Site icon ETHIO12.COM

“ከውስጥ በር ለማስከፈት … ከጣራ በላይ ጩኸት” አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘ

” ከጣራ በላይ ጩኸት” ሲል የጠራውን ዘመቻ አብን ሲቃወም ያቀረበው ምክንያት ” ለሶስተኛው ዙሩ የትህነግ ወረራ መንገድ ተራጊዎች” በማለት ነው። የአማራ ክልል አመራሮች በስልታን የሚፋተጉ መሆናቸውን እንደ ችግር አንስቶ የወቀሰው አብን፣ የህግ ማስከበሩን ዘመቻ እንደሚደግፍ ደፍሮ አቋሙን አስታውቋል። ይሁን እንጂ አፈሳጸሙ ላይ የሚታዩ ግድፈቶች መታረም እንዳለባቸው አስታውቋል።

ሕዝብ በአዋኪዎች መማረሩን በዝርዝር ያነሳው አብን የህግ ማስከበሩ ዘመቻ ህግን ያከበረ እንዲሆን ጠይቋል። አያይዞም “መቀመጫቸውን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ያደረጉና በጠላት የኃይል አሰላለፍ ውስጥ የገቡ በ “ጸረ-ብልጽግና-አቋም” ሽፋን ለአሸባሪው ትሕነግ ስልታዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ግለሰቦች እና ቡድኖች ለክልሉ አለመረጋጋት ተጨማሪ ምክንያት መሆናቸውን አብን ይረዳል፡፡ በአማራ ብሔርተኝነት ጭምብል ዲጅታል ወያኔ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚመራው የማወናበጃ ዘመቻም ለክልሉ እና ለሀገር አለመረጋጋት ተጨማሪ ፈተና መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል” ብሏል።

ሙሉ መግለጫውን ከስር ያንብቡ።

በተጨማሪም መቀመጫቸውን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ያደረጉና በጠላት የኃይል አሰላለፍ ውስጥ የገቡ በ “ጸረ-ብልጽግና-አቋም” ሽፋን ለአሸባሪው ትሕነግ ስልታዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ግለሰቦች እና ቡድኖች ለክልሉ አለመረጋጋት ተጨማሪ ምክንያት መሆናቸውን አብን ይረዳል፡፡ በአማራ ብሔርተኝነት ጭምብል ዲጅታል ወያኔ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚመራው የማወናበጃ ዘመቻም ለክልሉ እና ለሀገር አለመረጋጋት ተጨማሪ ፈተና መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ ፓርቲያችን አብን ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ፣ አማራ እንደ ሕዝብ የተጋረጡባቸውን የኅልውና አደጋ ለመቀልበስ በጦር ግንባር ከሚደረገው ዝግጅት ጎን ለጎን ፣ የጸጥታ እና የደኅንነት ፈተናዎችን የደቀኑ ውስጣዊ ተግዳሮቶችን በጥንቃቄ እና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ መፍታት እንደሚያስፈልግ ያምናል፡፡

የአብን ሙሉ መግለጫ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ኅልውናዋ ላይ አደጋ የጋረጠ ጦርነት ላይ መሆኗ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችን እና ሕዝቦቿ በአጠቃላይ ፣ በተለይም የጥቃቱ ቀጥተኛ ተጋፋጭ የሆኑት የአማራ እና የአፋር ሕዝብ የሽብር ቡድኑ በመራው የትግራይ ወራሪ ኃይል ከደረሰባቸው ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ሳያጋግሙ ፣ ወራሪው ጦር ለሶስተኛ ዙር ጦርነት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የሽብር ቡድኑ መሪዎች በአደባባይ አውጀዋል፡፡ በዚህ ሀገራዊ አውድ ውስጥ ባለንበት ሰዓት ገዥው ፓርቲ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እና ክልሎች የሕግ ማስከበር ዘመቻ ላይ እንደሆነ አውጇል፡፡ መንግስት የሕግ ማስከበር ያለውን ዘመቻ በአማራ ክልልም እያከናወነ ይገኛል፡፡ ዘመቻው ከተለያዩ የኅብረተሠብ ክፍሎች ትችት እና ነቀፌታን እያስተናገደ የሚገኝ ሲሆን ፣ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በየደረጃው ያለውን መዋቅር በመጠቀም የመንግሥትን እርምጃ በንቃት ሲከታተል ቆይቷል፡፡

