ETHIO12.COM

በርካቶች ወደ አማራ ክልል በሚፈልሱበት አቅጣጫ የትህነግ ተዋጊዎች እጅ እየሰጡ ነው

በቆቦ መስመር ተጀመረ የተባለውን ጦርነት ተከትሎ የትህነግ ተዋጊዎች ማፈግፈጋቸውና በርካታ እጅ መስጠታቸው ተሰማ። በተደጋጋሚ የትግርያ ሰላማዊ ሰዎች፣ በተለይም ወታቶችና ታዳጊዎች ወደ አማራ ክልል በሚፈልሱበት አቅጣጫ ተጀመረ የተባለው ውጊያ ሃያ አራት ሰዓት አልሞላውም። ከጦርነቱ ወሬ በፊት ከአሜሪካ የወጣው ዜና ለትህነግ ተስፋ ሰጥቶ እንደነበር ተመልክቷል።

የአካባቢውን ስም ከመጥቀስ ተቆጥበው ለአዲስ አበባ ዘጋቢያችን መረጃ የሰጡ እንዳሉት በትህነግ በኩል የውጊያውን መስመር አስፍቶ ለማጥቃት የተሞከረ ቢሆንም፣ መከላከያ በምድርና በአየር ምላሽ ለመስጠት ጊዜ አልወሰደም። መንግስት በተደጋጋሚ የአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች ሙሉ በሙሉ በተጠንቀቅ እንደሆኑ ሲያስታውቁ እንደነበር ይታወሳል።

በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በኩልም የሚፈልጉትን በሃይል ለማስፈጸምና ተያዘብን የሚሉትን አካባቢ በጉልበት ለማስመለስ ዝግጅታቸውን መጨረሳቸውን በቀድሞ ሌተና ጄነራል ታደሰ ወረደና በትግራይ መሪ ዲክተር ደብረጽዮን አማካይነት ለትግራይ ህዝብና ለዲያስፖራ ደጋፊዎቻቸው ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

ወደ አማራ ክልል የገቡ የትግራይ ተወላጆች ወጣቱን ሰብስበው አካላቸው የጎደለና በክራንች የሚሄዱትን በማቅረብ “ካላሻችንን ተረከቡን” በሚል አስገድደው ለወታደርነት እንደሚመለምሉ፣ ዕርዳታ ለወታደሮች ብቻ እንደሚውል፣ ወጣቶች የመዋጋት ፍላጎት እንደሌላቸው፣ ከትግራይ የሚሸሹትን እርምጃ ይወስዱባቸውል…” በሚል በርካቶችን ያነጋገረ መረጃ መስጠታቸው ከላይ ከተቀመጠው የጦርነት ዝግጅት ዜና ጋር የሚጣላ ሆኖ ከርሟል።

ይህ ሰሞኑንን አሜሪካ ከመቶ የሚልቁ የአየር ሃይል አባልቷን (Highly specialized unit) ከትናንት በስቲያ ወደ ምስራቅ አፍሪካ መላኳን የሚያሳይ መረጃ ሆን ተብሎ በየሚዲያው እንዲራባ ተደርጓል። ይህ ወደ ምስራቅ አፍሪቃ ተላከ የተባለው ቡድኑ ለወራት የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል። ትህነግ ይህን ሃይል እንደተማመነ አስቀድመው ሲናገሩ የነበሩ ተጨማሪ አሳባቸውን አላከሉም። ቀደም ሲል የትግራይ ወራሪ ሃይል ወደ ደብረ ሲና ሲያቀና አሜሪካ በተመሳሳይ በጅቡቲ ያለውን ሃይሏን በሰላም ማስከበርና ዜጎቼን አስወጣለሁ በሚል ልታንቀሳቅስ እንደምትችል ከመንግስት መውደቅ ጋር አያይዛ ስትናገር እንደነበር ይታወሳል። እንዲህ ያለው አሰራሯ የህዝብን ስነ ልቦና ለማሳት የምትጠቀምበት እንደሆነ የሚገልጹም አሉ።

ምንም ሆነ ምን በክረምት እንደሚጀመር ቀጠሮ የተያዘለት ጦርነት በድርድር ቅድመ ዝግጅት የሰላም ተስፋ ጭሮ የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቷል። ዛሬ ሌሊት ላይ ከትግራይ የወጣው መረጃ ” የአብይ ጦር” የሚሉት የኢትዮጵያውያን መመኪያ የሆነው የመከላከያ ሰራዊት አስቀድሞ በስም በተጠቀሱ አካባቢዎች ጦርነት መክሰቱን፣ ጦርነቱንም የትግራይ ሃይል እንደሚመከት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ጦርነቱን እንዲያስቆምና ለትህነግ ተዋጊዎች ወገናዊ እርዳታ እንዲያደርግ ጥያቄ በማቅረብ ትህነግ ይፋ በማድረግ ቀዳሚ ሆኗል።

