ETHIO12.COM

የም.አፍሪቃ ስጋቶች በተባሉ ላይ የውሳኔ አሳብ ለማቅረብ የቀጣናው አገራት የጦር ጀነራሎች ምክር ላይ ናቸው፣ መግለጫ ያወጣሉ

– በምስራቅ አፍሪቃ አልሸባብ፣ ሸኔና ትህነግ ሊያደርሱት የሚችሉት የጸጥታ ስጋት ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ፣ ከሱዳን፣ ከዩጋንዳ፣ ከደቡብ ሱዳንና ከታንዛኒያ በመጡት ከፍተኛ የጦር ጀነራሎች እየተመከረበት መሆኑ ታውቋል፤

ለሁለት ቀናት የሚቆየዉ የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያ ኢንተለጀንስ ፎረም የምስራቅ አፍሪካን የጸጥታና የደህንነት ስጋቶችን በመተንተን የዉሳኔ ሃሳቦችን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ያልተለመደ የቀጠናው አገራት የጦር ጀነራሎች ስብሰባ በጋራ የተካሄደው የኢትዮጵያን መንግስት በግል አገራቱ ጋር ምክክር ካደረገ በሁዋላ ነው።

በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ በሚገኘዉ ፎረም ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከጅቡቲ: ከሶማሊያ: ከሱዳን: ከዩጋንዳ: ከደቡብ ሱዳንና ከታንዛኒያ የመጡ የመከላከያ የመረጃ ኦፊሰሮች መሳተፋቸውን የመንግስት የዜና አውታሮች አመልክተዋል።

በኢፊዲሪ መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌ/ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ በተዘጋጀችዉ የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያ መረጃ ፎረም ላይ የተሳተፉ የተለያዩ ሃገራት የመከላከያ አመራሮችን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኦቢኤን ዘግቧል። ጀነራሉ የፎረሙ ዋና አላማም የምስራቅ አፍሪካ ሃገራትን አብሮነትና የጋራ ትብብር ማጠናከር እንደሆነ አመክተዋል። በምስራቅ አፍሪካ የሚታየዉን የጸጥታ ስጋትና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ከመከላከል ረገድ ፎረሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ሲሉ አክለዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየዉ ፎረም ላይ የጸጥታ ስጋቶችን ቀድሞ ማወቅና ቀድሞ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ወይይት ይደረጋል። ፎረሙ ተወያይቶ የሚያጸደቃቸዉ ጉዳዮች ለሃገራቱ ሕግ አዉጪዎችና የመከላከያ አመራሮች የሚቀርቡ መሆናቸዉን የተናገሩት ሌ/ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ፎረሙ መልካም አጋጣሚዎችንና ስጋቶችን ለመወሰን ያግዛል ብለዋል። ዘርዝሩ ባይገለጽም በምስራቅ አፍሪቃ አልሸባብ፣ ሸኔና ትህነግ ሊያደርሱት የሚችሉት የጸጥታ ስጋት በቀጠናው ስጋትና የስጋት ማስወገድ ትንተና አግባብ ምክር ከሚደረግባቸው ቅድሚያዎቹ ናቸው። ትህነግ ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት እንዳለው በተደጋጋሚ ሲገለጽ መቆየቱ የሚታወስ ነው።


ህወሃት በሚያኮርፍባቸው የሶማሊያ ‹አሸባሪ› ድርጅቶች ይጠረጠራል

ህወሃት በሶማሊያ ከሚንቀሳቀሰው አሸባሪ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለው ተብሎ 


በፎረሙ ላይ የተሳተፉት የሶማሊያዉ የመከላከያ መረጃ ደህንነት ዳይሬክተሩ ሜጀር ጄኔራል ሰዓድ መሃመድ ሰዓድ ፎረሙ የምስራቅ አፍሪካን ደህንነት ከማረጋገጥ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ማለታቸው ተሰምቷል። አገራቸው ካለችበት ችግርና በርካታ ዋጋ ከመትከፍለበት የአልሸባብ ጉዳይ ጋር አያይዘው ሰፊ መረጃ ማቅረባቸው ታውቋል።

የጂቡቲዉ የመከላከያ መረጃ ደህንነት ኃላፊዉ ኮለኔል ሜጀር አደን ዑዳሌ ፎረሙ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ተመሳሳይ አቋምና ስትራቴጂ እንዲኖራቸዉ ከማድረግ አንጻር ትልቅ ጠቀሜታእንዳለው አመልክተው በአፋር በኩል ለጅቡቲ የሚደገሰውን ድግስ በማንሳት ስግታቸውን በይፋ አንስተዋል።

ይህ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያ ኢንተለጀንስ ፎረም በተከታታይ በተሳታፊ አገራቱ በየተራ እንደሚካሄድና በመንግስት ደረጃ አቋም የሚያዝበት እንደሆነ ከስብሰባው የሚወጡ መረጃዎች ያመልክታሉ። ምክክሩ በሚይዘው አቋም መሰረት ህግ ሆኖ የሚወጣ ሰነድ እንደሚዘጋጅ ታውቋል።

ኢትዮጵያ ትህነግን በአፍሪቃ ደረጃ አሸባሪ ለማሰነት በቀጣናው ቅድሚያ ስራ መጀመሯን ጠቅሰን ዘግበን ነበር።

Exit mobile version