ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ ያልተፈቀዱ መሳሪያዎች ወደ ትግራይ ለማጓጓዝ የሞከሩ እዳታ ሰጪ ተቋማትን አወገዘች

በአፋር ሰርዶ በተተከለው ኬላ የእርዳታ ድርጅቶች ያልተፈቀደ መሳሪያ ለማስተላለፍ ሲሞክሩ መያዙን የአፋር የመረጃ ምንጮ ለዘግጅት ክፍላችን አመልክተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን “በሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት በሚል ሰበብ ለወራሪው ሃይል የጥፋት ዓላማ የሚውሉ መሳሪያዎች እንዳይገቡ ከፍተኛ የቁጥጥር እና የፍተሻ ስራዎች ይጠናከራሉ” ሲሉ በደፈናው መናገራቸው ተሰምቷል።

ኤፒ እሳቸውን ጠቅሶ “ኢትዮጵያ ያልተፈቀዱ መሳሪያዎችን ወደ ትግራይ ለማጓጓዝ የሞከሩ እዳታ ሰጪ ተቋማትን አወገዘች” ሲል ዘግቧል። ይሁን እንጂ አቶ ደመቀ ዝርዝር አላብራሩም።

ምን አይነት መሳሪያ ሲተላለፍ እንደነበር በግልጽ ሳያስታውቁ በደፈናው ያስታወቁት ሚኒስትሩ ጥበቃው እንደሚተናከር መናገራቸውን ተከትሎ ነው የመረጃው ምንጮች በተደጋጋሚ ተገጣጣሚ መሳሪያ ሊተላለፍ ሲል የተያዘው። የተያዙትም መሳሪያዎች በተለያዩ ዙሮች እንዳያስታውቁ ባምድረግ በአነስተኛ መተን ለመላክ ሲሞከር መያዙን አመልክተዋል።


Ethiopia accuses aid agencies of delivering banned equipment to Tigray

“I have noticed there are efforts to transport more fuel than allowed and some banned equipment that can be used to carry out the terror group’s aims,”


በከፍተኛ የውጭ መንግስትታ ጫና ውስጥ ያለው መንግስት ኬላውን ማጠናከሩና ፍተሻውን ለማጠናከር ከመጀመሪያ ጀመሮ የያዘውን አቋም የሚደግፉ በተወሰነ ደረጃ የሾለከ ሊኖር እንደሚችል ስጋት አላቸው። በተለይም አየር መቃወሚያ ለማግኘት በከፍተኛ ደረጃ የትህነግ ሰዎች ሲወተውቱ እንደነበር ይታወሳል።

Demeke Mekonnen Hassen  በፌስ ቡክ ገጻቸው ያሰራጩት ጽሁፍ የሚከተለው ነው

በዛሬው ውሎ ወደ አፋር ክልል በማቅናት ከፌዴራል እና ከክልሉ መንግስት የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን በሰመራ እና በሰርዶ ኬላ የመስክ ምልከታ አድርገናል።

እንዲሁም ከተለያዩ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰጪ ድርጅት ተዎካዮች ጋር በሁለንተናዊ ድጋፍ አሰጣጥ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አካሄደናል።

በተጨማሪ በሰርዶ ኬላ ወደ ትግራይ ክልል የሚሄደውን የሰብአዊ ድጋፍ ስርዓትና ሁለገብ እንቅስቃሴ ጎብኝተናል።


The Most Vulnerable Countries Amid Wheat Shortages. Ethiopia is not included

Ukraine and Russia are also among the world’s top exporters for other important food staples. Around two thirds of the global exports of crucial sunflower products like oil and feed come from Ukraine and Russia.


እንደሚታወቀው የአፋር አናብስት በከሃዲው ሃይል የተቃጣበትን ጥቃት ከጎረቤት የአማራ ህዝብ፣ ከመከላከያ ሰራዊት እና ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ለመመከት ያደረገው ርብርብ እና ያስመዘገበው ታሪካዊ ድል እጅግ የሚያኮራ ነው።

የአፋር ህዝብ በወራሪው ሃይል በተሰነዘረበት ጥቃት ራሱ እየተፈናቀለ፣ ራሱ እየቆሰለ እና ራሱ እየሞተ ለትግራይ ወገኖቹ ሰብዓዊ ዕርዳታ ተደራሽ እንዲሆን እያደረገ ያለው ድጋፍ እና ትብብር በእጅጉ የሚያስመሰግን ነው።

የአማራ ክልል ህዝብ ለትግራይ ተፈናቃዮች አቀባበል እና ድጋፍ እንዳደረገ ሁሉ፤ የአፋር ክልል ህዝብም በግጭቱ ሰለባ እየሆነ፤ ለወገኖቹ ቅድሚያ በመስጠት ዕርዳታ ወደ ትግራይ እንዲገባ ያደረገው ትብብር እና ድጋፍ በአዎንታ የሚወሰድ ትክክለኛ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ መገለጫ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።



ወራሪው ሃይል በፈጠረው ግጭት ባስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ እና በድርቅ ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች በደረሰው ጉዳት በሃገሪቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ይሻሉ።

በሁሉም አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ፈጣን ምላሽ የመስጠት እና በዘላቂነት የማቋቋም ስራዎች በትኩረት በመከናወን ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው የመስክ ምልከታ ለአፋር ክልል ተፈናቃዮችን የሰብዓዊ ዕርዳታ ተደራሽ የማድረግ ርብርብ እንዲሁም በሰርዶ በኩል ወደ ትግራይ የሚላከው እርዳታ እየተሳለጠ መሆኑን ተመልክተናል።

በአሁን ጊዜ በአማራ፣ በትግራይ እና አፋር ክልል ለሚገኙ ተረጂዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊረባረቡ ይገባል።

በሰርዶ በኩል ወደ ትግራይ ክልል የሚላኩ ሰብአዊ ዕርዳታዎች ለትግራይ ተረጂ ወገኖች ተደራሽ መሆናቸውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰጪ አካላት የመከታተል እና የማረጋገጥ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።

በተያያዘ በሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት በሚል ሰበብ ለወራሪው ሃይል የጥፋት ዓላማ የሚውሉ መሳሪያዎች እንዳይገቡ ከፍተኛ የቁጥጥር እና የፍተሻ ስራዎች ይጠናከራሉ።

በአጠቃላይ በመላው ሃገሪቱ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ የተፈናቀሉ ወገኖችን በዕለት ደራሽ ድጋፍ እና በዘላቂነት መልሶ የማቋቋም እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ይቀጥላል

Exit mobile version