Site icon ETHIO12.COM

ከሳኡዲ ተመላሾች መካከል ወንጀል የፈጸሙ ላይ ምርመራ ሊጀመር ነው- የሰው ንግድ አንዱ ነው

ከሳውዲ አረቢያ ተመላሽ ዜጎች መካከል ያሉ አጥፊዎችን በምርመራ ለመለየት የሚያስችል የምርመራ ቡድን ወደ ሥራ እንዲገባ አቅጣጫ ተሰጠ

የምርመራ ቡድኑ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ እንዲገባ አቅጣጫውን የሰጠው በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ነው ።
በሰው መነገድና ሰዎችን ድንበር ማሻገር ወንጀሎች ከሳውዲ አረቢያ ተመላሾች መካከል የሚኖሩ አጥፊዎችን ለህግ ማቅረብና የወንጀል ተሳትፎ ያላቸው ግለሰቦች ከመለየት አንፃር ልዩ የምርመራ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ሥራ አንዲገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል ።
መንግሥት በሰዎች የመነገድ ወንጀልና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና የዚህ ወንጀል ሰለባ የሆኑ ዜጎችን መብት ለማስከበርና ተጋላጮችን ለማስተማር የሚያስችሉ የተለያዩ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባሻገር ወንጀሉን ለመግታት የሚያስችል የሕግ ሥርዓት የተዘረጋ ቢሆንምና መሻሻሎች ቢኖሩም እስካሁን ግን የሚጠበቀውን ያህል ውጤት ማምጣት አለመቻሉ ተገልጿል ።

ሕገ-ወጥ ድርጊቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥር እየሰደደ እና መልኩን በመቀያየር እየተባባሰ በመምጣቱ ዜጎችን ለአስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና እንግልት እየተዳረጉ በመሆኑ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉም የበኩሉን አንዲወጣና ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አንዲሁም የወንጀሉ ተጠቂ ቤተሰቦች ወይም ማህበረሰቡ አዘዋዋሪዎችን ለህግ አስከባሪ አካላት መጠቆም ተገቢ እንደሆነ በውይይቱ ላይ ተነስቷል ።

የምርመራ ዕቅዱ በፍትሕ ሚኒስቴር ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል߹ ከፌደራል ፖሊስ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ለተውጣጡ ባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን በዕቅዱ ላይ ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች በአዘጋጆች ተገቢው ምላሽ ተሰጥቷል ።

የምርመራ ቡድኑ በንዑስና በቴክኒክ ቡድን ተከፋፍሎ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ አንዲገባ አቅጣጫ በመስጠት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ።

Via attorney general

Exit mobile version