በመንግስት እየተወሰደ ያለው እርምጃ የሕጋዊነት ችግር ከዚህም ከዚያም የታየበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለበርካታ ትችት እና ቅሬታ መነሻ የሆነ ሲሆን ፣ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ክልሉን ለማተራመስ እና ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግበስበስ የቋመጡ ግለሰቦችን እና ቡድኖችንም እየተመለከትን እንገኛለን፡፡ አሸባሪው ትሕነግ ከሚመራው የትግራይ ወራሪ ጦር ጋር ሲደረግ በነበረው ጦርነት ወራሪውን ጦር “መንገድ ለቃችሁ ወደ አራት ኪሎ አሳልፉት” እያሉ ሲቀሰቅሱ የነበሩ እና ሕዝባችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት እንዲደርስ ድጋፍ ያደረጉ የሽብር ቡድኑ አፈቀላጤዎች ፣ ዛሬም ለአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው በመቅረብ አማራ ክልል ላይ “መሬት አንቀጥቅጥ አመጽ እና ሰልፍ” ጥሪ በማድረግ ለሶስተኛ ዙር ወረራ ዝግጅቱን ላጠናቀቀው የጠላት ወራሪ ኃይል ከውስጥ በር ለማስከፈት እና መንገድ ለመጥረግ ከጣራ በላይ እየጮሁ ይገኛሉ፡፡

በበርካታ የሀገራችን ኢትዮጵያ አካባቢዎች እየተከሰተ ያለው የጸጥታ መደፍረስ እና የሰላም እጦት በአማራ ክልልም ተደጋግሞ ተከስቷል፡፡ ክስተቶቹ የክልሉን ሕዝብ ማኅበራዊ እረፍት ነስተዋል ፤ የየአካባቢውን ሰላም ፣ ጸጥታ ፣ ንግድ ፣ ኢንቨስትመንት እና ማኅበራዊ መስተጋብር እየተፈታተኑ ሲሆን በመንግስት መዋቅር ውስጥ ካለው ብልሹ አሰራር እና አቅም ማጣት ጋር ተዳምሮ ክልሉን ለከፍተኛ የጸጥታ ስጋት ተጋላጭ አድርጎታል፡፡ ለክልሉ አለመረጋጋት እና የጸጥታ መደፍረስ በርካታ ምክንያቶችን መጥቀስ ቢቻልም ፣ አንዱ ምክንያት በገዥው ፓርቲ ውስጥ ያለው ክፍፍል እና የስልጣን ግብግብ ነው፡፡ በገዥው ፓርቲ ውስጥ የተፈጠረው ስንጥቅ የተለያዩ ሕገወጥ ቡድኖችን ከጀርባው በማሰለፍ እና ለሕገወጥ እንቅስቃሴዎች ሽፋን በመስጠት ክልሉ እንዳይረጋጋ እና ሕዝባችን የተደቀነበትን የኅልውና አደጋ በሙሉ ትኩረት እንዳይመክት ምክንያት ሆኗል፡፡

በተጨማሪም መቀመጫቸውን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ያደረጉና በጠላት የኃይል አሰላለፍ ውስጥ የገቡ በ “ጸረ-ብልጽግና-አቋም” ሽፋን ለአሸባሪው ትሕነግ ስልታዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ግለሰቦች እና ቡድኖች ለክልሉ አለመረጋጋት ተጨማሪ ምክንያት መሆናቸውን አብን ይረዳል፡፡ በአማራ ብሔርተኝነት ጭምብል ዲጅታል ወያኔ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚመራው የማወናበጃ ዘመቻም ለክልሉ እና ለሀገር አለመረጋጋት ተጨማሪ ፈተና መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ ፓርቲያችን አብን ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ፣ አማራ እንደ ሕዝብ የተጋረጡባቸውን የኅልውና አደጋ ለመቀልበስ በጦር ግንባር ከሚደረገው ዝግጅት ጎን ለጎን ፣ የጸጥታ እና የደኅንነት ፈተናዎችን የደቀኑ ውስጣዊ ተግዳሮቶችን በጥንቃቄ እና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ መፍታት እንደሚያስፈልግ ያምናል፡፡

