Site icon ETHIO12.COM

አቶ ምትኩን በስኳር ያጠበው ኤልሻዳይ የትህነግ ድርጅት መሆኑ ተሰማ – የሚስጢር ምርመራ ይፋ ሆነ

ኤልሻዳይ የተባለውና ራሱን የግብረ ሰናይ ተቋም አድርጎ ሲሰራ የቆየው ድርጅት የትህነግ ኣንድ ክፋይ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች አየወጡ ነው። የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ ኣመራር ኮሚሽን ኮሚሽነርን ከነቤተሰባቸው በስኳር ያጠበው ይህ ድርጅት አቶ ስብሃት ነጋ ልዩ ከለላ ሲያደርጉለት አንደነበር ድርጅቱን ጠልቀው የሚያውቁ አስታውቀዋል።

የትግራይ ተወላጅ የሆኑት የኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ የማነ ገ/ማሪያምና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች የአቶ ምትኩን ሚስት፣ልጆች፣ አናት በየደረጃው በከፍተኛ ደረጃ በሙስና ያጠመቁት በተለይ በአማራ፣ በአፋርና በጋምቤላ ተረጂዎች ስም በተፈጸመ የተቀናጀ ሌብነት መሆኑንን የፖሊስ ማስረጃ ያመለክታል።

ትህነግ በስልጣን በነበረበት ወቅት ሞራላቸው አላሽቆ አንደሰራቸው ከሚነገርላቸው ባለስልጣናት መካከል ኣንዱ አንደሆኑ የሚነገርላቸው ኣቶ ምትኩ ለተመደቡበት ቦታ ብቁ አንዳልሆኑ፣ በተሳሳተ መረጃና ዳታ ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ ሲደረግ በወጉ ማስተባበል የማይችሉ፣ ለውጭ አገር መገናኛዎች ኣግባብ ባለውና በጸዳ ቋንቋ ማስረዳት የማይችሉ መሆናቸውን አየተጠቀሰ ሲተቹ ነበር። ዛሬ ለመስማት በሚያስቸግር ደረጃ በሙስና መነከራቸው ሲሰማ “በተሳሳተ መረጃ በኤልሻዳይ አማካይነት ትህነግን በሚጠቅም መልኩ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ሲያስቀጠቅጡ ስለመቆየታቸው ምርመራ ሊደረግ አንደሚገባ ጠቁመዋል። በሙስና ያጠመቃቸው ድርጅት የትህነግ አጅ በመሆኑ ምርመራው ከሙስና በዘለለ አንደሆነም ተሰምቷል”

የመንግስት መገናኛ ዘዴዎች አንዳሉት ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን መንግስትዊ ያልሆነ ገብረሰናይ ድርጅት በተረጂዎች ስም ከብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለእርዳታ የተዘጋጀን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶችን አላግባብ ወስዶ ለግልጥቅም አውሏል በሚል ተጠርጥረው ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል። በዚህም መሰረት ፖሊስ ባደረገው የማጣራት ስራ የተሰበሰበውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በተለይ ለኢቲቪ አስታውቋል። በምርመራ ሂደቱ የተገኙ ግኝቶችም፦

1ኛ- ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን በየጊዜው አሉ ተብሎ እርዳታ የሚጠየቅላቸው ዜጎች በትክክል ስለመኖራቸው እና አለመኖራቸው በተደረገ ምርመራ፡- ድርጀቱ በክልል ካሉት ማዕከል ውስጥ በ3 ማዕከላት ማለትም በአማራ ክልል ቁጭት ለልማት ማዕከልከ 2010 እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ የተረጂዎችን ቁጥር በመጨመር፤ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2019 ማእከሉ 14 ተረጂዎች ብቻ እያለው ዓመቱን ሙሉ በ2 ሺህ 631 ተረጂዎች ስም የእርዳታ ስንዴ ጠይቆ ከኮሚሽኑ የተሰጠው መሆኑን በማስረጃ ተረጋግጧል።

