Site icon ETHIO12.COM

ጅቡቲ የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ላይ ስጋት አየፈጠረች ነው? እንደ ዩክሬን

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲን የሚገኙበት የአፍሪካ ቀንድ ዛሬ ላይ የመካከለኛው ምስራቅ ኃያላን ተፎካካሪዎች እና የአለም ኃያላን ሀገራት የጦርነት ቀጠና ለማድረግ በሚያደርጉት ሩጫ የቀጠናው ሀገሮች ትልቅ ፈተና ላይ ወድቀዋል።

ቀደም ሲል ቀጠናው የአለማችን ታላላቅ ኃያላን በተለይም በቻይና እና በዩናይትድ ስቴትስ ፉክክር ላይ ነበር። ነገር ግን ዛሬ ላይ የአፍሪካ ቀንድ ለአዳዲስ ተፎካካሪ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች የጦር ሜዳ ሆኗል። ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ቱርክ፣ኳታር፣ ኢራን እና ግብፅ በአፍሪካ ቀንድ ጥቅሞቻቸውን የሚያስጠብቁ ዋና ቀጣናዊ ተዋንያን እየሆኑ ነው።

አካባቢው ታዳጊ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገሮች መሆኑ ለኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ኢንቨስትመንት የሚስብ ቀጠና መሆኑ አስፈላጊነቱ ያጎላው ቢሆንም ሁለት ወቅታዊ ሁኔታዎች እንደ ምክንያት ይቀርባሉ።

የመጀመሪያው ምክንያት ጂኦግራፊያዊ ነው። ቀንዱ የኤደንን ባህረ ሰላጤ እና የባብ ኤል- ሜንዴብ የባህር ዳርቻን የሚዋሰን በመሆኑ በዓለም ላይ ካሉት አስፈላጊ የባህር መስመሮች አንዱ ነው። በእስያ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአውሮፓ ገበያዎች መካከል የሚደረጉት አብዛኛዎቹ የንግድ እንቅስቃሴዎች በዚህ መንገድ ስለሚሄዱ የዚህ የባህር ዳርቻ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ በጣም ወሳኝ ነው። ከ10% በላይ የሚሆነው የዓለም የባህር ጭነት አብዛኛው ከአውሮፓ እና የእስያ ንግድን ጨምሮ በየዓመቱ ያልፋል። ለስልታዊ ምክንያቶች ብዙ አገሮች በዚህ ክልል ውስጥ መገኘታቸውን ማጠናከር ይፈልጋሉ።

ከዚህም በላይ የአፍሪካ ቀንድን በጣም አስፈላጊ የሚያደርገው ሁለተኛው ምክንያት ቀጠናው በእስያና በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ለአፍሪካ ገበያ ዋነኛ መግቢያ በር ተደርጎ መወሰዱ ነው።

በአፍሪካ ቀንድ ወታደራዊ ሰፈሮች መስፋፋት በኢኮኖሚያዊም ሆነ በወታደራዊ ምክንያቶች የቀጠናው ጂኦስትራቴጂካዊ ጠቀሜታን ለመጠቀም የአለማችን ኃይላኖች ወታደራዊ ሰፈሮችን ለመገንባት ሲሯሯጡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ታይቷል።