አብን ለሕግ የበላይነት መከበር ቁርጠኝት ያለው እና በአማራ ክልልም ሆነ በመላው ሀገራችን ሕግ ለማስከበር የሚደረጉ ጥረቶችን የሚደገፍ ቢሆንም ፣ መንግስት በሕግ ማስከበር ዘመቻው እያከናወነ ያለው የእስር አካሄድ ላይ እየታዩ ያሉ ግድፈቶች አሳሳቢ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ ለብልሹ አሰራር እና ለዘፈቀደ ውሳኔ በተጋለጠው የክልሉ ሕግ ማስከበር ዘመቻ እስካሁን ድረስ ከአራት ሽህ የሚበልጡ የክልሉ ነዋሪዎች መታሰራቸውን የክልሉ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል፡፡ ከዘመቻው ጋር በተያያዘ ከገዥው ፓርቲ ጋር የፖለቲካ እና የሃሳብ ልዩነት ያላቸውን ወገኖች የማሳደድ እና መሰል ችግሮች እየተመለከትን እንገኛለን፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል የንቅናቄያችን አመራሮች እና አባላት ይገኙበታል፡፡

በመንግስት እየተወሰደ ያለው እርምጃ የሕጋዊነት ችግር ከዚህም ከዚያም የታየበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለበርካታ ትችት እና ቅሬታ መነሻ የሆነ ሲሆን ፣ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ክልሉን ለማተራመስ እና ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግበስበስ የቋመጡ ግለሰቦችን እና ቡድኖችንም እየተመለከትን እንገኛለን፡፡ አሸባሪው ትሕነግ ከሚመራው የትግራይ ወራሪ ጦር ጋር ሲደረግ በነበረው ጦርነት ወራሪውን ጦር “መንገድ ለቃችሁ ወደ አራት ኪሎ አሳልፉት” እያሉ ሲቀሰቅሱ የነበሩ እና ሕዝባችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት እንዲደርስ ድጋፍ ያደረጉ የሽብር ቡድኑ አፈቀላጤዎች ፣ ዛሬም ለአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው በመቅረብ አማራ ክልል ላይ “መሬት አንቀጥቅጥ አመጽ እና ሰልፍ” ጥሪ በማድረግ ለሶስተኛ ዙር ወረራ ዝግጅቱን ላጠናቀቀው የጠላት ወራሪ ኃይል ከውስጥ በር ለማስከፈት እና መንገድ ለመጥረግ ከጣራ በላይ እየጮሁ ይገኛሉ፡፡

ፓርቲያችን አብን በመንግስት እየተወሰደ ያለው እስር ላይ እየታሉ ያሉ ግድፈቶች እያሳሰበው ያለውን ያክል ፤ ዲጅታል ወያኔ ፣ ኢትዮ 360 እየተባለ የሚጠራው ሚዲያና መሰል የአሸባሪው ትሕነግ ተከፋይ ሚዲያዎች አጋጣሚውን ተጠቅመው ክልሉን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ እያደረጉት ያለው ሰፊ እና የተቀናጀ ዘመቻ ያሳስበዋል፡፡ በመሆኑም፦

  1. የሕግ የበላይነትን እና ሥርአትን ሕግን እየሸራረፉ እና መብቶችን እየጣሱ ማረገገጥ የማይቻል በመሆኑ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እያከናወነ ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ በሕግ አግባብ ብቻ እንዲያከናውን እያሳሰብን ፣ ክልሉ እያከናወናቸው ያሉት የጅምላ እስር ለብልሹ አሰራር እና ለዘፈቀደ ውሳኔ ተጋላጭ በመሆናቸው በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
  2. የክልሉ መንግሥት እየወሰደ ባለው እርምጃ የአብን አመራሮችን እና አባላትን ጨምሮ ባላቸው የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ምክንያት በግለሰቦች ላይ እየተፈጸመ ያለው እስር እንዲቆም እና በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት የታሰሩ ሰዎች ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
  3. የክልሉ መንግስት እየወሰደው ባለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ሂደት እየታዩ ያሉ ግልፅ ችግሮችን ሰበብ በማድረግ የአማራን ክልል የግጭት ማዕከል ለማድረግ እየሰሩ ያሉ ግለሰቦች እና ቡድኖችን አብን በጽኑ የሚያወግዝ ሲሆን ፣ ጠላት ጦርነት ለመክፈት በተዘጋጀበት ወቅት የአመጽ ጥሪ ማድረግ ያለንበትን አጠቃላይ የጸጥታ ከባቢያዊ ሁኔታ የዘነጋ እና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ከመሆኑም በላይ ለጠላት የሚደረግ ስልታዊ ድጋፍ በመሆኑ የአመጽ ጥሪ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳስባል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)

አዲስ አበባ ፣ ሸዋ ፣ ኢትዮጵያ

Exit mobile version