Site icon ETHIO12.COM

የህወሓት የሽብር ሰነድ ሲገለጥ…

አሸባሪው ህወሓት ሀገርን የሚያፈርስበትና የኢትዮጵያን ህዝብ በመበቀል ለመከራ የሚዳርግበት አዲስ ሰነድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር ገብቷል። አሁን እያካሄደ ያለው ውጊያም የዚሁ አካል ነው።

ፅሁፉ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ በማሳጠርና መታየት ያለባቸው ነጥቦች ብቻ ቀርቧል።

ከሰነዱ የተወሰዱ ዋና ወና ሃሳቦች

# ስለ ሰላም አማራጮች ያላቸው አቋም:

• የሰላም አማራጭ በሚል ስትራቴጂው፣ በአንድ በኩል ጊዜ ወስዶ ለአጠቃላይ ዘመቻ ለመዘጋጀት በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት ሰላም ፈላጊ አይደለም ብሎ ለዓለም ማህበረሰብ ጥላቻ ለማሰተጋባት እንዲያግዘው በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የጀመረው አካሄድ በፍፁም የማያዋጣና የትግራይ ህዝብን ጥቅም የማያስከብር መሆኑን ያስቀምጣል።

የአፍሪካ ህብረትን የማደራደር ሚና

አሸባሪው ህወሓት ለሰላም ምንም አይነት ዝግጁነት እንደሌለው በተጋለጠው ሰነድ ላይ የአፍሪካ ህብረትን የማደራደር ሚና እንደማይቀበለው ገልጿል።

በሰነዱ ላይ በጦርነት ሂደት ውስጥ የመረጃ ልዕልና ለማግኘት እና በርካታ ኃይሎችን ከጎንህ ለማሰለፍ ከሚያስችሉ ሁኔታዎች አንዱ፣ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ችግሮችን በሰላም ለመፍታት ቁርጠኝነት እንዳለህ አስመስለህ እራስህን ማቅረብ መሆኑ ሊረሳ አይገባም ሲል አሸባሪው ህወሓት ጠቅሷል።

በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የተጀመረው አካሄድ በፍፁም የማያዋጣ እንዳልሆነ ቡድኑ ገልጿል።

በአደራዳሪነት የተመረጡት የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ ለዐቢይ አህመድ ባላቸው ፍቅርና እንክብካቤ ሚዛናዊነታቸው ጎደሎ ሁኖ አግኝተነዋል ሲል አሸባሪው ህወሓት በሰነዱ አስፍሯል።
ስለሆነም በዚህ አይነት አደራዳሪ ኃይል የሚቀርብ የድርድር ነጥብ የትግራይን ህዝብ ፍላጎት የሚያሟላ ባለመሆኑ የቀረበውን የሰላም አማራጭ የሽብር ቡድኑ እንደማይቀበለው ገልጾ፤ የሰላም ዋስት እና የሚረጋገጠው በቀረበው የሰላም አማራጭ ሳይሆን በክንዳችን ብቻ መሆኑን በፅኑ እናምናለን ብሏል።

• የውስጥ ትግላችን በማገዝ የሚንቀሳቀሱ እንደ ኦነግ የመሳሰሉ አጋሮቻችን እንዲሁም በተለያዬ የዓለም መአዘናት የሚገኙ የትግራይ ዲያስፖራና ዓለም አቀፍ አጋዦቻችንና አጋሮቻችን በዚህ ጊዜ የተሳካ ጥምረት በማድረግ ወደ አዲስ አበባ በምናደርገው እንቅስቃሴና ዘመቻ ከጎናችን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ጋር በዝግ ባደረገው ውይይት አረጋግጧል።

የአማራ ሃይል የተመለከተ

• ይሄ ፅንፈኛ የአማራ ተስፋፊ ሃይል በትግራይ ላይ ካሳየው ጫፍ የወጣ ጥላቻ በላይ፣ በክልሉ ያገኘውን ሕዝባዊ ተቀባይነት ሽፋን በማድረግ እና ጠንካራ ቅንጅት በመፍጠር ከአማራ ክልል መንግሥት የሚስተካከል አቅም መፍጠር በመጀመሩ የዐቢይ አስተዳድር በወሰደው ርምጃ በተወሰነ መልኩ መዳከም ታይቶበታል።

