Site icon ETHIO12.COM

“ሚናችንን እንለይ” እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ሊጀመር ነው

” ሚናችንን እንለይ” የሚል እንቅስቃሴ በይፋ በኢትዮጵያ ሊጀመር መሆኑንን የአስተባብሪዎቹ መሪ ለኢትዮ12 አስታውቀዋል። ንቅናቄው የማንንም እምነት፣ አመለካከትና ወገናዊነት አይጋፋም። ነገር ግን ሁለት ቦታ መረገጥን፣ ሃጋዊና ህገ ወጥ መንገድን አጣምረው የሚከተሉትን ያወግዛል። እየተከታተለ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያጋልጣል።

ኢትዮጵያዊነትን ፍጹም ለድርድር የማያቅረበው የ”ሚናችንን እንለይ” እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን እየማጓት፣ እየበሉባትና እየኖሩባት በድብቅ ስለታቸው የሚያርዷትን ክፍሎች ማጋለጥና መታገል ዋናው አጀንዳው እንደሆነ አስተባባሪው ተናግረዋል።

“በርካታ ጉዳዮችን እያየን ነው። ዝምታው አያዋጣም። እኛም እንደሌሎች ለአገራችን ምስጥ መሆን አለብን” ያሉት አስተባባሪው እንቅስቃሴው በተለይም በአዲስ አበባ ተጀምሮ በዋና ዋና የተመረጡ ከተሞች የሚሰፋ እንደሚሆን አመልክተዋል።

“የሃይማኖት ድርጅት ያህል ጥብቅ ዲሲፒሊን አለን። ዲሲፒሊናችን ኢትዮጵያዊነት ነው። በባንዲራና በአጉል መፈክር ማጭበርበርን እንቃወማለን” ሲሉ አስተባባሪው አቋማቸውን ገልሰዋል። በቅርቡ ሃሳባቸውን ለምንግስ አቅርበው ውይይት የማድረግ ዓላማ ዕቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል።

እስከ ቀበሌና መንደር የሚዘልቅ ” የሚናችንን እንለይ” እንስቃሴ አብዝቶ የሚጠየፈውና አብዝቶ የሚታገለው ኢትዮጵያ እምብርት ላይ ሆነው ማሯን እየላሱ ለነሱ በድብቅ የሚመስል፣ ነገር ግን በግልጽ በሚታይ መልኩ ለኢትዮጵያ ጸር የሆነ ድርጅት የሚደግፉና የሚረዱትን ነው። አስተባባሪው “ሚናቸውን ይለዩ” ሲሉ የሚገልጿቸው እነዚህ ወገኖች ምርጫቸው የሚከበር ነው። የፈለጉትን አመለካከት መያዝ ይችላሉ። ነገር ግን በሁለት ቢላዋ መብላት፣ በሁለት መለያ መቻወት፣ በሁለት ቀለም መሽሞንሞን፣ ሁለት ተቃራኒ መንገድ ማጣቀስ አይችሉም።

ፍጹም ለአገር በሚቆረቆሩ ወገኖች አሳብ አፍላቂነት የተጀመረው እንቅስቃሴ በሙሉ ፈቃደኛነት ላይ የተመሰረተ፣ በሙሉ ፈቃደኛነት ላይ ተመስርተው አገራቸውን መጠበቅና ለአገራቸው ሰላይ መሆን የሚፈልጉ ውስን አባላትን የያዘ ነው። እንደ አስተባባሪው ይህ ንቅናቄ አገር ወዳዶችን በጥብቅ ዲሲፒሊን ማደራጀት መጀመሩን ግለሰዋል። በተለያዩ የስራ መስክ የሚገኙ፣ በትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰሩ፣ በትምህርት ቤታን ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም በተለያዩ ተቅማትና በመንደሮች እንቅስቃሴ እንዲጀምሩ ይደረጋል። “ታሪክና ጊዜ አስተምሮናልና በየስፍራው በመኖሪያ ቤት ሳይቀር እየተደራጁ ሲያታልሉን ለነበሩ ዳግም አንፈቅድላቸውም” ሲሉ እንቅስቃሴ መረር ያለ አቋም እንዳለው አስተባባሪው አስረድተዋል።

እንቅስቃሴው ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረገ ሲሆን በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን፣ ይፋ ሲሆን ህዝብ ልዩ እውቅና እንደሚሰጠው፣ የመንግስትን የጸጥታ ተቋማት አቅም በእጅጉ የሚያግዝና “ነቀዞች” ያሉዋቸውን ፋታ የሚነሳ እንደሚሆን ከሃላፊው ገለጻ ለመረዳት ተችሏል። መሰል እንቅስቃሴዎች ስማቸው ቢለያይም በበርካታ አገሮች መኖራቸውንም አስታውሰዋል። “ህዝብ የአገሩ ሰላይ ነው። እኛም ህዝባችንን የአገሩ ሰላይ እናድርጋለን። ይህም የሚሆነው በወዶ ፈቃደኛነት ብቻ ነው” ሲሉ አመልክተዋል።

ሲያጠቃልሉም ” ኢትዮጵያን እየጠቡ ማረድ አይቻልም የሚል መሪ ቃል ተዘጋጅቷል” ብለዋል። ሰላም ሊያመጣ በሚችል ማናቸውም ጥረት ንቅናቄው እንደሚደግፍና እንደሚያደንቅም ጠቁመዋል። ሴረኞችን እንደሚኮንኑና እስከወዲያኛው እነሱ ከሚያደርጉት በላይ ሲስተም በመዘርጋት እንደሚታገሏቸው በድጋሚ ገልጸዋል። “የኢትዮጵያ ህዝብ የዋህ ነው፣ አገር ወዳድ ነው። ክፉዎች የዋህነቱን እንደ ሞኝነት በመቁጠር ቆምረውበታል። ያ ጥፋት ዛሬ አይደገምም። እንቅስቃሴውም ዓላማው ይህና ይህ ብቻ ነው። በፊትለፊት ወዳጅ፣ በጀርባ ባለ ካራ የሆኑት አያታልሉንም። ስላወቅን የሚጠቅመው ሚና መለየት ብቻ ነው”

Exit mobile version