Site icon ETHIO12.COM

የጣልቃ ገብነት አባዜ፣ የኢትዮጵያዊነትና የምዕራባዊነት ፍጥጫ

TPLF is anyways the foster child of Egypt and the west
ብርሃኑ ሌንጂሶ

በሶስተኛ ደረጃ የወያኔ ፍቅር ነው። ወያኔ ምዕራባውያን በኢትዩጵያ ላይ የጫኑት ኢ-ቀጥተኛ ቀኝ ገዥ ነው። ይህን ለማድረግ የ40 አመታት ኢንቨስትመንት አፍስሰውባቸዋል። TPLF is anyways the foster child of Egypt and the west

State Minister – Irrigation Development at Ministry of Irrigation & Lowlands – Ethiopia,

የሀሳብ ምግብ – ነጻ አሳብ – በብርሃኑ ሌንጄሶ – የመስኖ

የኢትዮጵያዊነትም የምዕራባትም ዋነኛ ምሰሶ ይመስለኛል ጣልቃ ገብነት (Interventionism)። ምዕራባዊነት ጣልቃ ገብነትን በማራመድ ላይ የተገነባ ስነልቦና ስሆን ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ላይ የተገነባ ስነልቦና ነዉ። ምዕራባዊነት ጠቅልሎ መግዛት ይፈልጋል ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ነፃነትና ሉሃላዊነት ያቀነቅናል። ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት የምዕራባዊነት አንት ተስስ ነዉ ማለት ይቻላል።

ምዕራባዊነት:-

ምዕራባዊነት ቋሚ ትርጉምና ገጽታ ያለው ፅንሰሃሳብ ባይሆንም ከግሪኮ-ሮማን ስልጣኔ ጋር የሚገናኝ የተሻለ ስልጣኔና ዘመናዊነት ጋር የተሳሰረ ፅንሰሃሳብና የስነልቦና ውቅር እንደሆነ ድርሳናት ያስረዳሉ። የፅንሰ ሃሳቡ ውልደት ከክርስቶስ ልደት በፊት በ479 እንደሆነም ይነገራል። በዚህ ጊዜም ግሪክ (The Greek city states) ከፐርሺያን ኤምፓየር (Persian empire) ጋር የተዋጉበት ወቅት እንደነበር እና ግሪኮች በጦርነቱ እጅግ በጣም የተበለጡ ቢሆንም ትልቁን የፐርሺያን ኤምፓየር ማሸነፍ የቻሉበት እንደነበር ይታወቃል። በአቀማመጥም የግሪክ ሲቲ ስቴት ወደ ምዕራቡ የፐርሺያን ኤምፓየር ደግሞ በምስራቅ አቅጣጫ የነበረ ሲሆን በጦርነቱ የግሪክ አሸናፊነት የምዕራባውያን አሸናፊነት ሆኖ ተወሰደ።

ከዚህ በተጨማሪ ግሪኮች ራሳቸውን የሰው ፍቅር ያላቸው የሰለጠኑ አድርገው ሲያዩ በአንፃሩ ፐርሺያኖችን ደግሞ አምባገነንና ኋላቀር አድርገው ያዩ ነበር። ከዚህ እንደምንረዳው ምዕራባዊነት ስለምዕራባውያን ጥሩነት ብቻም ሳይሆን ምዕራባውያን ላልሆኑ ህዝቦች መጥፎ ግንዛቤን ይዞ የተፈጠረ ፅንሰሃሳብና የልቦና ውቅር መሆኑን መጥቀስ ይቻላል።

ከዚያም በዘለለ ምዕራብ አውሮፓ ከህዳሴ (Renaissance) ከመገለጥ ዘመን (Enlightenment) ከሳይንስ አብዮት (Science revolution) እና ከኢንዱስትሪ አብዮት (industrial revolution) ጋር በተገናኘ መልኩ ራሳቸውን የአለም ብርሃን አድርገው የማየት ከዚያም አልፈው የዘመናዊነት፣ የልማት፣ የእድገት፣ የስልጣኔ፣ የዴሞክራሲ እና የሰው ልጅ ሁሉ መብት ተሟጋች አድርገው የዓለምን እይታ ለመቀየር ጥረት አድርገዋል። በዕድገት አስተሳሰብም ዘመናዊነት ምዕራባዊነት (የምዕራባውያንን ዕሴቶች መቀበል እና መላበስ) አውሮፓዊነት ነው የሚሉ ፀሃፊዎችም አሉ።

