Site icon ETHIO12.COM

«ግብፅንና ሱዳን የሚጎዱበት ምክኒያት የለም» ሃምዛ ናስር

ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡን ስትገነባ ራሷን ከመጥቀም ባለፈ የሌሎችንም ጥቅም ታሳቢ አድርጋ እንጅ እንደሚባለው ግብፅንና ሱዳንን ለመጉዳት አደለም ።

የመካከለኛው ምስራቅ የውሃ ፎረም ፕሬዝዳንት የሆኑት ሃምዛ ናስር አልጀዚራ ላይ በነበራቸው ኢንተርቪው ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ ነው።

እንደ ሃምዛ አስተያየት ከሆነ ኢትዮጵያ ከግድቡ ሀይል ማመንጨት በመጀመሯ የግብፅና የሱዳን ወንድሞቻችን የውሃ ደህንነታችንን ይጎዳል የሚለው ክስ መሰረት ቢስ ነው ሲሉ አጣጥለውታል።

ግብፅና ሱዳን እንኳንስ አሁን ግድቡ በአንድና በሁለት ተርባይን ስራ መጀመሩ «.ሊጎዱ..» ይቅርና ግድቡ ተጠናቆ ኢትዮጵያ በይፋ ያስታወቀችው አስራ ሦስቱም ተርባይኖች ተገጥመው ስራ ሲጀምሩም የታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች ከግድቡ ይጠቀማሉ እንጅ ምንም ነገር የሚጎዱበት ምክኒያት የለም ነው ያሉት።

አክለው ዶክተር ሃም የተርባይኖች ቁጥር በጨመረ ቁጥር የጉዳት መጠኑ ይቀንሳል
እንጅ የተርባይኖች ቁጥር መጨመሩ ማንኛውንም ሀገራት አይጎዳም ብለዋል።

የካይሮ ወንድሞቻችን ደጋግመው ስለውሃ
አለቃቅ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ዋስትና ይሰጠን ሲሉ ይደመጣሉ ። በግድቡ የሚገጠሙት አስራ ሶስቱ ተርባይኖች እያንዳንዳቸው በአመት እስከ ግማሽ ቢሊዮን የሚደርስ ውሃ ግዴታ ከግድቡ ይለቃሉ። ይኸ ማለት ደግሞ ከ30 ቢሊዮን
ኪዩቢክ በላይ ውሃ ይሄድላቸዋል ማለት ነው።

ግብፆች ከዚህ የተሻለ ምን አይነት የዋስትና ማረጋገጫ ነው የሚፈልጉት በማለት የጠየቁት ዶክተር ሃምዛ፣ አክለውም
የህዳሴ ግድቡ የሀይል ማመንጫ ግድብ በመሆኑ ውሃን ይዞ ማስቀረት አይችልም
ኢትዮጵያም በውሃዋ የመጠቀም መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታ አለባት ብለዋል ።

አገሪቱ ወደፊት መስኖ ተኮር ኢኮኖሚ ላይ አትኩራ መስራቷ ስለማይቀር ሌሎች ግድቦች መገንባቷ አይቀሬ። ስለዚህ በተፋሰሱ ዙሪያ ያሉ ሀገሮችም በተመሳሳይ የልማት ፕሮጀክት ነድፈው መንቀሳቀሳቸው
አለባቸው እንጅ ኢትዮጵያን ተፈጥሮ በሰጣት ሀብቷ እየታገሉ የዘላለም ዋስትናቸውን ማስጠበቅ አይችሉም። አገሪቱን ከዚህ በኋላ በምንም አይነት ተአምር ከናይል ወንዝ ፖለቲካና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ መግፋት አይቻልም።

ስለዚህ ግብፃውያን የውሃ ፍላጎታችውን ማሟላት ይችሉ ዘንድ ከ ሀገራቸው የውሃ ሀብት ውስጥ ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም አቅደው ከወዲሁ መንቀሳቀስ መጀመር ያዋጣቸዋል። በማለት የወንድማዊ ምክራዊ ሀሳባቸውን ለግሰዋል

Abay News Network

ዩቲዩብ https://youtu.be/1riQyH2_eLE

Exit mobile version