ማስታወሻ
የቀይ ባህር ኢኒሼቲቭ በአውሮፓ ህብረት ሙሉ በሙሉ የሚደገፍ፣ 6.1 ሚልዮን ዩሮ በጀት ያለው፣ በቀይ ባህር የባህር ላይ ደህንነት መርሃ ግብር ነድፎ ወደ ስራ መግባቱን የፕሮጀክቱ ድረ ገጽ ያስረዳል። ኢትዮጵያ በትህነግ ውሳኔና አቀነባባሪነት የአሰብ መብቷንና የቀይ ባህር ድርሻዋን እንድታጣ፣ የባህር ሃይሏ እንዲፈርስ ከተደረገ ሃያ ስምንት ዓመት በሁዋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ሃላፊነት ሲመጡ ባህር ሃይል በድጋሚ መደራጀቱና ዘመናዊ የጦር መርከብ ግዢና ተመሳሳይ ስምምነቶችን ከፈረንሳይ ጋር ማደርጓ ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባህር ለሌላት አገር ባህር ሃይል ማዋቀራቸውና ዘመናዊ የጦር መርከብ ባለቤት ለመሆን ከፈረንሳይ ጋር ያደረጉት ስምምነት ዓለም ጭልጥ ብሎ የትህነግ ደጋፊ ሲሆን ተስተጓጉሎ እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይ ባሉ መረጃዎች ፈረንሳይ አቋሟን እየቀየረችና ድጋፏን ዳግም እያደሰች በመሆኑ የባህር ሃይል ነክ ስምምነቶቹ ወደ ተገባር እንደሚቀየሩ ይጠበቃል። ከሩሲያም ጋር ይፋ ያልሆኑ ስምምነቶች መፈጸማቸው አይዘነጋም።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በአለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም (INTRPOL) አስተባባሪነት በምስራቅ አፍሪካ በባህር ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል።
በምስራቅ አፍሪካ በባህር ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ የሬድ ሲ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክት (Red Sea Initiative) ኃላፊዎች ስለፕሮጀክቱ አጠቃላይ ሁኔታ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በውይይቱ ለቀጠናው ብሎም ለአለም ስጋት የሆኑ የወንጀል አይነቶችን ለመግታትና በትብብር ለመስራት ፕሮጀክቱ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያና የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀሎችን ለመግታት ትላልቅ ስራዎችን እንደሰራችም በማንሳት በምስራቅ አፍሪካ ትልቁን ኢኮኖሚ እንደምታንቀሳቅስና በ2015 ዓ.ም የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረትን (EAPCCO) በሊቀ-መንበርነት በመረከብ የቀጠናው ሀገሮችን በማሳተፍ ወንጀሉን በጋራ ለመከላከል ሚናዋን እንደምትወጣ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በሽብርተኝነት፣ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲሁም የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመከላከል ሰፊ ተሞክሮ ያላት በመሆኗ ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ያላትን ትልቅ ልምድ ለቀጠናው ብሎም ለአፍሪካ ታካፍላለች ሲሉ ለፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡
ሕገ ወጥ የሰዎችና የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን እንዲሁም የተሰረቁና የጠፉ ሰነዶችን የመከላከል ዓላማ አድርጎ ለአምስት ዓመታት የሚቆየው ይህ ፕሮጀክት በአለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም (INTRPOL) አስተባባሪነት በአለም አቀፍ Martime ድርጅት (IMO)፣ በአውሮፓ ህብረት (EU) እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት መድሀኒትና ወንጀል ቁጥጥር (UNODC) በጋራ ይሰራል። በአፍሪካ ኢትየጵያን፣ ጂቡቲን፣ ሶማሊያን፣ ሱዳንን፣ የመንንና እና ኤርትራን በአባልነት ያቀፈ ነው፡፡
የአቅም ግንባት፣ የሎጀስቲክስ ድጋፍ ለማድረግ እንዲሁም ኦፕሬሽን ለማከናወን የኢትዮጵያ ሞጆ ደረቅ ወደብ ጣቢያ ፣የሶማሊያ ቦሳሳ ወደብ፣የሱዳን ፖርት ሱዳን፣የየመን ኤደን ፖርት እንዲሁም የጅቡቲ ጅቡቲ ኢንተርናሽናል ፖርት የተመረጡ መሆኑ በውይይቱ ተገልጿል ፡፡
በፕሮጀክቱ ፕሮግራም መሰረት ስልጠናው በሚቀጥሉት ቀናት በኢትዮጵያ ሞጆ ደረቅ ወደብ ጣቢያ ላይ እንደሚጀመር ኃላፊዎች መገለጹን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መረጃ ያሳያል ሲል የዘገበው ኢፒድ ነው።
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media briefing regarding the country’s diplomatic activities over the week, Spokesperson of the Ministry Nebiyu Tedla, indicated that Ethiopian delegation led by State Minister of Foreign Affairs Ambassador Mesganu Arga participated in the consultation… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its statement, the Council underscored the need to mend the deep-seated national fractures through an inclusive approach. According to the council, three problem-solving mechanisms are put in place so as to address the existing and new political challenges resulted… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the people of Somaliland in a democratic constitutional referendum. The Government of the Republic of Somaliland’s Statement Regarding the G7 Communique First and foremost, the Government and the people of the Republic of Somaliland are deeply offended by the… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”