Site icon ETHIO12.COM

መከላከያ ሱዳንን ለማስተንፈስ ዝግጁ ሆኖ የመንግስትን ትዕዛዝ እየጠበቀ መሆኑንን አስታወቀ


ከፍተኛ መኮነኑ ድርጊቱን በማስመልከት በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ከሱዳን ህዝብ እና መንግሥት ጋር ያላት መልካም ግንኙነት ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ከመሆኑም ባሻገር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ታሪካዊ በሆነው የሱዳን የአብዬ የሰላም ማስከበር ተልእኮ በሡዳንና በደቡብ ሡዳን ሀገሮች የተመረጠ በመሆኑ በአለም የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ታማኝነቱ ይበልጥ ጎልቶ እንድታይ አድርጎታል።
ይሁን እንጅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሱዳን መንግሥት ከሽበርተኛው የህወሀት ቡድን ጋር በተናበበ መልኩ የሱዳን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው እስከ መውረር የዘለቀ የሁለቱን ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት የማይመጥን ተግባር ከመፈፀሙ በላይ ፀብ አጫሪ መግለጫ ሰጥቷል።
ዛሬም ድረስ የሱዳን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በመግባት ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ቢሆኑም በቀጠናው ለደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን የመከላከያ ሰራዊታችን ግዳጁን በህግና በደንብ የሚወጣ ጀግና መሆኑ እየታወቀ የሠራዊቱን ስም በሀሠት የሚያጠለሹ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል።
በሠራዊታችን ላይ የሚነዛ የሀሠት ፕሮፖጋንዳን በማስመልከት እውነቱን ለማወቅ አጣራለሁ ለሚል ማንኛውም አካል በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።
በተጨማሪም መንግስታችን ከሱዳን ጋር ያለውን የቀጠና ውጥረት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት እያደነቅን ሰራዊታችን አሁንም ቢሆን ትእዛዝ ከተሰጠው እንደ ሽፍታ ሳይሆን በመደበኛ ውጊያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስወጣት በሙሉ ቁመና ላይ ይገኛል ። ከአገር መከላከያ ገጽ ቃል በቃል የተወሰደ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንደ ሽፍታ ሳይሆን በግልጽ በፕሮፌሽናል መንገድ የሱዳንን እብሪት በማስተንፈስ በሃይል የያዙትን መሬት ለማስመለስ የመንግስትን መመሪያ በመጠባበቅ ላይ ነው፣ የሚሰጠውንም መመሪያ ለመፈጸም በሙሉ ዝግጅት ላይ መሆኑንን ይፋ አድርጓል። መከላከያ ሲታዘዝ የሚፈጽመው የሱዳንን መንግስት አሳስተው የሚገፉት ሃይሎች ለሰላም የተዘረጋውን የኢትዮጵያን እጅ አልቀበልም ብሎ ሲገፋበት ነው።

የቀድመውን ዘመን ያስቆጠረ የሁለቱን አገራት ግንኙነት በማይመጥን መልኩ የሱዳን መንግስት ተደጋጋሚ ትንኮሳ ሲያካሂድ እንደቆየ ያመለከቱት የኢፌዴሪ አገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ዛሬ ላይ ግን ትንኮሳን መታገስ እንደማይቻል አምለክተዋል። ማስጠንቀቂያም አቅርበዋል።

ለሰላምና ለቆየ ዘመን ተሻጋሪ ወዳጅነት ኢትዮጵያ ዋጋ እንደምትሰጥ ያመለከቱት ኮሎኔሉ ሱዳን ከሚገፏት አካላት ፍላጎት ነጻ በመሆን ሳይመሽ እንድታስበበት አመልክተዋል። አያይዘውም ይህ ሳይሆን ቀርቶ እንደቀድሞ አይነት ትንኮሳ የሚሞከር ከሆነ ሱዳንን የማያዳግም ምላሽ ሊሰጥ የመከላከያ ሰራዊት በቂ ቁመና ላይ ሆኖ በመጠባበቅ ላይ መሆኑንን አስታውቀዋል።

