ጌታቸው ረዳ “አጋጣሚውን በመጠቀም ወልቃይትን በሃይል እናስመስል የሚል ቡድን አለ” አሉ፤ ትህነግ “270 ሺህ ጦር አለኝ” አለ

በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለውን ግጭት እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ ወልቃይትን ጨምሮ የትግራይን ግዛቶች በሃይል እናስመስል የሚሉ ወገኖች መኖታቸውን አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አደረጉ። መንግስት ከሰጠው የክልሉ በጀት ለ270 ሺህ ተዋጊ ሃይል ቀለብ ማቅረባቸውንም አመልክተዋል።

“አቶ ጌታቸው የሰጡት መግለጫ በአማራ ክልል የሚካሄደው ግጭትና ጦርነት ልዩ ተልዕኮ ባላቸው ሃይሎች የተጠለፈ ነው” የሚለውን የስጋት ትንታኔ እንደሚያጠናክር ዜናው በታተመበት ስር አስተያየት የሰጡ ገልጸዋል። ዶክተር ደብረጽዮን ይህን አጋጣሚ መጠቀም ይገባል የሚል አቋም ከያዙት ወገኖች መካከል መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ጥሪ ማቅረባቸው አይዘነጋም።

“በኃይል ማስመለስ ይቻላል። ነገር ግን የፕሪቶሪያው ስምምነት ከእነ ብዙ ችግሮቹና እጥረቶቹ ከተቀበልን በኋላ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በፌደራል መንግሥት ዘንድ የስምምነቱ አፍራሽ ተደርገን እንዳንቆጠር መጠንቀቅ ያስፈልገናል” ሲሉ ዳግም ጦርነት የማስጀመሩ ፍላጎት እሳቸው የሚመሩት ወገን አቋም እንዳልሆነ ለማሳየት ሞክረዋል። አቶ ጌታቸው አጋጣሚውን ለመጠቀምና ዳግም የአማራ ክልልን ለመያዝ ፍላጎት አላቸው ያሉዋቸውን ክፍሎች ማንነት አልገለጹም።

መንግስት የትግራይ ክልል እስከ ታች ባሉ መዋቅሮች በአግባቡ ማስተዳደርና መቆጣጠር ካልቻለ ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት እንደሚቸገር መግለጹን ይፋ አድርገዋል። ለዚህም ይመስላል የክልሉ ግዚያዊ አስተዳዳር መዋቅር እንዲሁም የክልሉን የፖሊስ ኃይል፣ የግለሰቦች አገልጋይ እንዳይሆን ከላይ እስከ ታችኛው እርከን ድረስ መልሶ የማደራጀት ስራ መጀመሩን አቶ ጌታቸው ይፋ ያደረጉት።

“አስገራሚ” በተባለው፣ አንዳንዶች ደግሞ “ኑዛዜ” ያሉት የአቶ ጌታቸው መግለጫ ሌላም ሚስጢር ይፋ አድርጓል። ከትግራይ ወደ አማራ ክልል መሳሪያ እየገባ እንደሆነ የስፍራ ስም ጠቅሰው ተናግረዋል። ተውናያኖቹን በይፋ በስም ባይጠሩም አኩራፊዎቹና ” የጊዜያዊ አስተዳደሩን አናውቅም” ብለው የትግራይ የበታች መዋቅሮችን የተቆጣጠሩት ሃይሎች ስለመሆናቸው ግን ጥርጥር የለውም። ካፈንጋጮቹ ወገን የጦር አመራሮች ጋር ግንኙነት ያላቸው የአማራ ክልል አመራሮችና የፓርቲ ሰዎች ስለመኖራቸው ቀደም ሲል ሲገለጽ እንድነበር ይታወሳል። ይህ ረጅም የትህነግ እጅ በአማራ ክልል ውስጥ በሚፍለገው ደረጃ ሰላም እንዳይሰፍን ማድርጉን ” ሽንፍላው ብአዴን” በሚል የሚጠሩት ደጋግመው ሲገልጹ እንደነበርም ይታወሳል።

