Site icon ETHIO12.COM

ዕርድታ የተሸከሙ 47 ተሽከርካሪዎች ወደ መቀለ አቀኑ፤ ትህነግ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች እንዲለቅ ተዘዘ

የሰብአዊ እርዳታ የጫኑ የተባባሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም የምግብ ፕሮግራም 47 ተሽከርካሪዎች ወደ መቀሌ ማቅናታቸውን ተገለጸ። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በወረራ ከያዝቸው አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ ታዘዘ።

https://videos.files.wordpress.com/5Zroz1yT/6455751834405562989.mp4
Arrived video from Mekele

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ እንዳለው ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ያመሩት ምግብ፣ ምግብ ነክና ሌሎች ህይወት አድን ዕርዳታ ተሸክመው ነው። ከምግብና ምግብ ነክ ነብስ አድን የዕርዳታ ቁሶች በተጨማሪ ሶስት ቦቴ ነዳጅ የጫኑ መኪናዎችም አሉበት። የዓለም ፕሮግራም ተሽከርካሪዎቹ ያለምንም ችግር እየተጓዙ መሆኑንም ይፋ አድርጓል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የትህነግ ታጣቂዎች በሃይል ወረው ከያዟቸው አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ ቀደም ሲል በተደረገ ንግግር አሜሪካ አዲስ ለሾመቻቸው የምስራቅ አፍሪቃ ልዩ መልዕክተኛ ቃለ ገብተው እንደነበር ያስታወቁ የዝግጅት ክፍላችን ተባባሪ መረጃ አቀባዮች ትህነግ ቃሉን ባለማክበሩ ልዩ መልዕክተኛው ቅሬታቸውን ገልጸዋል። መንግስትም ይህንኑ አስረድቷል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዲስ መሳሪያ ታጥቆና ከወትሮው በበለጠ ጉድለቱን አስተካክሎ ለማናቸውም ዘመቻ ዝግጁ እንደሆነ በማመልከት ለሰላም ሲባልና ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ ሲባል የተኩስ አቁም እርምጃ መውሰዱ በትህነግ በኩል በበጎ እንዳልታየ መንግስት አቤቱታውን አቅርቧል። ሕዝብም ቅሬታ እየገለጸና በአፋርና አማራ ክልል ሰላማዊ ነዋሪዎች ተወረው መንግስት ዝምታ መምረጡ እንደ ከፍተኛ ድከመት እየታየ መሆኑን፣ ይህ ደግሞ ፖለቲካዊ ችግር እንደሚያመጣ፣ ትህነግ ዓላማው ይህ እንደሆነ አስታውቋል።

መንግስት አምርሮ ባቀረበው ቅሬታ ላይ አስፈላጊ ከሆነ በቀናት ውስጥ የተወረሩ አካባቢዎችን ማስለቀቅ በአሁኑ ወቅት አስቸጋሪ እንዳልሆነ፣ የትህነግ አካሄድ የማይታረምና ሙሉ ለሙሉ ለሰላም ሙሉ በሙሉ የማይተባበር ከሆነ በማንኛውም ሰዓት መንግስት ሃይል ሊጠቀም እንደሚችል ማስታወቁን የመረጃ ምንጮቹ አመልክተዋል።

አቤቱታው በወኪሎቻቸው አማካይነትና በአሸማጋዮች በኩል የደርሳት አሜሪካ ትህነግ በሃይል ከያቅዝቸው አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ የመጨረሻ መመሪያ የተሰጠው ከሶስት ቀን በፊት የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድና ምክትላቸው ፓይተን ኖፍ ወደ አዲስ አበባ ከማቅናታቸው በፊት ነው። ለጉዳይ ቅርብ የሆኑ እንዳሉት ትህነግ ትናንት ከተወሰኑ የአፋር አካባቢዎች መልቀቁን ለትግራይ ሕዝብ ያስታወቀው ከዚህ ማስተንቀቂያ በሁዋላ ነው።

ሕዝብ በሁሉም አቅጣጫ ሰላም እንደሚፈልግ እየገለጸ ነው። አገሪቱ ውስጥ የተከሰተው ቀውስ እጅግ አሳሳቢ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ጦርነት አማራጭ ባለመሆኑ ” የእሳካሁኑ ይብቃ” የሚሉ በርክተዋል። በትግራይ የከፋ ችግር እንዳለ ሁሉ በዋግ ህምራና በአፋር እየሆነ ያለው ሁሉ ለነገ የሚባል እንዳልሆነ የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው።

አሜሪካ በአምባሳደሯ በኩል በጀመረችው የጫና ድርድር ትህነግ ከያዘው በታ ሁሉ ለቆ እንዲወጣ በታዘዘው መሰረት የማያደርገው ከሆነ አማራ ክልል የራሱን እርምጃ ሊወስድና ወገኖቹን ሊታደግ እንደሚችል ለፌደራል መንግስት ማሳሰቢያ መስጠቱን የጠቀሱ እንዳሉት፣ መንግስት የአማራ ክልልን አቤቱታና ማስጠንቀቂያ እንደሚጋራ ጠቅሶ ለሚመለከታቸው የትህነግ ደጋፊዎች ማስታወቁ ታውቋል።

መልዕክተኛው አዲስ አበባ በገቡ ማግስት ሰፊ ቁጥር ያለው እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ አቅንተዋል። ትህነግም የተባለውን በተግባር ለመፈጸምና ሪፖርት ለማድረግ ቃል መግባቱን ያገኘነው መረጃ ያመለከታል።

Exit mobile version