” የሱዳን ጦር የሚነዛው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ” የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ዛሬ አስታውቋል። መከላከያ ይህን ያስታውቀው ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው የገቡ ወታደሮቿ በአካባቢው ሚሊሻ ከተገደሉ በሁዋላ ነው።

በግብጽ መሪ አልሲሲ የሃዘን መግለጫ የተላከላት ሱዳን ኢትዮጵያን ከሳ ለተባበሩት መንግስታት እንደምታሳውቅ እየገለጸችበት ባለበት ሰዓት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሞቱት የሱዳን ወታደሮች ማዘኑንን ገልጾ ጉዳዩን እንደሚያጣራ አስታውቋል። አያይዞም ድንበር ጥሶ የገባው የሱዳን ሃይል አስመልክቶ ሱዳን ያቀረበችው ሮሮ ተቀባይነት እንደሌለው አመልክቶ ከጦርነት ነጋሪት ጉሰማ እንድትታቀብ አሳስቧል።

“የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምርኮኞችን አያያዝ ባልጠበቀ መንገድ ወታደሮቼን ገድሏል” በሚል የሱዳን ጦር የሚነዛው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ያስታውቀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ተከትሎ ነው። የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በቦታው እንዳልነበርና የኢትዮጵያን ግዛት ዘልቆ የገባው የሱዳን ኃይል ከአካባቢው ሚሊሻዎች ጋር መጋጨቱ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

የመከላከያ ሚኒስቴር ትህነግ በሰሜን ዕዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት በፈፀመበት ወቅት የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ወረራ መፈጸሙን አስታውሶ፤ ጦሩ በተለያየ ጊዜ ውስጣዊ ችግሮች ባጋጠሙ ቁጥር በኢትዮጵያ ላይ ትንኮሳዎችን ሲያደርግ መቆየቱን እንደቆየ ገልጿል።

በዚሁ የተለመደ ተግባሩ ሰሞኑ ደግሞ የሱዳን ኃይል ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት በአካባቢው በነበሩ የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ላይ ጥቃት ማድረሱንና ከሁለቱም ወገን ጉዳት መድረሱን ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በስፍራው ባልነበረበት ሁኔታ ” ምርኮኞችን ገደለ ” በሚል የሱዳን ጦር ክስ ማቅረቡ ተቀባይነት የሌለው መሰረተ ቢስ ክስ መሆኑም ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል።

የደረሰውን ጥቃት በተመለከተ ማጣራት የሚፈልግ አካል ካለ ከሁለቱ ሀገራት መከላከያ ሠራዊት ተወካዮች የተውጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ እንዲጣራ ለመተባበር የኢትዮጵያ ሠራዊት ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አረጋግጧል። ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ ገብታ ከአካባቢ ሚለሻ ጋር ተጋጭታ ወታደሮቿን ካጣች በኃላ የኢትዮጵያ ጦር ወታደሮቼን ገደለብኝ ስትል ክስ አሰምታለች።

ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም በሀገር መከላከያ ሚነስቴር በኩል በሰጠችው ምላሽ በተፈጠረው ሁኔታና የሰው ህይወት በመጥፋቱ አዝናለሁ ነገር ግን ሱዳን እራሷ የፈፀመችውን ጠብ አጫሪ ትንኮሳ ወደ ኢትዮጵያ ማላከኳ ተቀባይነት የለውም በተጨማሪ መከላከያው ባልነበረበት የመከላከያውን ስም እያነሳች የምትነዛው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው ስትል አስረግጣ ተናግራለች።

የሱዳንን በኢትዮጵያ ጦር ወታደሮቼ ተገደሉብኝን የሚለውን መሰረተ ቢስ ክስ ተከትሎ የግብፁ መሪ ” በሱዳን ወታደሮቹ ሞት እጅጉን አዝኛለሁ ” ሲሉ የሀዘን መልዕክት ለሱዳን ጦር አዛዥና ለሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን እና ለሱዳን ህዝብ መላካቸውን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ክስ ብቻ ሳይሆን ሱዳን እንደምትበቀል ዝታለች። የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር መካከል ተገኝተው ለጊዜው በይፋ ያልተገለጸ መመሪያ ሰጥተዋል።

