Site icon ETHIO12.COM

ከቤት እጣ ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባ አስተዳደርን “ማጅራት መቱ” የተባሉ የፈጸሙት ድራማ

በዚህ ሂደት የቤት ስርቆት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት ጭምር መግለፅ ይቻላል፤ ዓላማው መንግስት ህዝብን ማገልገል ብቃት የለውም የሚል ገፅታ ለመፍጠርና ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲያምፅ ለማድረግ በማሰብ ነው፣ የምዝገባው ዳታውን በቴሌግራም ጭምር ሲላላኩ እንደነበር በኋላ በምርመራ ታውቋል፣ በግልፅ ማንሳት የምንፈልገው በወቅቱ የተሰጠን ማብራርያ ከእውነት የራቀ መሆኑን በባለሙያዎች ተረጋግጧል፣

ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሰተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ፤ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የአጣሪ ቡድን መሪ አቶ በሀይሉ አዱኛ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከኢመደአ፤ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፤ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጎ ወደ ማጣራት ስራ በመግባት ሲጣራ ቆይቶ በዛሬው እለት በጋዜጣዊ መግለጫው ይፋ ተደርጓል፡፡

በመግለጫው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያነሷቸው ነጥቦች፤

👉 የጋራ መኖርያ ቤት እጣ በማውጣት ሂደት ባጋጠመ ችግር ህዝቡንም ከተማ አስተዳደሩንም ያሳዘነ ድርጊት ተፈጽሟል፣

👉 በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ህብረተሰቡ በትእግስት በመጠበቅ፤ የጀመርነውን ጥረት ከጎናችን በመቆም ላሳየው ጥረት ከልብ እናመሰግናለን፣

👉 ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ችግር ቢያጋጥም እንኳን በቀጥታ ኦዲት እናደርጋለን ብለን በገለፅነው መሰረት በደረሰን ጥቆማ በሚመለከታቸው አካላት የማጣራት ስራ እንዲጀመር አስደርገናል፣

👉 የቴክኖሎጂ ውንብድና አጋጥሞናል፣ አመራር የመራው ውንብዳ ነው፣

👉 በዚህ ሂደት የቤት ስርቆት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት ጭምር መግለፅ ይቻላል፤ ዓላማው መንግስት ህዝብን ማገልገል ብቃት የለውም የሚል ገፅታ ለመፍጠርና ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲያምፅ ለማድረግ በማሰብ ነው፣

👉 በዚህ ሂደት ችግር እንዳጋጠመን ማጣራት መጀመራችን የህዝብን ሃብት መታደግ እንድንችል አድርጎናል፣

👉 ህብረተሰቡ መብቱን ለማስጠበቅ ያደረግነውን ጥረት ተረድተን ድሃውን ማህበረሰብ መታደግ በመቻላችን ያስደስተናል፣

👉 የቀረበልን ሪፖርት በሚገባ ሲስተሙ ተቆጣጣሪ ጭምር እንዳለውና አስተማማኝ እንደነበረ ነው፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት በዚህ ቡድን የለሙና ጥቅም ላይ የዋሉ ሲስተሞች ነበሩ፣

👉 ማረጋገጫ ለማግኘት የተሄደበትና ተቋም ለተቋም የተደረጉ ግንኙነቶችም ችግር ነበረባቸው፤ ሰዎች ለሰዎች የተደረጉ ግንኙነቶች አይነት የተደረጉ ግንኙነቶችም መመልከት ተችሏል፣

👉 ኢንሳ ማረጋገጫ ሰጥቶ እንደነበር በወቅቱ ተገልፆ ነበር፣ ነገር ግን ህጋዊ በሆነ ደብዳቤ የተረጋገጠ እንዳለሆነ ታይቷል፣

👉 ዳታው በሰዎች አጅ ለአምስት ቀን ያህል መቆየቱና ይህም የተከናወነው በሃላፊዎች ትእዛዝ ነበር፣

👉 የምዝገባው ዳታውን በቴሌግራም ጭምር ሲላላኩ እንደነበር በኋላ በምርመራ ታውቋል፣

👉 በሂደቱም እጣ ቁጠባ ያቋረጡ ሰዎች ፤ቁጠባቸውን ከረሱበት ቦታ ጭምር እጣ እንዲወጣላቸው መደረጉ፣

👉 የማጣራት ሂደቱን እጣ የወጣ እለት ከሰዓታት በኋላ መጀመሩን፣

👉 ይህ የማጣራት ሂደት ኢንሳ አራት ባለሙያዎች መወከሉንና ከሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ከብሄራዊ ደህንነት የተዋቀረ ኮሚቴ ስራውን ሲሰራ ቆይቷል፣

👉 ቴክኖሎጂዎች ለመጠቀም ያደረግነውን ጥረት ወደፊትም ይቀጥላል፤ ቴክኖሎጂዎችን የሚያለማው ሰው ቢሆንም ወደፊት በረቀቀ የሙያ ስልት እጣ አወጣጡን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እናድርጋለን፣

👉 በግልፅ ማንሳት የምንፈልገው በወቅቱ የተሰጠን ማብራርያ ከእውነት የራቀ መሆኑን በባለሙያዎች ተረጋግጧል፣

👉 ባለሙያዎችና አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ አንድ ሃላፊና አንድ ምክትል ሃላፊ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፣

👉 ሌሎች እርምጃዎች እንደ ሚዛኑ የሚቀጥል ይሆናል፣

👉 የከተማ አስተዳደሩ አሁንም ቆራጥ አቋሙ የህዝቡን መብት ማስከበር በመሆኑ ይህንን ቤት ለህዝብ ለማቅረብ ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ጭምር የጎደለውን መሰረተ ልማት በሟሟላት ለህዝብ ማድረሱን፣

👉 የኮንዶሚኒየም መጥፎ ታሪክን ላለመድገም ከፍተኛ ፍላጎት ነበረን፤ አሁንም ይቀጥላል፤ አሁንም የተቋም ግንባታ አጠናክረን እንቀጥላለን፣

ስለሆነም በዚህ ሁሉ ችግር እና ሂደት የወጣን እጣ ተዓማኒነት ስለሌለው እጣው ሙሉ ለሙሉ ውድቅ እንዲሆን ተደርጓል።

Exit mobile version