Site icon ETHIO12.COM

360 አማራ ክልል የደረሰ ምርት እንዳይሰበሰብ ቅስቀሳ እያካሄደ ነው

ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ በማለት በሃይል የትግራይን ሕዝብ አግቶ የያዘው ትህነግ እንደሚደጉመውና ከግብጽ ጋር ዝምድና እንዳለው የሚነገርለት 360 የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ በአማራ ክልል የደረሰ ምርት እንዳይሰበሰብ ቅሰቀሳ መጀመሩን ተቆርቋሪዎች አመለከቱ። የአዲስ አበባ ወጣቶች በቅንጅት ወቅት ድምጻ መሰረቁን መቃወማቸውን ተከትሎ በየጎዳናው ሲረሸኑ ” ሊቦች ናቸው” በማለት በተገደሉት ላይ መግለጫ ሲሰጥ የነንበረው ኤርሚያስ ለገሰና የኢህአዴግ የአዲስ አበባ ወጣቶች መሪ የነበረው ሃብታሙ አያሌው ናቸው ቅስቀሳውን እያካሄዱ ያሉት።

ቅሰቀሳው የተጀመረው የምዕራብ ጎንደር በከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ምርት እኒሰበሰብ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የቀን ሰራተኞች እንደሚፈለጉ ያወጣውን ማስታወቂያ ተከትሎ 360 በውክልና ዕህል እንዳይሰበሰብ መቀሰቀሱን በይፋ ከተቃወሙት መካከል ጌታቸው ሽፈራውና ቹቹ ኧባቸው ይገኙበታል። ጽሁፉ መረጃ አካቶ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ምዕራብ ጎንደርን ጨምሮ ሰፊ እርሻ መሬት ያላቸው አካባቢዎች ሰብል የሚሰበስብ ሰራተኛ ማስታወቂያ ሲያወጡ ይህ የመጀመርያቸው አይደለም። ማህበራዊ ሚዲያ በማይታወቅበት ጊዜ በኢቲቪና አማራ ቲቪ ጭምር በሚሊዮን የሚቆጠር ሰራተኛ እንፈልጋለን ብለው ማስታወቂያ ሲያስነግሩ ኖረዋል። ባለፈው አመት በዛ ቃውጢ ጦርነት ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ በርካታ ሰብል የሚሰበስብ ሰራተኛ በማስታወቂያ ጠርተዋል። በሌላ አካባቢ ያለው አርሶ አደር የራሱ ሰብል እስኪደርስ ለአንድና ሁለት ወር ሰርቶ እንደሚመለስ ይታወቃል። በቋሚነት በርሃ ወርዶ የሚሰራ፣ ካምፕ ተሰርቶለት በአካባቢው የሚከርም ሞልቷል። የሰብል ስብሰባን ብቻ ስራቸው አድርገው በቆላማ አካባቢዎቹ የሚኖሩ በርካታ ወጣቶች አሉ። ለረዥም አመታት ዩኒቨርሲቲዎች ከሚቀበሉት ወጣት በላይ የቋራ፣ የመተማ፣ አርማጭሆ፣ ወልቃይት ጠገዴ አካባቢዎች ሰብል የሚሰበስብ ወጣት ይቀበላሉ። በርካታ ህዘብ የሚሳተፍበት ስለሆነ አዲስ ገቢዎቹ ጎፈር፣ የለመዱት ሳሉግ እየተባሉ ይጠራሉ። በቆላማ አካባቢዎች በሰራተኞች የተመሰረቱ ከተሞች አሉ።