በተደጋጋሚ ብአዴን ውስጥ ሲላላኩ የኖሩ አመራሮች ተጠራርገው እንዲወጡ ሲያሳስቡ የነበሩ በወረራው ወቅት መረጃ ሲሰጡና ክልሉን በተለያዩ መውቅሮች በሃላፊነት እየመሩ በተግባር ለትህነግ ሲሰሩ የነበሩትን ሳይቀር በስም ይጠቅሱ ነበር። እነዚሁ ወገኖች አሁን አቶ ጌታቸው ከሰጡት ምስክርነት ጋር አያይዘው ይህንኑ የቀድሞ ጥቆማቸውን ያጎላሉ።

“በክልሉ የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር የፖለቲካ ድክመት ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው፤ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ውድቀት የሚመኙ የተደራጁ ግለሰቦች አሉ” ሲሉ ተሰምተዋል። አክለውም ” ከትግራይ ባህር ዳር፤ ደሴና ሰመራ የጦር መሳሪያ የሚያዘዋውሩ ሰዎች መኖራቸውን ግልጽ አድርገዋል። በተለይ ባህር ዳር መጠቀሷ ጉዳዩን “እነማን፣ ከማን ጋር ሆነው” የሚለው ጉዳይ ማጣራትና መመርመር እንደሚያሻው አመላካች ሆኗል። እንደተባለው ሽያጭም ከሆነ ማን ነበር ክፍያውን የሚፈጽመው? በማን በኩል? የትና እንዴት? ዱባይ ወይስ … የሚሉ በርካታ ጉዳዮች ዜናው ከተሰማ በሁዋላ የሚነሱ ጥያቄዎች ሆነዋል። አገር ለቀው የወጡ ሰዎችም በዚህ ጉዳይ ሊመረመሩ እንደሚገባ አመላካችም ሆኗል።

አቶ ጌታቸው ከአስተዳደሩ እንዳፈነገጡ የሚገልጿቸው ወገኖችን በዝርዝር ይፋ ባያደርጓቸውም፣ በያዙት አቋም የሚታወቁ የትህነግ ቁልፍ ሰዎች በመሆናቸው፣ “መሳሪያ ንግድ ይባል” እንጂ መልኩ ሌላ እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ይግለጻሉ። በባህር ዳር የነበሩና ከጦርነቱ በፊት የነበረውን እንቅስቃሴ የተከታተሉ ቀደም ሲል ” አጋጣሚውን ተጠቅመን የትግራይን ግዛቶች እናስመልስ” የሚሉት ወገኖች አማራ ክልል ካለው እንቅስቃሴ ጀርባ መኖራቸውንና መሳሪያ በገፍ ሲያቀርቡ እንደነበር ጠቁመው ነበር። እነዚህ ወገኖች በአማራ ክልል በተነሳው ጦርነት ውስጥ ጉዳዩ ያልገባቸው በቀናነት የሚታገሉ የሚመስላቸው እንዳሉም አመልክተው ነበር።

ትህነግ አማራና ኦሮሞን በሕዝብ ደረጃ ወደ ለየለት ጦርነት ለማስገባት በከፍተኛ ደረጃ ሲነቀሳቀስና የጥላቻ ትርክት እየፈጠረ ሲያሰራጭ እንደነበር የሚገልጹ ” አሁን የሚደረገውን ጦርነት የኦሮሞና አማራ አድርገው የሚያቀርቡት ወገኖች የትህነግ ዓላማ አስፈጻሚ እንደሆኑ የሚያሳይ ነው። ኦሮሞና አማራ ከተዋጉ የትኛውን አገር ነው ማስተዳደር የሚቻለው። ይህ አገር የማፍረስ አጀንዳ እንጂ ሌላ አይሆንም” በሚል ረጋ ብሎ ለማሰብ አሁንም እንዳልረፈደ ይገልጻሉ።