ቡርሀን ትንሹ ፋሻጋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙት አል ዑስራና ዋድ ኮሊ አካባቢዎች የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር የጎበኙት ትናንት ነበር። በጉብኝቱ የተሰማው ሱዳን ” የአጸፋ ምላሽንማ ሳንሰጥ አንቀርም ” ስትል መዛቷ ነው። ጦራቸው የሃገሩን ዳር ድንበር ለመጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት በቁርጠኛ እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

ለሃገራቸው መስዋዕት የሚከፍሉ ወታደሮች ደም “በከንቱ ፈስሶ” አይቀርም ሲሉም ዝተዋል። ሁኔታው ተጨባጭ መልስ እንደሚያገኝ ቃል በመግባት ከሰሞኑ በአል ዑስራ ያጋጠመው ፈጽሞ አይደገምም ማለታቸው ተሰምቷል። የሱዳን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው እየገቡ ግድያ፣ ንብረት ዘረፋና የግብርና ስራ ሲያውኩ መቆየታቸው፣ ከ250 የማያንሱ እርሻ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች መስራት ተስኗቸው መቅመጣቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የሱዳን ሃይልን መመከት ብቻ ሳይሆን አልፎ ገብቶ ልክ ማስገባት አይከብዳቸውም። ግን የሚፈልጉት የመንግስትን ፈቃድና የትጥቅ ደጋፍ ነው። መንግስት ደግሞ የጦርነት አድማሱ እንዳይሰፋበትና ሃይሉ እንዳይበተን ሲል ለጊዜው ዲፕሎማሲ መምረጡና የታጋሽነት አካሄድ መመርጡ ሲገለጽ ቆይቷል። ይህን አካሄዱን በመንቀፍ ትህነግና ግብጽ የሚደግፋቸው “የኢትዮጵያዊያን” ሚዲያዎች መንግስት እንዲዋጋ አዛኝ መስለው ይወተውታሉ። ይህ ውትወታቸው መንግስትና ህዝብ መካከል ልዩነት ለመፍጠርና መንግስት ለድንበር መከበር ግድ እንደሌለው ለማሳየት ሲሆን ዋናው ዓላማው ይህንኑ ፍርሃቻ መንግስት ጦነት ውስጥ ገብቶ ሃይሉን እንዲበታትን ለማድርገ ነው።

በሱዳን መሬቶች ላይ ሚደረግ ምንም ዐይነት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በጎብኝታቸው መጨረሻ ትዕዛዝን አስተላልፈዋል። አል ፋሽቃ ኢትዮጵያና ሱዳን የባለቤትነት ጥያቄ የሚያነሱበት ሰፊ ለም መሬት ነው። ኢትዮጵያ ጦርነት ስትገባ የሱዳን ጦር የወረረው ይህ ሰፊ መሬቱ እንዲለቅና የድነር ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ኢትዮጵያ ብትጠይቅም ሱዳን አሻፈረኝ ማለቷ አይዘነጋም። አሻፈረኝ ማለቷ ብቻ ሳይሆን በአካባቢው መሰረት ልማት ማስጀመሯም እየተገለጸ ነው።

ከሰሞኑን ፤ ሱዳን ሞቱብኝ ያለቻቸው ወታደሮች ፤ የኢትዮጵያን ድንበርን አልፈው የገቡና (ጠብ አጫሪዎች እራሳቸው ናቸው) ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር ግጭት የፈጠሩ የሱዳን መደበኛ ወታደሮች ሲሆኑ ኢትዮጵያም በጠፋው የሰው ህይወት ማዘኗን መግለጿ ይታወቃል።

Exit mobile version