ምዕራባዊነት በአስተሳሰብ ደረጃ ራስ ተኮር (Ethnocentric) ነው። እኛ የተሻለ ዕውቀት ያለን ህዝቦች ነን፤ እኛን የሚመስሉ እኛን የሚከተሉ የተሻለ ይሆናሉ፤ እኛን የማይመስሉና የማይከተሉ ደግሞ ጥሩ ያልሆነ እና መሻሻል ያለባቸው ስለሆኑ እኛ ጣልቃ እየገባን የማሻሻል፣ የማሰልጠን፣ የማስተካከል ሃላፊነትም መብቱም አለን ብለው ያስባሉ።

በዚህ አተያይ ነው የምዕራብ ሃገራት አፍሪካን ለመከፋፈል የወሰኑት። በዚህ አተያይ ነው የቅኝ አገዛዝ የተጀመረው። እውነታው ግን ለራሳቸው ዕድገት የሚሆን ሃብት ለማፈላለግ ነበር። በባሪያ ንግድ ጉልበት በመበዝበዝ የተሻለ ጥቅም ስላገኙ አሁን ደግሞ ሌሎች ንብረቶችን በማግኘት መበልፀግ ነው ኣላማቸው። ይህንን አተያይ በኋላ በሌሎች የአለማችን ህዝቦች ላይ ለመጫን ከፍተኛ ጥረትና ሙከራ አድርገዋል። አለመከተልም በአማራጭ ደረጃ እንዳይኖር ለማድረግ ብዙ ጥረዋል። በኋላም በፖለቲካ አስተሳሰብ ሌሎች ላይ ለመጫን አሁንም ድረስ ሙከራዎች የቀጠሉ ስለመሆኑ ማንሳት ይቻላል።

ምዕራባውያን ዛሬም ድረስ የራሳቸውን ባህልና የፖለቲካ አስተሳሰብ ካላቸው ሃገራት እንደ ቻይና፣ ሩሲያና ኢራን ጋር የሚያደርጉት እሰጥ ገባ ከዚሀ “እኛ የተሻለን ነን፤ እኛን የማይመስሉ ሁሉ የተሻሉ አይደሉም ስለዚህ ጣልቃ እየገባን ጫና እያደረግንባቸው የተሻሉ እንዲሆኑ እናደርጋለን ከሚለው አስተሳሰባቸው የመነጨ ስለመሆኑ መጥቀስ ይቻላል።

ኢትዮጵያዊነት:-

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ልክ እንደ ምዕራባዊነት ቋሚ የሆነ ትርጉምና ገፅታ ባይኖረዉና በጊዜ ህደት የሚይዘው የመሬት ስፋትና ህዝብ የተለዋወጠ ቢሆንም የዛሬው የኢትዮጵያ ገፅታና አሁን ያለው የኢትዮጵያዊነት ሰነልቦና በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተቀረጸ ስለመሆኑ የታሪክ ድርሳኖች ይጠቁማሉ። አሁን ላለው የኢትዮጵያዊነት ገፅታ፣ ስነልቦናና ማንነት አስተዋፅኦ ካደረጉ ነገሮች መካከልም ዋነኛው ሊባል የሚችለው ይሄው ከላይ ያነሳነዉ የምዕራባውያን አስተሳሰብ ስነልቦናና ጣልቃ ገብነት ነው ማለት ይቻላል።

የኢትዮጵያውያንን የስነልቦና ውቅር ከገነቡ ታሪካዊና ማህበራዊ ክስተቶች መካከል እንደ ጣልቃ ገብቶ ንብረቱን ለመዝረፍ፣ ማንነቱን ደፍጥጦ የራሱን ለመጫን የመጣውን ወራሪ መክቶ መመለሱ ነው። ይህን ለማድረግም ኢትዮጵያውያን ከጫፍ ጫፍ በመንቀሳቀስ በአንድነት ቆመው መመከታቸው ተመልሶ የኢትዮጵያውያን የማንነትና የስነልቦና መሰረት መሆን ችሏል።