አሁንም ግን የዚህ ሃይል አመራሮች በህዝብ ጉያ ተደብቀው ስለሚገኙ ምቹ ሁኔታ ካገኙ ዳግም ሃይል አግኝተው መነሳታቸው አይቀርም። ይህ ሁኔታ የትግራይ ሰራዊት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀምበት የሚገባ ሲሆን፣ ይሄ ሃይል ራሱን “ፋኖ” ብሎ በመጥራቱ የተወሰደበት ርምጃ በርከት ያሉ የአማራ ታጋይ ሃይሎች ከዐቢይ ጎን ተሰልፈው ለመንቀሳቀስ ያላቸውን እንዲቀንስ አድርጎታል። ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራት የተፈጠረውን መሻከርና ክፍተት የበለጠ እንዲከር ማድረግ ይገባል።

አፋር ክልልን በተመለከተ

• የዓፋር መንግሥት የእርዳታ ተደራሽነት በመቆጣጠር በየጊዜው ምክንያት የሌለው ግጭቶች በመፍጠር በአዋሳኝ አከባቢዎች በዘላቂነት ሰላም እንዳይሰፍን በማድረግ በአከባቢው የሚኖሩ ተጋሩ በስጋት ውስጥ እንዲሆኑ አድርጓል። በአወል አርባ የሚመራ ግጭት ቀስቃሽ ቡድን ከዐቢይ አስተዳድር በሚሰጠው አድናቆትና ቁጥር የሌለው የትጥቅ እገዛ አይኑ የታወረ፣ ጆሮው የተደፈነ በመሆኑ፣ ትግላችን በሚያግዙ የዓፋር የነፃነት ታጋዮችና ቤተሰቦቻቸው አፈናና ግድያ እየፈፀመባቸው ይገኛል።

ኤርትራን በተመለከተ

• ይሄ ፍፁም አምባገነን የሆነ የኤርትራ መንግሥት፣ አሁንም እንደ ትላንት ዋነኛ የሰላምና የትግራይ ህዝብ ነፃነት ጠላት መሆኑ ዳግም እያሳየ ይገኛል። ይሄ ጨቋኝ መንግሥት ባጭር ጊዜ መፍትሄ ካላገኘ ሕዝባችንን ወደ ማያቋርጥ ጦርነትና መከራ ዳግም ለማስገባት የሚችል ስጋት በውስጡ የያዘ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ የዐቢይ ታማኝ አመራሮችና ደጋፊዎች በክልላቸው ውስጥ በምናደርገው እንቅስቃሴ የሚያግዙንን የውስጥ አካላት እያደኑ ማጥቃት ቀጥለዋል።

ከኦነግ ጋር ያለን ግንኙነት

• ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አመራር ጃል ሚልኬሳ ጋር በሚስጢር ባደረግነው ውይይት፣ ባጭር ጊዜ አመራራቸው ወደሚመች አከባቢ ወይም ወደ አጎራባች ሃገሮች ስልታዊ ማፈግፈግ የሚያደርጉበት ሁኔታ እንዲመቻች፣ እንዲሁም የመከላከል አቅምና ዝግጁነት የሌላቸው የሰራዊቱ አባላት ከተቻለ ዩኒፎርማቸውን ጥለው ወደ ሕዝባቸው እንዲቀላቀሉና እንዲደበቁ ካልተቻለም ለመንግሥት ሃይሎች እጃቸውን መስጠት የተሻለ አማራጭ እንደሆነ አንስቶ ነበር።

• በወለጋ ያለው ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አመራር መካከል ጃል ራሣና ጃል ቃንቄ በፋሺስት ዐቢይ ከተከፈተባቸው ከበባ ለመውጣት አስቸኳይ ዘዴ ዘይደው መመርያ በመስጠት ወደሚመች ምስጢራዊ ቦታዎች እንዲንቀሳቀሱ የተደረገው ሙከራ የተሳካ ነው። በዚህ አግባብ በአንዳንድ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አመራሮች መካከል የትግል ስልት ልዩነት ቢኖርም በአስቸጋሪ ሁኔታ ሁነንም የመረጃ ልውውጣችን እና መተጋገዛችን የሚቀጥል ይሆናል። የዚህ ግንኙነት ዋነኛ መሰረት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለአዲስ አበባ ካላቸው ቅርበትና ለሚታሰበው ዘመቻ ከፍተኛ ትግል በማድረግ ድል ሊያስመዘግቡ የሚችሉ በመሆናቸው ላይ ካለን መተማመን የሚመነጭ ነው።

• ይሁን እንጂ አሁንም የፋሺስት ዐቢይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳን አገዛዝ ሽባ በማድረግ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው የመጨረሻ የትግል ምዕራፍ ላይ የቅርብ አጋዦች እነዚህ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በመሆናቸው ሊስተካከሉ የሚገባቸው እና ባለፈው ግምገማ የታዩ ክፍተቶች ታርመው ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እንዲዘጋጁ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ይቀጥላል …

Exit mobile version