ድርጅቱ በአፋር እና ደቡብ ክልል ማዕከል የተረጂዎችን ቁጥር በመጨመር የጠየቀ እና የወሰደ መሆኑን፣ በጋምቤላ ክልል ማዕከል ስም የጠየቀው ተፈቅዶለት ያልወሰደ እና በሙከራ ደረጃ የቀረ መሆኑን በማስረጃ ለማረጋገ ጥተችሏል

2ኛ- ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን በተለይ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ አለአግባብ ከኮሚሽኑ ጠይቆ የተሰጠውን የእርዳታ ስንዴ ምን እንደሚያደረገው በተደረገ ምርመራ፡- ድርጅቱ ከመንግስት የወሰደውን ስንዴ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ለሚገኝ ኪያ የዲቄት ፋብሪካ (ሶሮሮ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር) 66 ሺህ ኩንታል ስንዴ በ66 ሚሊዮን ብር ሸጦ ግንዘቡን የወሰደ መሆኑን፣ 6 ሺህ ኩንታል ስንዴ በብር 6 ሚሊዮን ግምት በ4 ተሸከርካሪ በአይነት ከሶሮሮ ትሬዲግ የተለዋወጠ መሆኑን፤ ኤልሻዳይ ድርጅት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አዋሽ መልካ የሚገኝ ነጃኼ ሬዲን የድቄት ፋብሪካ ባለቤት እና ሰራተኛ ስም 27 ሚሊዮን ብር የገባለት በመሆኑ ነጃሄ ትሬዲን ተጠይቆ 15 ሚሊዮን ብር ያስገባው ከኤልሻዳይ ስንዴ ገዝቶ መሆኑን በሰነድ በማስደገፍ ቃሉን የሰጠ ሲሆን ቀሪው 12 ሚሊዮን ብር ቢሆን የሰነድ አያያዝ ችግር ነው እንጂ የስንዴ ግዥ ብር ነው በማለት የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል።

3ኛ- በኤልሻዳይ ድርጅት የበላይ አመራር አቶ የማነ ገ/ማሪያም እና በኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ መካከል መመሳጠር መኖር እና አለመኖሩን በተደረገ ምርመራ፡- ኤልሻዳይ ኮሚሽኑን እርዳታ ለመጠየቅ ያዘጋጀው የአንድ ጊዜ በእጅ ፁሕፍ የረቀቀ መጠይቅ ሰነድ ተገኝቶ በፎረንሲክ ምርመራ ረቂቂ የእጅ ፁህፍ ተመርምሮ የብሔራዊ አደጋ መከላከል ስራ አመራር ከሚሽን ኮሚሽነር በኤልሻዳይ ስም የተዘጋ መሆኑ ተረጋግጧል። በተጨማሪም በኮሚሽነሩ ቤተሰቦች ላይ በተደረገ ማጣራት፦

1ኛ – የኮሚሽነሩ ወንድ ልጅ ኢያሱ ምትኩ ካሳ በኤልሻዳይ ድርጅት በተላለፈ ገንዘብ መኪና ተገዝቶለት ይህንኑ መኪና መልሶ ኤልሻዳይ የገዛው መሆኑን በማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን፤ እንዲሁም ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በኤልሻዳይ ድርጅት ፀሀፊ ስም በወር 15 ሺህ ብር በተከራየው ሙሉ ጊቢ ውስጥ የሚኖር መሆኑን መረጃ ደርሶ፤ በቤቱ ውስጥ የተባለው የኮሚሽነሩ ልጅ መኖሩን ወርሃዊ ክፍያውንም ኤልሳሻዳይ ድርጅት እንደሚከፍልለት በሰውና በሰነድ ተረጋግጧል፣

2ኛ- የኮሚሽነሩ ሴት ልጅ ወ/ሮ ሚኪያ ምትኩ ካሳ በኤልሻዳይ ድርጅት ውስጥ ተቀጣሪ ሳትሆን በኤልሻዳይ ድርጅት ፔሮል ውስጥ ስሟ ተካቶ ለ1 ዓመት ያክል በወር አምስት ሺህ ብር ደመወዝ በባንከ በኩል ሲከፈላት እንደነበር በማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል። እንዲሁም ከኤልሻዳይ ድርጅት የባንክ ሂሳብ ብር 800 ሺህ ብር ወደ ሚኪያ ምትኩ በተለያዩ ጊዚያት ገቢ መሆኑን በሰነድ ማረጋገጥ ተችሏል፤ እንዲሁም ተጨማሪ ማጣራም በማጣራት ላይ ይገኛል