ይህ የኢትዮጵያውያን የአሸናፊነት፣ የነፃነት እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ስነልቦና ደግሞ ምዕራባውያን ለራሳቸው ከሰጡት ማንነትና ስልጣን ጋር በእጅጉ የሚጋጭ ነው። ይህ ግጭት ነው ምዕራባውያን ኢትዮጵያን በአይነቁራኛ እንዲመለከቷትና እንዲከታተሏት ያደረገው።

ከዛም ባለፈ ኢትዮጵያ ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ምሳሌ በመሆን ታነሳሳብናለች የሚለውም እውነታ አለ። በተጨማሪም የኢትዮጵያ መልክአምድራዊ አቀማመጥ የተለየ ትኩረት እንድትስብም ያደርጋታል። ከዚህ አንፃር በቀጥታ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት ቀላል ስላልነበረ በተለያዩ አማራጮች አካባቢያዊና ውስጣዊ ችግሮችን በመደገፍና በማቀጣጠል ችግሮቹን ለማባባስ ያልተቋረጠ ሙከራዎችን አድርገዋል። አሁንም ተመሳሳይ ሙከራዎችን እያየን ነው።

ባጠቃላይ ምዕራባዊነት ከቆመባቸው ምሰሶዎች ዋነኛው “እኛ የተሻልን ነን፤ የሰው ልጆች ሁሉ የተሻሉ የሚሆኑት እኛን ከመሰሉ እና እኛን ከተከተሉ ብቻ ነው፤ ስለዚህ እኛን እንዲሆኑ ጣንቃ እየገባን እንቀይራቸዋለን” የሚል ነው። ከዚህ በተቃራኒ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ “አልገዛም፤ በእኔ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አትችሉም” የሚል ጠንካራ አቋም ላይ የተገነባ ስነልቦና ነው። እነዚህ ሁለት እሳቤዎች የሚፃረሩ፣ የሚጋጩ ናቸው።

በሁለተኛ ደረጃ ኢትዮጵያ ነፃነቷን አስጠብቃ በመቆየቷ የብዙ ቅኝ የተገዙ ሃገራት የነጻነት ምሳሌ ሆና ትታያለች። ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያ የተሻለ ነገር ካሳየች ሌሎች ቅኝ የተገዙ ሃገራት የኛን ጣልቃ ገብነት ላይቀበሉ ይችላሉ በማለት ከፍራቻ የመነጨ ጫና ኢትዮጵያ ላይ ለማሳረፍ ወስነዋል። በአጠቃላይ የምዕራባውያን የኢትዮጵያ እይታ በፍራቻ የተሞላ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራና የህዝብ ድጋፍ ያለው መሪ ከመጣ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን አፍሪካውያንን በማስተባበር በመለወጥ ለኛ ጣልቃ ገብነት የማይመች አህጉር ይፈጥራሉ ብለው ይፈራሉ። ከዚያ ባለፈ ደግሞ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ጠንካራና በአንፃራዊነት የተረጋጋች ሃገር ናት። የምዕራቡ ሃገራት ከመካከለኛው ምስራቅ የሚያገኙትን ጥቅም በቀጣይነትም ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ ትልቅ ሚና አላት። ከዚህ አነፃርም የምዕራባዊያንን ጥቅም ብቻ በትዕዛዝ ለማስጠበቅ የቆመ ደካማ መሪ እንዲኖር ይፈለጋል።

የምዕራባዊያን ለወያኔ ፍቅር ለለውጥ ፍራቻ ለምን?

ከላይ ባስቀመጥናቸው የጥቅም ፍላጎቶች፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ እና የጠንካራ ሀገር ፍራቻና ባጠቃላይም በአፍሪካ ውስጥ ባላቸው የጠንካራ መሪ ፍራቻ የተነሳ በየሃገሩ ለእነሱ ተላላኪ መሆን የሚችሉ ዕውቀትና የህዝብ ድጋፍ የሌላቸውን መሪዎችን ለማፍራት ብዙ ስራዎችን ይሰራሉ ምዕራባውያን። ወያኔ በዚህ መንገድ ወደ ስልጣን የመጣ ቡድን ነበር። ወደ ስልጣንም የመጡት አንዳንድ ፀሃፊዎች እንደሚሉት “The Cohen coup in Ethiopia” በሚባል መንገድ ነው። ከዚያ በኃላ ወያኔዎች የምዕራባውያንን ስነልቦና የመላበስ ባህር በሰፊዉ አሳይተዋል።

