Site icon ETHIO12.COM

ከ85 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባዕድ ጋር ቀላቅሎ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ ማደያ ታሸገ

በጌዴኦ ዞን በወናጎ ከተማ ከ85 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባዕድ ጋር ቀላቅሎ ለህብረተሰቡ ስሸጥ የነበረን ማደያ ማሸጉን የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል ።

የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያው እንዳስታወቀው ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በወናጎ ከተማ ከ85 ሺህ ሊትር በላይ ባዕድ ቀላቅሎ ለህዝቡ ሲሸጥ የነበረ ማደያ እንደነበር ደርሼበታለሁ ብሏል ።

የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ምስጋና በራሶ እንዳስታወቁት መንግስት የህዝብን ፍላጎት ለሟሟላት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የነዳጅ አቅርቦት ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል ።

ህገ ወጥ ንግድ ለመከላከል በትኩረት እየሰራ የሚገኘው የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ከወናጎ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ከህዝቡ ባገኘነው ጥቆማ መሠረት ለህብረተሰቡ ከባዕድ ተቀላቅሎ ሲሸጥ የነበረ ነዳጅ የማጣራት ስራ ለማጠናከር ባደረገው ጥልቅ ክትትል ቤንዚኑ የጥራት ጉድለት እንደነበረ ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለማጣራት ችሏል ።

የወናጎ ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስንታየሁ ጎሎ በከተማ እየተበራከተ የመጣውን ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴና ከደረጃዎች በታች የሚመጡ ምርቶችን የመቆጣጠር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል ።

በዚህም መሠረት ከ85 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባዕድ ጋር ቀላቅሎ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረው ማደያ ላይ ጥልቅ ክትትል በማድረግ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

ህገ-ወጥ ተግባራትንና መሰል ችግሮች ለመቅረፍ ከተማ አስተዳደሩ ከዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ጋር በጋራ በመሆን የክትትል ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥል አቶ ስንታየሁ ገልጸዋል ።

(ኢ.ፕ.ድ)

Exit mobile version