Site icon ETHIO12.COM

የፓርላማ አባላት ያለመከሰስ መብት የሚነሳበት አዲስ ድንብ እየተዘጋጀ ነው

በፓርላማ አባልነት ከለላ ህግና ስርዓት የሚጥሱ የፓርላማ አባላትን በአፋጣኝ ወደ ህግ ለማቅረብ የሚያስችል አዲስ መመሪያ ተዘጋጅቶ በስራ ላይ ሊውል በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ።

በተከታታይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነታቸውን በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝብን የሚያውኩ፣ አጀንዳ የሚሰፍሩ፣ በኮድ ጥሪ የሚያቀርቡና ለዓመጽ የሚገፋፋ መረጃ የሚያራቡትን ለማረቅ ታስቦ የተዘጋጀው ህግ ሚስጢር ማባከንና፣ የአገርን ገበና አሳልፎ መስጠትንና ማናቸውንም በህግ የተከለከሉ ጉዳዮችን በሚፈጽሙ የፓርላማ አባላት ላይ ክስ መመስረትና ተጠያቂ ማድርግ የሚያስችል እንደሆነ ለአሰራሩ ቅርብ የሆኑ አመልክተዋል።

የተወካዮች ምክር ቤት የህግ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አለመከሰስን በመጠቀም የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመግታት አዲስ መመሪያ አዘጋጅቶ ቢጨርስም ዜናውን ያጋሩን ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም።

የፓርላማ አባላትን በህግ ለመጠየቅ ያለመከሰስ መብትን ለማንሳት የሚወስደውን ጊዜ፣ እንዲሁም መብቱ ተንቦርቅቆ ህግን ለመጣስ የሚሰጠውን ክፍተት እንደሚሞላ የተነገረለት አዲሱ ህግ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆንና ትክክለኛውን አግባብ ተከትሎ እንደሚጸድቅ ለማወቅ ተችሏል።

Exit mobile version