Site icon ETHIO12.COM

አገር መከላከያ “የጥቁር አንበሳ” ካዴቶችን አስመረቀ፤ ” በቁጭት እየገነባን ነው”

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ለ69ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን “የጥቁር አንበሳ” ዕጩ መኮንኖችን አስመረቀ። ተመራቂዎቹ “የጥቁር አንበሳ” መባላቸው በምዕራባዊያንና በውስጡ ነበሩ በተባሉ “ካሃዲዎች” የተበተነውን ታልቁን የኢትዮጵያ መከላከያ ያስታወሰ መሆኑ ልዩ ስሜት የሚሰጥ እንደሆነ ምርቃቱን ተከትሎ አስተያየት ተሰጥቷል።

የ69ኛ ተመራቂ መኮንኖች አብዛኞቹ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩበት ስራቸውን አቁመው በራሳቸው ተነሳሽነት እናት ሀገር ጥሪን ተቀብለው ሰራዊቱን የተቀላቀሉ ናቸው።

“ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም በሚል ቁጭት ነው ኢትዮጵያን የሚመጥን የመከላከያ ኃይል ለመገንባት እየሰራን ያለነው” በማለት የጦር ኃይሎች ም/ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ በተናገሩ ማግስት፣ አዳዲ መኮኖች መመረቃቸው፣ ጀነራሉ በንግግራቸው የሚገነባው ኢትዮጵያን የሚመስልና የሚመጥን ሰራዊት ዘመናዊና ቲክኖሎጂን የተላበሰ፣ በምሁራን የተገነባ እንደሚሆን ካመላከቱት ጋር ተያያዥ ሆኗል። ተመራቂዎቹ የመጀመሪያና ሁለተና ዲግሪ ያላቸው፣ በራሳቸው ተነሳሽነት ከሲቪል የስራ መስካቸው ወደ ውትድርና ያመሩ ተተኪ መኮንኖች መሆናቸው ታውቋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ኢትዮጵያዊ ጀግንነት፣ከሀገር ፍቅርና ከህገመንግስቱ የሚቀዳ አላማና ሁለገብ እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ የጠቀሱት ደግሞ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ ናቸው። ይህንንም ያሉት በምረቃው ስነስርዓት ላይ ነው።

በተከታታይ በወታደራዊ ሳይንስና ትምህርት የሰለተኑ፣ በሚካናይዝድና መኢንተለጀንስ የተሰሩ አዳዲስና ወጣት ሙያተኞችን እያካተተ ያለው የመከላከያ ሰራዊት ውጊያን በትንሽ ኪሳራ፣ በአጭር ጊዜ ማተናቀቅ እንዲችል ተደርጎ እየተሰራ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገልጽ እንደነበር ይታወሳል።

በ1983 የኢትዮጵያ መከላከያ ” የደርግ ሰራዊት” ተብሎ እንደተበተነው ሁሉ በቅርቡ ትህነግ አማራና አፋር ክልልን ወሮ በነበረበት ወቅት ” እጃችሁን ለትግራይ ሃይልን ስጡ” በሚል ጥሪ ሲቀርብለት የነበረና ወረራውን በአጭር ጊዜ ራሱን አደራጅቶ የቀለበሰና ልምድ ያካበተ እንደሆነ ከፍተኛ መኮንኖች ሲያስታውቁ ቆይተዋል። በወቅቱ የትህነግ አመራሮች ይህ በአዲስ እየተደራጀ ያለውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት “የአብይ ሰራዊት” በማለት ዳግም እንደሚያፈርሱት ሲዝቱ እንደነበር ይታወሳል።

የምረቃውን ስነ ስርዓት አስመልክቶ በታተሙ ምስሎች ለመረዳት እንደተቻለው የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ የነበሩትና የኅብረትሰባዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች ጀግና አንደኛ ደረጃ ኒሻን የተሸለሙት ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ሃብተማርያምና ሌሎች እውቅ የቀድሞ በለኮከብ መኮንኖች በስነስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ዛሬ የመንግስት መገናኛዎች እንዳሉት የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ 69ኛ ዙር የጥቁር አንበሳ ኮርስ የሲቪል ወታደራዊ መኮንኖችን በምክትል መቶ አለቃ ማዕረግ ዛሬ አስመርቋል። በመርሀ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ፣የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልእክት የሀገር መከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ኢትዮጵያዊ ጀግንነት፣ከሀገር ፍቅርና ከህገመንግስቱ የሚቀዳ አላማና ሁለገብ እውቀት ሊኖራችሁ ይገባል ብለዋል።

የነገ የሀገር ኩራት ጀነራሎችና ሀገር መሪዎች መሆናችሁን በቅጡ በመረዳት ለአላማችሁ የምትታትሩ፣የምትተጉና ከቀድሞ የጦር መሪዎች ተምራችሁ የምትሰሩና የምታሰሩ መሆን ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፤ የዛሬ ተመራቂዎች የተሰጣቸውን ስልጠና በብቃት በመወጣት የመከላከያ ሰራዊት አባል መሆን የቻሉ መኮንኖች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ በገባችበት ወቅት ሀገራቸውን አስቀድመው በአስቸጋሪና ውስብስብ ስልጠና ተፈትነው ያለፉና ለምረቃ የበቁ መኮንኖች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

የ69ኛ ተመራቂ መኮንኖች አብዛኞቹ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩበት ስራቸውን አቁመው በራሳቸው ተነሳሽነት እናት ሀገር ጥሪን ተቀብለው ሰራዊቱን የተቀላቀሉ ናቸው።

Exit mobile version