– በተለይም ጂቡቲ ላይ ነው የሁሉም ትኩረታቸው። የቀጠናው እውነተኛ ስትራቴጂካዊ ማዕከል ለመሆን የምትፈልገው እና የምስራቅ አፍሪካ መግቢያ በር ተደርጋ የምትወሰደው ጥንጥዬዋ ጅቡቲ የኃያላን መንግስታት ሀገሮችን ወታደራዊ ቤዝ ለመመስረት ተመራጭ አድሮጓታል። ጅቡቲ 8 የጦር ሰፈሮችን ታስተናግዳለች። እነሱም የዩናይትድ ስቴትስ፣ የጃፓን (ከግዛቷ ውጭ ያለው ብቸኛ ወታደራዊ ጦር ሰፈር ነው)፣ ጣሊያን፣ ቻይና፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ፈረንሳይ (ቅኝ ገዥዋ በመሆኗ ወታደራዊ ሰፈሩ በጣም አስፈላጊው ነው)፣ ጀርመን እና ስፔን ናቸው። በዚህም ምክንያት ጅቡቲ በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደራዊ ተቋም ያላት ሀገር ሆናለች። ሀገሪቱ ከእነዚህ የጦር ሰፈሮች በአመት 300 ሚለመዮን ዶላር ታገኛለች። የውጭ ወታደራዊ ሰፈሮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እና በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በተለይም በጅቡቲ የሚገኙ የተለያዩ ሀገሮች ወታደሮች መገኘታቸው የባብ ኤል-ማንደብ ባህርን ቀጣናዊ ደህንነት፣ ኢኮኖሚያዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታ ያሳያል።

– ኤርትራ በበኩሏ የሩሲያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ወታደራዊ ሰፈር ታስተናግዳለች።
🇸🇴ሶማሊያ የቱርክ የጦር ሰፈር የሚገኝባት ሲሆን የኤምሬትስ ሁለተኛ ሰፈር ከሶማሊያ በተገነጠለችው ሶማሊላንድ ውስጥ ነው። አሜሪካ በቅርቡ ጅቡቲ ያላትን የጦር ሰፈር ወደ ሶማሌ ላንድ ታዞራለች ተብሎ ይጠበቃል።

በአካባቢው ወደቦች (በተለይ በጅቡቲ፣ ፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ) ከፍተኛ ኢንቨስት ያደረገችው የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በ2015 በኤርትራ የጦር ሰፈር የከፈተች ሲሆን በቅርቡ ከሶማሌላንድ ጋር ስምምነት ተፈራርማለች። ሩሲያ አሁን በሱዳን ሁለተኛ ሰፈር ለመመስረት አቅዳለች።

የእነዚህ ተቋማት መገኘት ለቀጠናው ሀገራት ደካማ ኢኮኖሚ ጠቃሚ ነው። ነገር ግን ይህ ለአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እና ደህንነት ዘላቂ ችግር ሊያስከትል ይችላል።

በተጨማሪም የውጭ ኃይሎች በአካባቢው መኖራቸው እና እንቅስቃሴያቸው በሣህል ውስጥ ከሚገኙት እንደ አልሸባብ፣ ቦኮ ሃራም እና አሸባሪ ቡድኖችን በመዋጋት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የውስጥ ደህንነት ላይ ስጋት ይፈጥራል።

በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ባሉ ቀጣናዊ ኃይሎች መካከል ያለው የጂኦፖለቲካዊ ተፅእኖ ትግል በሁለት ምሰሶዎች ዙሪያ የተከፈለፐነው፦ በአንድ በኩል ጎረቤት አረብ አገሮች (ሳውዲ አረቢያ፣ ግብፅ እና ኤሚሬትስ) አንድ ጥምረት፤ በሌላ በኩል ምእራባዊያን አገሮች convergence የሚሏቸው ኳታር፣ ቱርክና ኢራን ናቸው)።

– ራሺያ ዩክሬንን እደከሰሰችው የቀጠናው ሀገሮች ጅቡቲን የደህንነት ስጋት ፈጥራብናለች በማለት ይቆነጥጧት ይሆን? ለጊዜ እንተወው።

-በነገራችን ላይ አሜሪካ ጅቡቲ ያላትን የጦር ሰፈር “ካምኘ ሌሙኒየር” ሙሉ ለሙሉ ነቅላ ሶማሌ ላንድ የማዞር እቅድ አላት።

– የአፍሪካ ቀንድ በዚህ ደረጃ እየተናጠ ባለበት ወቅት ሀገራችንን አቅሟን እንዳታጠናክር እያደረጓት ያሉት አሸባሪዎችንና ጽንፈኞችን ታሪክ ይፋረዳቸዋል።

Exit mobile version