቁ እንደነበር የጠቀሱት የጥናት ቡድኑ መሪ፤ ወደፊት የሚወጡ ብዙ መረጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው 12 ዋና ዋና ቦታዎ ላይ ከፍተኛ የጅምላ መቃብሮች እንዳሉ በቂ መረጃ ተገኝቷል ብለዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ሰፊ የሚባለውና በዚህ ዓመት በማይካድራ እደተፈጸመው ጭፍጨፋ በርካታ ሰዎች የተሰቃዩበትና የተቀበሩበት ‹‹ገሃነም›› ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ሲሆን ቦታው ለየትኛውም አገልግሎት ተደራሽ ያልሆነ አካባቢ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የጥናት ቡድን አባላት በአካባቢው ከአሸባሪው የሕውሓት ቡድን ጋር በቅርብ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎችን አግኝቶ በማነጋገር ባገኘው መረጃ ባለፉት 40 ዓመታት ከ60 ሺ በላይ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ነዋሪዎች በግፍ ታስረው እንዲረሸኑ መደረጉ ማረጋገጡን ጠቅሷል፡፡

የጅምላ መቃብሮቹ  በተጠናና በሚስጥር በተደራጀ መንገድ የወንዝ ተፋስስ መሰረት አደርጎ በመቀበራቸው በክረምት አጽሙ በጎርፍ እንዲወሰድ ተደርጓል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ለወደፊት በታሪክ እንዳይገኝና ታሪክን ለማጥፋት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ በተፋሰስ የተቀበሩ ሰዎች አጽም ወደ ተከዜ ወንዝ እንዲለቀቁ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡ 

በጀርመን ናዚ ስርዓት በጅውሽ የዘር እልቂት በዋናነት ጅዊሽ ላይ የነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች የጥናት ቡድን በሟቋቋም እንደሠሩ ሁሉ በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ እያንዳንዱን ጉዳይ ምርመራ በማድረግ ዝርዝር ጥናት በቋሚነት የሚሠራ (center for genocide study) ወይም የጅምላ ጭፍጨፋ የጥናት ማዕከል በማቋቋም እንደሚሠራ ረዳት ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል፡፡

ሞገስ ተስፋ

አዲስ ዘመን መጋቢት 28 ቀን 2014 ዓ.ም

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70240

Exit mobile version