ምዕራባውያን እኛ የተሻልን ተፈጥሮ አለን፣ የተሻለ ዕውቀትና ስልጣነ አለን ስለዚህ ጣልቃ እየገባን ማሰልጠን ጫና እየፈጠርን ማሻሻል አለብን ብለው ያምናሉ። በተመሳሳይ መልኩ ወያኔዎች እኛ የተሻልን ነን ኢትዮጵያን እኛ ካላስተዳደርን ህዝቡ ይባላል ይላሉ። ከዚያም አልፈው ኢትዮጵያን ካላስተደአደርናት እናፈርሳታለን ለማፍረስም ገሃነም ድረስ እንዘልቃለን ይላሉ።

ምዕራባውያን በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ ያሳዩት ጫና፤ ለማድረግ የሞከሩትም የጣልቃ ገብነት ሙከራ ጠንከር ያለ ነው። አዲስ ግን አይደለም። አሜሪካ ብቻ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ጫና አድርጋብናለች፤ አስጠቅታናለች። በጣሊያን ወረራ ጊዜ ማዕቀብ ጥላብናለች፣ ዚያድ ባሬን አስወግታናለች፣ ወያኔን ደግፋ ሃገራችንን ለብዙ መከራ ዳርጋለች። ጫናዉ አዲስ ባይሆንም ከሌላው ጊዜ በተለየ የጠነከረበት ምክንያት ሶስት ይመስለኛል፣

የመጀመሪያው የነበራቸው የጠንካራ መንግስት ፍራቻ ጋር ባለእጅጉ የሚገናኝ ነዉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ምዕራባውያን አፍሪካ ውስጥ ማየት የሚፈልጉት ዓይነት መሪ አይደለም። በምርጫ ሲመጣ ደግሞ በባሰ የሚፈሩት አይነት መንግስት እንደሚሆን ይታወቃል።

በጎረቤት የአፍሪካ ሃገራት መካከል እሱ የፈጠረው ስምምነት በዚህም ምክንያት የሰላም ኖቤል ተሸላሚ መሆኑ ብዙ የምዕራባውያን መሪዎችን ረብሿል። The potential of strong government in Africa is a western disease.

ሁለተኛው ምክንያት የግብፅ ምክንያት ነው። ግብፅ የምዕራብ ሃገራት ኢትዮጵያ ላይ ጠንከር ያለ ጫና እንዲያሳርፍና እንዲያዳክም ውትወታዎችን ታደርጋለች። የምዕራብ ሃገራትም ከግብፅ ጋር ባላቸው የጠነከረ ወዳጅነትና በአረቡ አለም የነሱን ጥቅም እንደምታስከብር ሃገር ተሰሚነቷ ትልቅ ነው።

በሶስተኛ ደረጃ የወያኔ ፍቅር ነው። ወያኔ ምዕራባውያን በኢትዩጵያ ላይ የጫኑት ኢ-ቀጥተኛ ቀኝ ገዥ ነው። ይህን ለማድረግ የ40 አመታት ኢንቨስትመንት አፍስሰውባቸዋል። TPLF is anyways the foster child of Egypt and the west

ዛሬ ምዕራባውያን ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት ጫና እና የጣልቃ ገብነት ሙከራ የእነዚህ የሶስቱ እንዲሁም የሌሎችም ታሪካዊና ስነልቦናዊ ጉዳዩች ድምር ውጤት ነው። ይሁን እንጅ ኢትዮጵያኖች ከፋፍሎ ለመግዛት ለመጣ ባንድ ላይ ቆመዉ በመመከት ረጅም ታሪክ አለን። ጣሊያኖች አፄ ዮሐንስን ለማሸነፍ ብሎ አፄ ሚኒለክን ዘመናዊ መሳሪያ አስተጥቀዋል። በኃላ ግን አፄ ሚኒልክ ያንኑ መሳሪያ ተጠቅሞ ጣሊያኖችን አሸነፈ። በዉስጥ ጉዳያችን ላንስማማ እንችላለን ከዉጭ የሚመጣብንን ጥቃት በጋራ በመመከት ግን ታሪክ የማይሸረዉ አንድነት አሳይተናል።

አሁንም እናሳያለን!

CC: Selamawit Kassa

Exit mobile version