ETHIO12.COM

‹‹በትግራይ በእርዳታ የመጡ መድኃኒቶች አዳዲስ ፋርማሲ ቤቶች ተከፍተው እየተሸጡ ነው›› ዶ.ር አረጋዊ

ትምህርት ቤቶችና የምርምር ተቋማት (አምአይቲ) የቁስለኞች መናኸሪያ ሁነዋል ያሉት ዶክተሩ፤እንደዛም ሆኖ መድኃኒትና የህክምና አገልግሎት የለም፤ይህን ተከትሎ ቁስለኞቹ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች እንደ አመፅ ተቆጥሮ የሚገደሉ

በትግራይ ክልል የመድኃኒት እጥረት ቢኖርም መቀሌ ከተማ ውስጥ ግን አዳዲስ ፋርማሲ ቤቶች ተከፍተው መድኃኒት ሲሸጡ አይተናል ሲሉ የዓይደር ሆስፒታል ሃኪም ዶክተር አረጋዊ ሐጎስ ገለፁ፡፡

ዶክተር አረጋዊ ሐጎስ ‹‹ስለ ሀገር›› በተሰኘው የኢቢሲ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት፤በመቀሌ በህዝብ ሆስፒታሎች የመድኃኒት እጥረት ቢኖርም በእርዳታ የመጡ መድኃኒቶች አዳዲስ ፋርማሲ ቤቶች ተከፍተው እየተሸጡ ነው፡፡

የምግብ እርዳታዎችና መድኃኒቶች ወደ ህዝብ ተደራሽ ይሆናሉ ወይ የሚል ጥያቄ አለኝ? ያሉት ዶክተሩ፤ለአንድ ሰው 15 ኪሎ ግራም ስንዴ ቢሰጥም እንጀራ ከተጋገረ በኋላ የአሸባሪው የሕወሓት ቡድኖች ህዝቡን ለታጣቂ ሀይላቸው አዋጡ እያሉ በዕርዳታ ያገኘውን እህል በእንጀራ መልክ መልሰው ስለሚወስዱት ህዝቡ በከባድ ችግር ውስጥ ይገኛል ብለዋል፡፡

ትምህርት ቤቶችና የምርምር ተቋማት (አምአይቲ) የቁስለኞች መናኸሪያ ሁነዋል ያሉት ዶክተሩ፤እንደዛም ሆኖ መድኃኒትና የህክምና አገልግሎት የለም፤ይህን ተከትሎ ቁስለኞቹ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች እንደ አመፅ ተቆጥሮ የሚገደሉ ብዙ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ዶክተር አረጋዊ ሐጎስየሽብር ቡድኑ አመራሮች ሳይሸማቀቁ ለትግራይ ህዝብ 370 ሺ ወጣት የት እንደገባ አይታወቅም ብለው ሲናገሩ በተዘዋዋሪ ሙቷል እንዳሉትና፤የቆሰለው፣እጅና እግሩ የተቆረጠ ብዙ ወጣት መኖሩን እንደተመለከቱ አወስተው፤የትግራይ ወጣት ሰርቶ መኖር ሲችል በስልጣን ጥመኞችና ዓላማ በሌለው ጦርነት ህይወቱን መገበሩና መሰቃየቱ ስህተት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የሕወሓት ሽብር ቡድን በወሎ አካባቢዎች በርካታ መድኃኒቶች መዝረፉን ያወሱት ዶክተሩ፤ተጭነው የተወሰዱ መድኃኒቶች፣ ገንዘብና ንብረት የት እንደገባ አይታወቅም፤ሌላው ቀርቶ ሲጭኑ የነበሩት ወጣቶች ሳይቀር ወዴት እንደሄዱ አያውቁም ብለዋል፡፡

አሁን በትግራይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ እጅግ የሚያሳዝንና፤ተስፋ የቆረጡ ወጣቶች ማየት የተለመደ ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ ፤የሽብር ቡድኑ አሁንም ወጣቶችን በግድ እያስታጠቀ ወደ ጦርነት ለማስገባት እየተረባረበ እንደሚገኝ ወላጆችም ቀድመው ወደ ጦርነት የወጡ ‹‹ልጆቻችን የት ናቸው›› የሚል ጥያቄ ሲያነሱ የሽብር ቡድኑ አመራሮች ‹‹እንደዚህ አይነት ጥያቄ አሁን አታንሱ ግዜው አይደለም›› እያሉ እንደሚያሸማቅቋቸውና ለእስር እንደሚዳርጓቸው ተናግረዋል፡፡

አሁን በትግራይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ እጅግ የሚያሳዝንና፤ተስፋ የቆረጡ ወጣቶች ማየት የተለመደ ነው ፤የሽብር ቡድኑ አሁንም ወጣቶችን በግድ እያስታጠቀ ወደ ጦርነት ለማስገባት እየተረባረበ እንደሚገኝ ወላጆችም ቀድመው ወደ ጦርነት የወጡ ‹‹ልጆቻችን የት ናቸው›› የሚል ጥያቄ ሲያነሱ የሽብር ቡድኑ አመራሮች ‹‹እንደዚህ አይነት ጥያቄ አሁን አታንሱ ግዜው አይደለም›› እያሉ …

‹‹ በአሁኑ ጊዜ የቀረው የትግራይ ወጣት ወደ ዘመቻ እንዲገባ በሽብር ቡድኑ እየተገደደ መሆኑን አመልክተው፤ ወጣቱ ‹‹የምንሞተውና የምንቆስለው ለማነው?›› የሚል ጥያቄ እንደሚያነሳም ጠቅሰዋል፡፡

ዶክተር አረጋዊ ሐጎስ

እንደዚህ ያሉ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ወጣቶች ‹‹ አሁን እንደዚህ አይነት ጥያቄ መነሳት የለበትም›› በማለት ለእስርና ለከባድ ቅጣት እየተዳረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ህዝብ በተለይ አረጋውያን ከቀያቸው መውጣትና መፈናቀል አይገባቸውም፤የትግራይ ህዝብ በሆዱ ብቻ ሳይሆን በአእምሮም አስረውታል፤ዙሪያውን በጠላቶች እንደተከበበ አድርገው በመሳል በፍርሃት እንዲሸበብ አድርገውታል፡፡

ዶክተር አረጋዊ ሐጎስ በዋጅራት ዓዲ ቀይሕ ከተማ የተወለዱ ሲሆኑ፤መቀሌ ዓይደር ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ሙያ ስፔሻላይዝ እየተማሩና በሙያቸው ህዝብን እያገለገሉ ሳለ፤እየተባባሰ በመጣው አሰቃቂ የህዝብ ስቃይና መከራ ከመቀሌ በእግር ተጉዘው ወደ መከላከያ ሰራዊት እንደገቡ ተናግረዋል፡፡

የሕወሓት ቡድን ወደ አማራ ክልል በገባበት ወቅት መድኃኒትና ንብረት ዘርፏል፤የዓለም ጤና ድርጅትና ሌሎች ድርጅቶች መድኃኒትና የህክምና ቁሳቁሶች ወደ መቀሌ በአውሮፕላን እያደረሱ እንደነበር ይታወቃል፡፡በመቀሌ ከተማ ከፍተኛ የመድኃኒት እጥረት ቢኖርም በአንጻሩ አዳዲስ ፋርማሲ ቤቶች ተከፍተው መድኃኒት እየሸጡ ስለሆነ ህዝብ ሊጠይቅ ይገባል ብለዋል፡፡

ሄርሞን ፍቃዱ

አዲስ ዘመን ሚያዝያ 22 ቀን 2014 ዓ.ም

Exit mobile version