3ኛ- የኮሚሽነሩ ባለቤት በወ/ሮ ሶፊያ ጀማል ስም ከእንይ ጀኔራል ቢዝነስ ሪል እስቴት (በወኪል የማነ ወ/ማሪያም በርሄ አማካኝነት (የኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ) ከኤልሻዳይ ድርጅት ሂሳብ ወጭ በተደረገ በብር 8,306,737.75 የቦታ ስፋት 388.75 ካሬ ሜትር የሆነ በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ የተገዛው መሆኑን እንዲሁም ተጨማሪ ጥቆማዎች ላይም ማጣራት እየተካሄደ ስለመሆኑ

4ኛ- የኮሚሽነሩ ወላጅ እናት ወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ከኤልሻዳይ ድርጅት 5,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን) ብር በሲፒ.ኦ ገቢ በሆነላት ብር በቦሌ ክፍለ ከተማ ብቻ በተደረገ ማጣራት በኤልሻዳይ ድርጅት እና የኮሚሽነሩ የቅርብ ጉዳይ አስፈፃሚ በሆኑ ግለሰቦችና የወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ህጋዊ ወኪሎች አማካኝነት 7 ቤቶች የገዛች መሆኑ በተጨማሪም ከወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ስም የተገዙ ቤቶችን በተመለከተ ሙሉ ውክልና ለኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለሆኑት አቶ የማነ ገ/ማሪያም ውክልና ሰጥተው የተገኙ መሆኑን ይህ ቀሪ የማጥራት ስራ የሚቀረው ቢሆንም መመሳጠር መኖሩን ያስረዳል።

እንዲሁም ከእነዚህ ሰባት ቤቶች መካከል አንዱን አቶ የማነህ ገ/ማሪያም በተሰጠው ውክልና መሰረት ከወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ለአቶ ምትኩ ካሳ መሸጡን ይህ ሽያጭ ሲፈፀም አቶ የማነ ገ/ማሪያም ሀሰተኛ መታወቂያ፣ ሀሰተኛ ፎቶ መጠቀሙን ተረጋግጧል። 5ኛ አቶ ምትኩ ካሳ ሚኖሩበት ቤት ቁጥር በማስመዝገብ እና የሌላን ሰው ፎቶግራፍ በመጠቀም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በስማቸው አሰርተው የተገኙ መሆኑን በማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል፣ ቤተሰባዊ ግንኙነቱ በመጣራት ላይ የሚገኝ 18 አመት ባልሞላው ልጅ መሀመድ አብዲልፈታህ አብዱላሂ በተበለ ስም ከእንይ ጅኔራል ቢዝነስ ሪል እስቴት ከኤልሳዳይ ድርጅት ሂሳብ ወጭ በተደረገ ገንዘብ በብር 8,306,737.75 የቦታ ስፋት 388.75 ካሬ ሜትር የሆነ በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ የተገዛው መሆኑን፣ በምርመራ መዝገቡ ላይ ተጠርጣሪ የሆኑት፡- 1. የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነሩ አቶ ምትኩ ካሳ እና ቤተሰቦቻቸው ፤ 2. የኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ የማነ ወ/ማሪያም፤ 3. የኤልሻዳይድርጅት ኦፕሬሽናል ዘርፍ ምክትል ስ/አስኪያጅ ዶ/ር ዮናስ ወ/ትንሳይ እና 4. የኤልሻዳይ ድርጅት የፋይናንስ ዘርፍ ምክትል ስ/አስኪያጅ አቶ ደመወዝ ኃይሉ መሆናቸውን የኢቢሲ.ዘገባ ያስረዳል።

Exit mobile version