Site icon ETHIO12.COM

የሸኔ ወታደራዊ ክንፍ መሪ ጃል ጅግሳ ተማረከ

የስቃይ ኑሮ ነው። በጫካ እያለን ቀምለናል። ያለ አላማ ነው የታገልነው። አሁንም በጫካ ያለው ኑሮ ታጣቂዎቹን አሰልችቶታል። የቡድኑ ታጣቂዎች በተዛባ መንገድ ከገቡ በኋላ ተገደው ህዝብን ያሰቃያሉ፣ ከበላይ አመራሮች በሚሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ሚሊሻና የመንግስት ሰረተኞችን እንገላለን። ይህ ተግባር ደግሞ ትክክል እንዳልሆነ ሁሉም ታጣቂዎች ቢያዉቁም ከትግሉ ከከዱ ቤተሰባቸው ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመፍራት ያለ አላማ በጫካ ውስጥ ይኖራሉ።

– ከሸኔ ምርኮኞችና ወዶ ገቦች አንደበት

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በሆሩ ጉድሩ ዞን የመከላከያ ሠራዊታችን በአሸባሪው ሸኔ ላይ ባደረገው ዘመቻ በርካታ የቡዱኑ አመራሮች እና አባላት ተደምስሰዋል ተማርከዋል። ከተማረኩት አመራሮች መካከል ጃል ጅግሳ አንዱ ነው።

ጃል ጅግሳ ትክክለኛ ስሙ ሞቱማ ኡማ ነው። ይህ የአሸባሪው ሸኔ ወታደራዊ ክንፍ መሪ በመከላከያ ሰራዊቱ በተደረገው ዘመቻ የቡድኑ አባላት በሙሉ በመደምሳሰቸው እጁን ለጀግናው ሰራዊታችን ሠጥቷል።

– ከምርኮኞቹ አንደበት

ጃል ጅግሳ (ሞቱማ ኡማ)፦ እስከአሁን በተደረገው ድርጊት ተፀፅቻለሁ። እኔ ወደ ትግሉ የገባሁት በተሳሳተ ቅስቀሳ ነው። አባኦ የኦሮሞ የነፃነት ትግል እንደሆነ ተነግሮኝ ብገባም ከገባሁ በኋላ ያገኘሁት የቡድኑ አላማ በፍጹም ይለያል። በጣም

ሌላኛው መሪም የቡድኑን እኩይ ተግባር በመረዳት አሸባሪው የሰጠውን የጃል ወይም የወታደራዊ ክንፍ መሪነት ትቶ በሰላማዊ መንገድ እጁን ለመከላከያ ሰራዊቱ ሠጥቷል።

ጃል ዴብሳ ኩማ፦ በሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን ውስጥ የታጣቂዎቹ ክንፍ መሪ ነበርኩ። ትግሉን የተቀላቀልኩት የኦሮሞ ህዝቦች የነፃነት ትግል ነው ሲሉኝ ነው ተነስቼ የገባሁት። ነገር ግን ከገባሁ በኋላ ተመልሰን የኦሮሞን ህዝብን ነው የወጋነው፣ የኦሮሞን ህዝብ በስሙ ነግደንበታል። ህብረተሰቡን ዘርፈናል፣ ገድለናል፣ አካል አጉድለናል። ስለሆነም የቡድኑ ክንፍ መሪ በመሆኔም በእጅጉ ተፀፅቼአለሁ።

የቡድኑ አላማ ትርጉም የሌለው ተራ ውንብድና መሆኑን ስለተገነዘብኩ የሰጠኝን የመምራት ኃላፊነት ትቼ በሰላም ለመከላከያ ሰራዊቱ እጄን ሰጥቼለሁ።

አሁንም ለቡድኑ ታጣቂዎች የማስተላልፈው መልዕክት እንደእኔ እጃችሁን በሰላማዊ መንገድ ለመከላከያ ሰራዊት ሰጥታችሁ ሰላማዊ የሆነ ኑሮአችሁን እንድትኖሩ ነው።

ሌላው በሰላማዊ መንገድ እጁን ለመከላከያ የሰጠው ጃል ዋዳ (ጫለ አዱኛ) ይባላል። ጃል ዋዳም የታጣቂ ቡዱኑ አባልና አመራር በመሆኑና በሚፈፅሙት ሰይጣናዊ ተግባር በመፀፀት በአከባቢው አባገዳዎች በተደረገው የሰላም ጥሪን ተቀብሎ ከእነሙሉ ትጥቁ እጁን ለመከላከያ ሰራዊታችን ሰጥቷል።

ጃል ዋዳ (ጫለ አዱኛ)፦ አሁን በመከላከያ ሰራዊታችን እጅ በመሆኔ ነፃነትና ሰላም እየተሰማኝ ነው። በተሳሳተ መንገድ ቡድኑን በመቀላቀሌ ተፀፅቻለሁ። ሌሎች በረሃ የሚገኙ የቡድኑ ታጣቂዎችም የተደረገውን የሰላም ጥሪ ተቀብላችሁ በሰላም እጃችሁን ለመከላከያ ሰራዊቱ ስጡ።
ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

ታሪኩ ሻሜቦ – Defence FB
ፎቶግራፍ ታሪኩ ሻሜቦ

Exit mobile version