See also  የፌዴሬሽን ምክር ቤትየወልቃይት ጠገዴና የራያ የማንነት ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ እየሠራ ነው

አማራ ክልል የተጀመረውን ውጊያ የሚመሩት፣ የሚቀሰቅሱትና የሚያደራጁ መሆናቸውን የሚገልጹ በአብዛኛው ትህነግ በፈጠረው ብአዴን ውስጥ ታዛዥ የነበሩ እንደሆኑ የሚናገሩ፣ አንዳንዶቹም ኢህአዴግ በኦሮማራ ትግል ሲዝል አቶ በረከት ያደራጇቸው እንደሆኑ ያስረዳሉ። ይህ አማራ መስሎ ከትህነግ ጋር የሚመጋገበው ሃይል ጦርነቱ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር እንደሚደረገ ወይም ” ከኦሮሙማ” ጋር እንደሆነ አድርጎ ሰፊ ቅስቀሳ ማካሄዱና ጥላቻ በስፋት ማሰራጨቱ አገሪቱን ማንም ተጠቃሚ ወደማይሆንበት ወደ ለየለት ብጥብጥ ለማስገባት እንደሆነ ያመለክታሉ። ይህ ደግሞ የዛሬው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ ” ሲኦልም ገብተን ቢሆን እናፈርሳታለን” ሲሉ የፎከሩትን፣ የትግራይ ሃይሎች የሳይበር ሰራዊት መሪዎችም ” ኢትዮጵያ ስትፈርስ ከማየት በላይ የሚያስደስት ነገር የለም” ሲሉ በይፋ የተናገሩትን የከሸፈ ፍላጎታቸውን ዳግም በሌላ ስትራቴጂ ለማስፈጸም የተስማሙ መኖራቸውን ማሳያ እንደሆነ ይገልገልጻሉ።

አቶ ጌታቸውም በትግራይ በተለይ ከጾታዊ ጥቃት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን የፈጸሙት “በኢትዮጵያ መንግሥት የተጋበዙ የውጭ ኃይሎች ናቸው” ሲሉም የኤርትራና የአማራ ሃይሎችን ስም ሳይጠሩ ከሰዋል። ትናንት የትህነግ አፈ ቀላጤ የነበሩት አቶ ጌታቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጨምሮ ሲከሱ እንደነበር አይዘነጋም። አሁን ግን የአገር መከላከያ ሰራዊትን ነጻ አድርገዋል።

ወረዳዎች እና በታችኛው እርከን ያሉ አስተዳደራዊ መዋቅሮች የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል እንዳይሆኑ የተደራጀ ንቅናቄ እንዳለም በግልጽ ያስረዱት አቶ ጌታቸው፣ የፌደራል መንግሥት ለትግራይ የአንድ ዓመት በጀት ብቻ መድቦ በመጀመሪያ ዙር 3 ቢሊየን ብር መቀበሉን አስታውቀው ሃሜት የነበረውን ጉዳይ ገልጸውታል። “ከ3 ቢሊዮኑ ለሲቪል ሠራተኛው የከፈልነው የአራት ወር ደሞዝ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ ለሲቪል ሰራተኛው ሳናወጣ ከ270 ሺህ በላይ ወታደሮችን ምግብ ማቅረብ ስለነበረብን ነው” ሲሉ አሁንም ትግራይ 270 ሺህ ከክልሉን በጀት የሚቀለብ ሰራዊት እንዳላት ተናግረዋል።

ለዚህ ይመስላል ሰለ ወልቃይት ሲናገሩ “በሃይል ማስመለስ እንችላለን” ብለዋል። ይሁን እንጂ አቶ ጌታቸው ወቅታዊ ሁኔታውን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም በትግራይ በኩል ያሉ ግዛቶችን በኃይል እናስመልስ የሚሉ ወገኖች እንዳሉ ይፋ አድርገዋል። “በኃይል ማስመለስ ይቻላል። ነገር ግን የፕሪቶሪያው ስምምነት ከእነ ብዙ ችግሮቹና እጥረቶቹ ከተቀበልን በኋላ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በፌደራል መንግሥት ዘንድ የስምምነቱ አፍራሽ ተደርገን እንዳንቆጠር መጠንቀቅ ያስፈልገናል” ብለዋል።

