Site icon ETHIO12.COM

ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋል

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ፕሬስ ሴክሬታሪ የሆኑት ቢልለኔ ስዩም ታይም መጽሔትን የአንድ ወገን ትርክትን በማትመ አደገኛ ስም የማጠልሸት ተግባር መፈጸሙን ጠሰው ማብራሪያ ጠይቀዋል።

ከዓለም መቶ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን አንዱ አድርጎ የመረጠው ትይም መጽሔት ከምርጫው ጎን ያተተው ሃተታ ላለፉት ሁለት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ሲካሄድ የነነረውን የተቀናጀ የማተልሸት ዘመቻ ጨምቆ በድጋሚ ያቀረበ መሆኑን በርካቶች መስክረዋል።

አንዳንዶች በይፋ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በማወደስ የታይም ሚዛን የሳተ ስም ማጠልሸት ተቃውመዋል። የዓለምን ሚዲያዎች፣ ታላላቅ የሚባሉ አገሮች፣ መሪዎችና ታዋቂ ተቋማትና የትባበሩት መንግስታት ህብረት ፈጥረው፣ ኢትዮጵያ ላይ ዘምተው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ አነጣጥረው ዘመቻ ከፍተው ነበር። ከዘመቻው ጎን ለጎንም አገር ለቀው እንዲወጡ ግፊት ሲደረግ እንደነበር ባለስልጣናት አስታውቀውም ነበር።

ከዚህ ሁሉ ዘመቻ በሁዋላ አዲስ አበባ በአማጽያን ቁጥጥር ስር እንደምትሆን እየተገለጸ ዲፕሎማቶች አገር ለቀው መውጣት በጀመሩበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሯቸውን ጥለው ወደ ጦር ሜዳ በመግባት ተዋግተው በማዋጋት ድል ማስመዝገባቸውን ለሚያከብር ሕዝብ ይህ ሃሜት ትርጉም እንደሌለው ተገልጿል።

በዚህ መነሻ ይመስላል ቢለኔ የቅሬታ ደብዳቤ የላኩት። መጽሔቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የ2022 የዓመቱ 100 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ አድርጎ ሲመርጥ፣ አብይ አሕመድ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም በማውረዳቸው የኖቤል ሽልማት መቀበላቸውን አስታውሷል። አያይዞም በትግራይ ጦርነት የተሳተፉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠያቂ አድርጓቸዋል። የአንድ አገር መከላከያ በክህደት ሲታረድ መንግስት ዝም ማለት እንዳለበት ግን አልተገለጸም።

የመጽሄቱ ወኪል አሪያን ቤከር፤ “የዐቢይ ኃይሎች በጅምላ ግድያዎች፣ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችና የዘር ማጽዳት ክስ ቀርቦባቸዋል” ስትል ቀደም ሲል በዘመቻ ሲደረግ የነበረውን የሚዲያ ዘመቻ ጠቅለል አድርጋ አቅርባለች።ታዲያ ቢልለኔ ስዩም “እንዴት ሆኖ” ሲሉ ለታይም መጽሔት በጻፉት የኢሜይል አቤቱታ ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈው “ሆን ተብሎ ስም ለማጥፋት ታስቦበት የተሰራ” ነው ማለታቸውን አቤቱታቸውን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።

መጽሄቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ግላዊ ማንነት ላይ ያነጣጣረ ወንጀል መፈጸሙን ያመለከቱት ቢለኔ፣ “ከፍተኛ” ሲሉ ወንጀሉን አውግዘዋል። ከዚህም በላይ ታይም መጽሄት ስለጦርነቱ በአንድ ወገን ብቻ የሚነገረውን ትርክት የሚያስተጋባ መሆኑንን ጠቅሰው ሙያዊ ክብር የጎደለው እንደሆነ ጠቁመዋል። መጽሄቱ ዕውነቱን ወደሁዋላ ገፍቶ የራሱን ትርክት በመላው ዓለም ማሰራጨት ለምን እንደፈለገ ማብራሪያ እንዲሰጥ ቢልለኔ በደብዳቤያቸው አጉልተው ጠይቀዋል።

የታይም መጽሔት የአፍሪካ ቢሮ ኃላፊ ቤከር ከወራት በፊት በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ሲባል የፌደራሉ መንግሥት የወሰደውን የተኩስ የተናተል የተኩስ አቁም ስምምነት በአመዛኙ ስትራቴጂካዊ ከመሆኑ ባሻገር የደረሰው የእርዳታ መጠን አነስተኛ እንደሆነም ጠቁማለች። እሷ ይህን ብትልም የተባበሩት መንግስታትና የምግብ ድርጅት ሃላፊዎች ከፍተኛ መተን ያለው እርዳታ መግባቱን ጠቅሰው መንግስት አመስግነዋል። ቤከር ትህነግ እየወሰደ ስላማይመልሳቸው ከባድ ተሽከርካሪዎችና አፋርና አማራ ክልል ላይ አሁን ድረስ ወሮ ስለያዛቸው፣ ቀደም ሲልም በስፋት ወረራ በፈጸመበት ወቅት የፈጸመውን ወንጀል፣ ዝርፊያ፣ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ የጅማላ ጭፍጨፋ በማመልከት ትህነግን አላኮነነችም። ቢለኔ የአንድ ወገን ሲሉ የኮነኑት ይህንኑ ነው።

Exit mobile version