Site icon ETHIO12.COM

በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ12 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ተያዘ

በሰሜን ጎንደር ዞን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ12 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ መያዙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የዞኑ አስተዳደር ሕገ-ወጥ የንግድ ሥርዓትን ለመከላከል ለአንድ ወር ያክል በሠራው የቁጥጥር ሥራ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኢንዱስትሪ ውጤቶች እና የግብርና ምርቶች መያዛቸውን የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዝናቸው ንጉሤ ገልጸዋል።

ምርቶቹ የተያዙት የዞኑ አስተዳደር ጥምር ኃይል አቋቁሞ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በቤት ለቤት አሰሳ እና በኬላዎች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑን አስታውቀዋል።

በድርጊቱ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ 41 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸው መገለጹን አሚኮ ዘግቧል።

በንግድ ሥርዓቱ ላይ ሰው ሠራሽ ችግር ሲፈጥሩ በተገኙ 320 ድርጅቶች ላይም ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።

ENA

Exit mobile version