ትህነግ ሰራዊት እያደራጀ እንደሆነ የሚያውቁ ” ጥንቃቄ ያሻል። መንግስትና የአገር መከላከያ ወልቃይትን ዘግተው ከፈተኛ ዋጋ ከፍለዋል። መከላከያ ላይ የተጀመረው ዘመቻና ስም ማጥፋት ዓላማው ሌላ ነው። ትህነግ ጦርነት ሲጀምር ‘የአብይ ጦር” ይለው ነበር። አሁን ደግሞ የኦሮሞ ጦር እየተባለ ሰራዊቱን ለመበተን የሚሞከረው ሙከራ ከማንም በላይ የአማራ ክልልን የጎበዝ አለቃ መፈንጫና የያዘውን የሚያሳጣው ይሆናል” በተደጋጋሚ እየመከሩ ያሉት።

እነዚሁ ረጋ ብለው ከሚያስቡት ወገን የሆኑ እንደሚሉት የአማራ ክልል እንደ ሽንፍላ ከትህነግ ተጽዕኖ ሊጸዳ አልቻለም። ትህነግ አማራ ክልል ውስጥ ያለው ትብትብ ከፍተኛ መሆኑንን በተደጋጋሚ የሚገልጹ፣ አማራ ክልል ጠንካራ አመራር እንዳይወጣለት የሚደረገውም ለዚሁ እንደሆነ ያሰምሩበታል።

አንዳንድ የትህነግ ደጋፊዎች ” በየትኛውም ወቅት ጦርነት ይከፈታክ። የተነጠቀውም መሬታችን ይመለሳል” በሚል ይህን አጋጣሚ የመጠቀም አዝማሚያ መኖሩን እንደሚጠቁሙ የገለጹ አቶ ጌታቸው ይህን ማረጋገጣቸው ለአማራ ክልል ህዝብ ከበቂ በላይ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ተናገረዋል። አክለውም ትህነግ የውስጥ ችግሩን ተቋቁሞ ወደዚህ ዳግም ወረራ ከመራ ተወደደም ተጠላም የአማራ ክልል ግንባር ቀደም መከታው የአገር መከላከያ ሰራዊት መሆኑ ታምኖ ከወዲሁ እርምት እንዲወሰድ ህዝብና የገባቸው አደባባይ ወጥተው ግፊት እንዲፈጥሩ መክረዋል። ይህ ካልሆነና ትህነግ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ያሰበውን የማሳካት ዕድል ቢያገኝ መንግስትንም ሆነ የአገር መከላከያን ተጠያቂ ማድረግ እንደማይቻል የሳይበር አርበኞችና ሳንቲም ለቃሚ ዩቲይበሮች ሳይቀሩ አስቀድመው ሊረዱት እንደሚገባ አስጠንቀቀዋል።

See also  የኦነግ ሸኔ ሃይል መፈረካከሱን መከላከያ አመለከተ፤ ሸኔ በአጋር የትህነግ ሚዲያዎች አላስተባበለም

አቶ ጌታቸው ያፈነገጡ ሃይሎች መኖራቸውን ሲያስታውቁ አያይዘው በክልሉ ለሶስት ቀናት በተከታታይ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ”  የሦስት ቀን ሰልፍ የሚባል ነገር የለም፤ አመፅ ካልሆነ በስተቀር” ሲሉ ሰልፉ ዓላማው ሌላ እንደሆነ ተናግረዋል። አሁን ባለው የምርጫ ቦርድ ህግ መሰረት ፓርቲዎቹ የቤት ውስጥ ስብሰባ ከማድረግ በቀር ሌላ መብት እንደሌላቸውም አመልክተዋል።

