አቢይ አሕመድ ብራሰልስ ገቡ፤ ከአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የልዑካን ቡድናቸው ስድስተኛውን የአውሮፓ ኅብረት እና የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች የጋራ ጉባኤ ለመሳተፍ በቤልጂየም ብራሰልስ መግባታቸውን ቢሯቸው ይፋ አድርጓል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ በርካታ ጉዳዮችን እንደሚቀይር ይጠበቃል።

ትህነግ በድንገት የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው የክህደት ጥቃት ሳቢያ የተጀመረውን የህግ ማስከበር ዘመቻ አሜሪካ መልኩን ካስቀየረችው በሁዋላ ከተወሰኑ አገራት በቀር የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ ላይ የተጣመመ አቋም ሲከተለ መቆየቱ ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጉባኤው ተሳትፏቸው ጎን ለጎን ከአውሮፓና ከዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ጋር ስብሰባዎችን እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አመልክቷል።

ኢትዮጵያ ላይ ሲደረግ የነበረውን ቅጥ ያጣና ዓላማው በግልጽ የማይታወቅ ዘመቻ በግል ከሚደረግ ግንኙነት በቀር አብይ አሕመድ እንዲህ ባለው መድረክ ሳይገኙ ከመቆየታቸው አንጻር የብራስልስ ጉዟቸው ትልቅ ትርጉም እንዳለው ተመልክቷል።

ከወር በፊት የህብረቱ የህዝብ ግንኙነት ከኢትዮ 12 ኢትዮጵያ ላይ ስላላቸው የተጣመመ አመለካከት ማብራሪያ እንዲሰጡና ለወደፊት ምን እንደሚያስቡ ተጠይቀው፣ ከአፍሪካ ጋር በአጋርነት መስራት የአውሮፓ ህብረት ቅድሚያ ተግባር መሆኑን በመጥቀስ ሲመልስ ለዚህም ኢትዮጵያ የአጋርነቱ መካከል እምብርት እንደሆነች “The partnership with Africa is a priority of the European Commission, and Ethiopia has always been central to this partnership.” የዩኒቱ መሪ ዲዲየር ቨርስ በኢሜል አስታውቀው ነበር።

አብይ አሕመድ ከዩታ ጋር ሲወያዩ ፊት ለፊት ከተነሳ ፎቶ የተወሰደ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከብራስልስ ” ከዩታ ኧርፒላይነን ጋር ተገናኝተን ኢትዮጵያ ለዕድገቷ የምታደርጋቸውን ጥረቶች በተመለከተ ተወያይተናል። አጋርነታችንን ለማጠናከር በሚያስችሉን አካሄዶችም ላይ መክረናል” ሲሉ በጽህፈት ቤታቸው ገጽ ላይ ለህዝብ መረጃ አቀብለዋል። ዩታ የአውሮፓ ዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ሲሆኑ የፊንላንድ ዝርያ አላቸው። የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይዘውት ከነበረው አቋምና ” መንግስት ነግሮኛል” ሲሉ ሕዝብን የማጥፋት እቅድ ስለመኖሩ በሃሰት ከመሰከሩት ወገን ከመሆናቸው አንጻር ውይይቱ አስፈላጊ እንደሆነ በርካቶች ያምናሉ።

የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ መካሄድ፣ የአስቸኳይ አዋጅ መነሳት፣ ላረጁ ወንጀለኞች የተገደበ ምህረት መስጠት፣ ለአገራዊ እርቅ ዝግጅት በሙሉ ልብ መነሳትና የሰሜኑንን ፖለቲካ ቀይሮ ከአውሮፓ ህብረት መሪዎች ጋር በተናጠልና በጋር መምከር ሲደረግ የነበረውን ዘመቻ ለሚያስታውሱና አሁን ድረጅ የሚሰራዉን ሴራ ለሚረዱ ታላቅ የዲፕሎማሲ ማገገሚያ መደላድል ነው።

ከውይይቱና ከስብሰባዎቹ ማብቂያ የሚላሉ ጉዳዮች ስለመኖራቸው በርካታ ግምቶች እየተሰሙ ነው።


Related posts:

«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ

Leave a Reply