ከ1950 በኋላ የትግራይ ወጣት ሳይቀር ተከዜን ዋኝቶ ተሻግሮ ሰርቶ ወደ ትግራይ ይመለስ ነበር። በዚህ ወቅትም ከደቡብ ኢትዮጵያ ድረስ ለሰብል ስብሰባ የሚመጡ ወጣቶች አሉ። አይደለም ሰብል ስብሰባው ሙጫና እጣን ለቀማው በሺህ ለሚቆጠር ወጣት የስራ አድል ይፈጥራል። ሰብል ለመሰብሰብ ብቻ አይደለም እያንዳንዱ አራሽ አካባቢውን የሚጠብቁለት ሚሊሻዎች ይቀጥራል። ስራ አስኪያጅ ይቀጥራል። አንዳንዱ ካምፕ ከትንንሽ ሰፈሮች አይተናነስም። አንድ አርሶ አደር በርካታ ሰራተኞች ይዞ ይከርማል። አንድ አርሶ አደር ለስድስት ወር ያህል ለአንድ የሰራተኞች አስተባባሪ ከፍተኛው እስከ 120 ሺህ ብር ድረስ እየከፈለው ነው። በወር 20 ሺህ ብር ማለት ነው። ምግብና መጠለያ ተችሎት። አንድ ሚሊሻ ለስድስት ወር እስከ 80 ሺህ ብር እየተከፈለው ነው። በወር ከ10 ሺህ ብር በላይ ነው። ምግብና መጠለያን አሰሪው ችሎ ጎን ለጎን የተወሰነ ሄክታር ይታረስላቸዋል። ሚሊዮን ሰራተኛ ወደ አካባቢው የሚሄደው እንዲህ አዋጭ ስለሆነ ነው።

ይህ ሆኖ እያለ ታዲያ ለሰብል ስብሰባ ማስታወቂያ ሲወጣ የመከላከያ ምልመላ አስመስሎ መጀመርያ ያቀረበው ትህነግ ነው። ከእሱ ጋር የሚሰሩና በሱዳን በኩል ሰርገው እየገቡ ህዝብን ለማጥቃት ሲጥሩ የከረሙ ተላላኪዎችም ቀስቅሰውበታል። እነዚህ አካላት ሰብል ሲያቃጥሉ፣ የአርሶ አደሩን ከብት ሲገድሉ የሚታወቁ ናቸው። አሁንም የሰብል ስብሰባ ማስታወቂያውን ሆን ብለው በሀሰት ወታደራዊ ምልመላ አስመስለው የሰሩበት ህዝብ ሰብሉን እንዳይሰበስብ ነው። አካባቢውን ወርረው ሰብሉን ማቃጠል ባይችሉ ሳይሰበሰብ እንዲቀር የሀሰት ዘመቻ ከፍተዋል። ኢትዮ 360 የሚባል ሚዲያ ይህን የህወሓት አጀንዳ እያራገበ ይገኛል። ይህን ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሆን ብሎ ካላስተላለፈ በአስቸኳይ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል። ህወሓት የአማራን ባለሀብት የሰሊጥ ነጋዴ ወዘተ እያለ ሲፈርጅ ከርሟል። አሁን ሰሊጡ እንዳይሰበሰብ ሲቀሰቅስ 360 ተደርቦ በህዝብ ጥቅም ላይ ዘምቷል።

ለሰራዊት አፈሳ ቢፈለግ ወጣቱ ያለ በየከተማውና በየቤቱ ነው። ምዕራብ ጎንደር ድረስ መሄድ አይጠበቅበትም። ምዕራብ ጎንደር ማንንም አታልሎ ወደ ጦር ግንባር የሚያስገባ አይደለም። አርሶ አደሩ ብቻውን ሱዳንን ቀጥ አድርጎ የያዘ የእነ ባሻ ጥጋቡ ቀዬ ነው። ኢትዮጵያም አንድ ሚሊዮን ምልምል አያስፈልጋትም።