ከበታች የአስተዳደር መዋቅ ተቀባይነት ያጣው የአቶ ጌታቸው አስተዳደርን ለመርዳት የፌደራል መንግስቱ ብዙም ፍላጎት እንዳሌለው አቶ ጌታቸው መግለጻቸው፣ የትግራይ ፖለቲካ እሳቸው እንዳሉት በድክመት የሚገለጽ ሳይሆን በክሽፈት የሚመደብ ሆኗል። በርካቶች እንዳሉት ” ኮሽ የሚል ነገር የለም” ይባልባት የነበረችው ትግራይ አሁን ላይ ለማዕከል የማይገዙ መዋቅሮች የበዙባት፣ ህይግና ደንብ የነጠፈባት፣ ከምንም በላይ ጸጥታና የተረጋጋ ኑሮ የመከነባት ክልል መሆኗ ጦርነት እየተጎሰመበት ላለው የአማራ ክልል ትልቅ ትምህርት እንደሚሆንና ከወዲሁ ነገሪችን ወደ ሰላማዊ አቅጣጫ መመለስ አማራጭ እንደሌለው ማሳያ ሆኗል።

አማራ ክልል የተጀመረው ጦርነት ከሰፋ የትሀንግ አድፋጭ ሃይል “ተወሰደኝ” የሚለውን መሬት ለማስመለስ ከተነሳ፣ በመላው ኢትዮጵያ ምን ሊከሰት እንደሚችል ማሰብ አዳጋች እንደማይሆን የገባቸው እየወተወቱ ነው። ኢትዮጵያ ሰፊ የመከላከያ ሃይል መገንባቷን የሚገልጹ፣ ይህ ሃይል በቀላሉ የሚናድና እንደ ደርግ ዘመን በሰርጎ ገብ አለቆቹ ሴራና ጉቦ የሚፈርስ ባለመሆኑ ይህን ሃይል ጠብቆ አገርን ባለችበት ማስቀጠሉ ከጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም የዘለለ ፋትዳ እንዳለውም ያመልክታሉ።

ምንም እንኳን ትህነግ ዳግም ወደ ጦርነት የሚመለስበት አጋጣሚ የሳሳ ቢሆንም፣ 275 ሺህ ጦር ጥቅማ ጥቅሙ ሲጓደልበት ራሱን በራሱ ማዘዝ ሊጀምር እንደሚችል ግምት አለ። አቶ ጌታቸውም ስጋታቸውን ፊትለፊት በዚህ ደረጃ ባይገልጹም አዝማማኢያው መኖሩን ጠቁመዋል። ይህ ቀለብ ብቻ የሚቆረጥለት ሃይል እስከመቼ በቀለብ ክፚ ብቻ ይቆያል? የሚለው ሲታሰብ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል። በመላው አገሪቱ ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሳሪያ መሰራጨቱን በመግለጽ ኢትዮጵያ ወደ ሰላማዊ መንገድ እንድትመለስ ከመከላካያና ፊደራል ፖሊስ በቀር ያልተፈቀደላቸው ኢመድበኛ አደረጃጀቶች እንዲከስሙ የተጀመረው ስራ ያለ ልዩነት በትክክል እንዲተገበር ከመግፋት በቀር መቃወሙ እንደማይጠቅም እነዚሁ ወገኖች ይመክራሉ።

አሜሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን አሕመድ “ኢትዮጵያ” ማለታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘታቸውን ተከትሎ ወዲያውን ለማስወገድ ለጀመረችው ዘመቻ ከፊት ያሰለፈችው ትህነግ “በጦርነቱ ተወሰደበኝ” የሚለውንና ቀደም ሲል የአማራ ርስት የነበሩትን አካባቢዎች መልሶ እንዲሰጠው ከፍተኛ ጫና እይፈጠረች መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል። ይህ በጉሮ በኩል የሚደረግ ከፍተኛ ጫና እንዳለ ሆኖ አሜሪካ በሌላ ገጽታዋ የሰላማዊ ዜጎች መብት ተቆርቋሪና አስከባሪ ሆና ዳግም ብቅ ብላለች። ወራሪና ተወራሪን ሳትለይ ” የአማራ ሃይሎች ከምእራብ ትግራይ ውጡ” ስትልና በጄኖሳይድ ስትከስ የነበረችው አሜሪካ ይህንኑ ዘመቻዋን በትመድ፣ በመብት ተሟጋቾች፣ በአማርኛ በሚሰራጩት ጭምር በዓለም ታዋቂ ሚዲያዎች፣ በአውሮፓ ህብረትና ተጸእኖ ፈጣሪ በሆኑ ተቁማት ሁሉ ታካሂድ እንደነበር የቀርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

በኢትዮጵያዊያን እምቢተኛነት ዓላማዋን ማሳከት ያልቻለችው አሜሪካ አሁን ላይ የያዘቸው አቋም ወላቅይት ለትግራይ እንዲመለስ ጫና በማድረግ መንግስትንና ህዝብን በተለይም ከአማራ ጋር ማጣላት ነው። ይህ ዛሬ አሜሪካ የምታራምደው የትህነግ የቆየ መርህ፣ የኢትዮጵያ ብሪክስ መግባትና ወደ ጸጥታው ምክር ቤት በድምጽ የመሳተፍ ጫፍ ላይ መድረሷ የፈጠረው ብስጭት ውጤት እንደሆነ የሚገልጹ አሉ።

በጥቂቶች ዓላማና ግብ ሳያስቀምጥ፣ ዙሪያውን ሳይቃኝ ማንም እየተነሳ በብሄር ሽፋን በጩከት የሚነዳው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለታሪካዊ ጠላቶች ምቹ ከመሆኑም በላይ አገሪቱን ዋጋ እያስከፈል፣ ኢኮኖሚዋን እየጎዳ፣ ህዝቡን ምሬት ውስጥ እዲከትና እንዲበሳጭ በሚያደርግ ቅስቀሳ ታጅቦ በፍጥነት እየገሰገሰ መሆኑ የበርካቶች ስጋት ሆኗል።

See also  ሸኔ ሸበልና ዋራባቦ የሚባሉ ይዞታዎቹን ተነጠቀ፤ ከሸኔ ወገን የተባለ ነገር የለም

የትግራይ መፈረካከስና፣ ሰፊ የወታደር አቅም፣ አሁን ላይ አማራ ክልል የተነሳው አለመረጋጋትና ግጭት አንድ ላይ ተዳምሮ ወደ ለየለት ምስቅልቅል እንዳያመራ ለመጠንቀቅ ከአቶ ጌታቸው መግለጫ የሚልቅ ማስጠንቀቂያ እንደሌለ የሚገልጹ “ሳይቃጠል በቅጠል” አስብሏል። አለያ ለጸጸትም ጊዜ ሊኖር እንደማይችል የበርካቶች ግምት ነው።

ችግሮች መኖራቸው የማይካድ ቢሆንም ቸግሮችን ለመፍታት የተመረጠው አካሄድ ከፍተኛ አደጋ ይዞ መጥቷል። በስማ በለውና በአካኪ ዘራፍ የሚነዳ ሁሉ ኢትዮጵያ የተሰራችበትን የፌደራል አወቃቀር በመረዳት፣ ይህንኑ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ወደ ሰከነና ሁሉን ወደሚያሳትፍ ለውጥ ማዘንበሉ ብቻ እንደሚያዋጣ የብዙዎች አገር ወዳዶች እምነት ነው። የሚያውቁትን አፍ ያዘጋው የኢትዮጵያ የስድብና የፍረጃ አመጽ አገር አልባ እንዳያደርገን የሚሰጉ ደግመው ደጋግመው እርጋታን እየተማጸኑ ነው።


Leave a Reply