መንግስት «…የሽብር ቡድኑ ወደደም ጠላም ወደ ሰላም አማራጭ እንዲመጣ ለማድረግ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳል» ሲል መግለጫ ያወጣው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ” መከላከያ እየመከተ ነው” ሲል የቀድሞው ዓይነት ወረራ እንደማይታሰብ አመልክቷል። አይይዞም ” ሆኖም ከመንግስት በኩል የቀረቡለትን በርካታ የሰላም አማራጮች ሁሉ ወደጎን በመተው የሽብር ቡድኑ ህወሃት ታጣቂ ቡድን ሰሞኑን ሲፈጽም የሰነበተዉን ትንኮሳ ገፍቶበት ዛሬ ንጋት ላይ በምስራቅ ግንባር በቢሶበር፣ በዞብል እና በተኩለሽ አቅጣጫዎች ከለሊቱ 11 ሰአት ጀምሮ ጥቃት ፈጽሟል። በወሰደዉ እርምጃም ተኩስ ማቆሙን በይፋ አፍርሷል፡፡ የፈጸመው ጥቃትም ሆነ እሱን ተከትሎ ያወጣው መግለጫ አሰቀድሞ ለትንኮሳው ሲዘጋጅ እንደነበር ግልጽ ማሳያ ነው” ሲል ሰላም ብቻ እንደሚያዋጣ አስታውቋል።

“… አሸባሪዉ የሕወሓት ቡድን በትንኮሳው ከገፋበት፤ መንግስት ሀገር የማዳን ሕጋዊ፣ ታሪካዊና ሞራላዊ ግዴታ ስላለበት እንዲሁም የሽብር ቡድኑ ወደደም ጠላም ወደ ሰላም አማራጭ እንዲመጣ ለማድረግ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳል፡፡ ይህንን ለማስፈፀም ደግሞ መንግስትና መላው የፀጥታ ሃይላችን ከነሙሉ ብቃትና ቁመናቸዉ በተጠንቀቅ ላይ ናቸው” ሲል በሁሉም ግንባር ያለው የጸጥታ ሃይል ለማንኛውም ግዳጅ ዝግጅት ላይ እንዳለ አመልክቷል።

ይህ በንዲህ እንዳለ ነው ማምሻው ላይ ትህነግ ያሰለፋቸው ከመመከት ወደ ማጥቃት ተዛውሯል የተባለውን የመከላከያ በትር መቋቋም አቅቷቸው እጃቸውን የሰጡት። ” ቁጥራቸው በርካታ ነው። ለጊዜው መዘርዘር አይቻልም። ግን እጅ ሰጥተዋል። የመታውም ሃይል ቀድሞ ከነበረው ይዞታው ሳይቀር አፈግፍጓል” ብለዋል። አያይዘውም የወገንን ሃይል ስቦ ወደ ራስ ሜዳ ለማስገባት የሚደረግ ስልት እንደንደፉ አድርገው ማውራት መጀመራቸውና ይህም ከንቱ እሳቤ አንደሆነ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ላለፉት አስር ወራት አንድም ቀን ሳይተኛ ስልጠና ላይ የኖረ ፕሮፌሽናል ተዋጊ መሆኑም መታወቅ እንዳለበት ገልጸዋል።

“ጦርነት ለትግራይ ወጣቶች የባህል ጨዋታ ነው” በሚል ጭራሹኑ ሽንፈት እንደማይገጥማቸው የሚናገሩት የትህነግ ደጋፊና አባላቱ ሲጠብቁት የቆዩት ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ እስካሁን የድል ወሬ አላወሩም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሰሞኑንን ከወጣቶች ጋር ሲወያዩ አማርጩ ንግግርና በንግግር ሰላም ማውረድ ብቻ እንደሆነ ገልጸው ” ጦርነት ተሞከረ፣ ተሞከረ አልሆነም ወደፊትም አይሆንም። በልመና ክላሽ ብቻ ሳይሆን የሚረዷቸውን ቢያሰልፉ ማሸነፍ አይቻልም” ማለታቸው አይዘነጋም።

በአብዛኞች ዘንዳ ሰላም ተስፋ እንዳለው ቢታሰብም፣ ጦርነት እንደሚጀመር ምልክቶች ስለነበሩ፣ የትግራይ ህዝብ ችግርም እየተባበሰና በትግራይ አጎራባች ያሉ ወገኖችም የችግሩ ሰለባ በመሆናቸው መንግስት ይህን አጀንዳ ዘግቶ ወደ ልማት ፊቱን እንዲያዞር የሚወተውቱ በርካታ ነበሩ።

Exit mobile version