ምዕራብ ጎንደርንና አካባቢውን የማያውቁ ይህን ያህል ሰራተኛ ምን ሊሰራ ነው ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ። በህወሓት አላማ ወይንም በምቀኝነት ግን ሰብል እንዳይሰበሰብ ሊቀሰቅሱ ባልተገባ ነበር። ኢትዮ 360 በጦርነቱ ምክንያት መሬት ጦሙን አደረ ሲል ከርሞ፣ አሁን ለሰብል ስብሰባ የሰራተኛ ቅጥር ሲወጣ የህወሓትን አጀንዳ እያራገበ በህዝብ ላይ ሌላ ጦርነት ከፍቷል። በአንድ ዞን ሚሊዮን የስራ እድል ሲፈጠር እንዲስተጓጎል እየሰሩ ነው። ይህን የተናገሩ ሰዎች በግብታዊነት ከሆነ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። አርሶ አደር ሰብል እንዳይሰበስብ ቅስቀሳ ማድረግ በህዝብ ላይ ጦርነት መክፈት ነው። ሚሊዮን ወጣት ስራ እንዳይሰራ መቀስቀስ ወንጀል ነው። ያፈጠጠ የህዝብ ጠላትነት ነው።

“ዉግንናችን ለማን ነዉ?” ቹቹ አለባቸው

ምዕራብ እና ሰ/ምዕራብ ጎንደርን፣ማለትም ከቋራ እስከ ሁመራ ካወቅኩት ጊዜ ጀምሮ በየአመቱ በተለይም በመኸር ስብሰባ ወቅት በሚሊየን የሚቆጠር የቀን ሰራተኛ ከመላዉ ኢትዮጵያ ጥሪ ይደረግለታል። እኔ በምመራዉ ወረዳም ጭምር የተለመደ አሰራር ነበር።

ይህ የሚሆነዉ በአብዛኛዉ ጦርነት ባልነበረበት ወቅት ሲሆን ጦርነት በነበረበት ወቅትም የተለመደ ነበር። ለምሳሌ ከኤርትራ ጋር በጦርነት በነበርንባቸዉ ወቅትም ይህ አሰራር የተለመደ ነበር። በዚህ ወቅት ጥሪዉን ተቀብሎ ለቀን ሰራ የሚዘምተዉ ሀይል እጅግ ብዙ ነበር።

ስለዚህ የአሁኑን ጥሪ ከጦርነት አፈሳ ጋር አያይዞ መመልከት ተገቢነት የለዉም። በተለይም ለአራሹ ገበሬ ጉዳት እንጅ ጥቅም የለዉም። ለገበሬ የሚቆረቆር ማንኛዉም ግለሰብ የገበሬ ምርት እንዳይሰበሰብ አይሰራም። ከዚህም በላይ ወቅቱ የአማራ ክልል ወጣቶች በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መከላከያን በመቀላቀል ላይ ባሉበት ሁኔታ እንዲህ አይነት ሀሳብ መሰንዘር ትርፉ ትዝብት ብቻ ይመስለኛል።

ይልቁንስ የልማት ጥሪዉ ለወጣቶቻችን፤ ሆነ ለገበሬዎቻችን እንደሚጠቅም አድርገን እንምከርበት።

በነገራችን ላይ የትግራይ አክቲቪስቶች ትግራይ “ዲያፍራ” አይደለችም ሲሉ እሰማለሁ። በፌደራል መንግስቱና በወያኔ መካከል እየተካሄደ ያለዉን ጦርነት ለመቋጨት ከሞላ ጎደል “የዲያፍራ” ን( Diafra) ሞዴልን እየተከተልን ይሆን? ጥያቄ ነዉ። ከሆነስ ወያኔ በተለይም መሪዎቹ በየትኛዉ በር ይሾልኩ ይሆን? ለሁሉም በተለይም በወልቃይት ጠገዴ እንዲሁም ስ/ጎንደር መወጠሩ ይሻላል።

በመጨረሻም ወጣቶች በቅድምያ መከላከያን ተቀላቀሉ። በተለያየ ምክንያት መከላከያን ለመቀላቀል ያልቻላችሁ ደግሞ የልማቱን ጥሪ ተቀብላችሁ ወደ ጎንደር ምዕራባዊ ቀጠና ትመሙ።

ድል ለመከላከያና በሱ ስር ለሚመሩ ሁሉም የፀጥታ ሀይሎቻችን!!!

Exit mobile version