Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ የዛሬ መረጃ

🇪🇹 መረጃ 1 ከኢፕድ የተገኘ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገራድ ዊል አየር ማረፊያ ሲደርሱ በሶማሌ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ኡመርና በሌሎች የክልሉና የፌዴራል ከፍተኛ አመራር አካላት ደማቅ አቀባበል ተደርገውላቸዋል።

🇪🇹 መረጃ 2 ከኢፕድ የተገኘ

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በጅግጅጋ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይገኛል። ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከውይይቱ በኋላ የተለያዩ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

🇪🇹 መረጃ 3 ከኢፕድ የተገኘ

የእንጂባራ ዩኒቨርስቲ ግቢውን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ አስተማሪ የሆነ ሥራ ሠርቷል

የእንጂባራ ዩኒቨርሲቲ ግቢውን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ አስተማሪ የሆነ ሥራ ሠርቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ዩኒቨርስቲው ግቢውን በማሣመር የሠራውን አኩሪ ሥራ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ችግር በመፍታትና በዓለም ደረጃ የሚወዳደሩ ልሂቃንን በማፍራት ይደግማል ብዬ አምናለሁ ብለዋል።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=409691601354301&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 4 ከኢፕድ የተገኘ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎትን አሰጀምሯል

ኩባንያው በአዲስ አበባ እና በአዳማ በ 100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የዳታ ማዕከል ገንብቷል፤ በዚህ ዓመት በሁለቱም ከተሞች ሁለት ተጨማሪ የዳታ ማዕከል እንደሚገነባ አስታውቋል። በቀጣይ አሥር ዓመታት 8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በማፍሰስም የዘርፉን ተጠቃሚነት የማሻሻል ዕቅድ እንዳለውም አመልክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት መጀመር ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን የብልጽግና ጉዞአችን ሞተር አድርገን የመንቀሳቀሳችን ማሳያ ነው ብለዋል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በበኩላቸው፤ የሳፋሪ ኮም በኢትዮጵያ አገልግሎት መጀመሩ ቀጠናዊ ትስስርን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።

🇪🇹 መረጃ 5 ከኢፕድ የተገኘ

በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የሰላም ንግግር ከሀገር ሉዓላዊነትና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓት አንፃር መታረም የሚገባቸው ጉዳዮች ን የወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ ይፋ አድርጎጓል።

🇪🇹 መረጃ 6 ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘ

ከናይጄሪያ፣ ኳታር፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከሳውዲአረቢያ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት ተደረገ

በካናዳ ሞንትሪያል እየተካሄደ በሚገኘው 41ኛው ዓለም አቀፍ የሲቪል አቬዬሽን ጉባኤ ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከናይጄሪያ፣ ኳታር፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከሳውዲ አረቢያ የትራንስፖርት ሚስትሮች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡

በውይይቱም ዘርፉ የሚፈጥረውን መልካም የሀገራት ትስስር ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

🇪🇹 መረጃ 7 ከኢፕድ የተገኘ

“አፍሪካ ለአፍሪካውያን” የተሰኘ አሕጉራዊ ኩነት በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

አፍሪካ ለአፍሪካውያን” የተሰኘ አህጉራዊ ሁነት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጸዋል። ኢትዮጵያ በሁነቱ ላይ “አህጉራዊ አንድነትን በማጠናከር ለጋራ ጥቅም መነሳት ይገባል” የሚል አቋሟን ታንጸባርቃለች ተብሏል።

🇪🇹 መረጃ 8 ከኢዜአ የተገኘ

ሚኒስቴሩ በመሬት አስተዳድር ዘርፍ ተማሪዎችን ለማሰልጠን ከስድስት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ

መስከረ የግብርና ሚኒሰቴር በመሬት አስተዳደር ዘርፍ በአጭር፣በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ድግሪ መርሃ ግብር ተማሪዎችን ለማሰልጠን ከስድስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር የስምምነት ፊርማ ተፈራርሟል።

የተፈረመው ስምምነት በዘርፉ የሚያስፈልገውን የሰው ሃይል እጥረት ለመቅረፍ ያለመ ሲሆን የመሬት አስተዳደር ዘርፉን ለመምራት በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ዉስጥ ከ138 ሺህ በላይ ባለሞያ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

🇪🇹 መረጃ 9 ከኢፕድ የተገኘ

የደብረ ብርሃን አንኮበር አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ 72 በመቶው ተጠናቋል

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘው የደብረ ብርሃን አንኮበር አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ 72 በመቶው ስራ ተጠናቋል፡፡ የፕሮጀክቱ ቀሪ ስራዎች በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው ተብሏል።

በአሁን ላይ 42 ኪሎ ሜትር ከሚረዝመው አጠቃላይ የመንገድ ግንባታ ውስጥ 30 ኪሎ ሜትር አስፋልት የማንጠፍ ስራ ወይም ከአጠቃለይ ስራው ውስጥ የፕሮጀክቱ 72 በመቶው ተጠናቋል፡፡

ለፕሮጀክቱን ግንባታ አንድ ቢሊየን 623 ሚለየን 194 ሺህ 217 ብር በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=409549494701845&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 10 ከኢፕድ የተገኘ

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመጠገን የተደረገው ጥናት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመጠገን እየተከናወነ ያለው ጥናት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ገለጹ።

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን የሚያስቃኝ አውደ ርዕይ ”ላሊይበላ በእምነት የታነጸ” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እንጦጦ ፓርክ ተከፍቷል።

🇪🇹 መረጃ 11 ከኢፕድ የተገኘ

በተቋማትና ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው የሳይበር ጥቀት እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የዜጎችና የተቋማት ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ከማደጉ ጋር ተያይዞ በተቋማትና በቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት እየጨመረ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታወቀ።

🇪🇹 መረጃ 12 ከኢፕድ የተገኘ

በ2015 ዓ.ም የሰላም፣ደህንነትና የጸጥታ ጉዳይ በቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል

በ2015 ዓ.ም የሰላም፣ደህንነትና የጸጥታ ጉዳይ በቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ።

ሰላም፣ደህንነትና የጸጥታ ጉዳይ በቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት ከሚሰራባቸው ጉዳይ መሆኑንም ገልጸዋል።

መስከረም 30 በሚደረገው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ መክፈቻ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አጠቃላይ የ2015 በጀት አመት ስራዎችን በዝርዝር የሚያቀርቡ ይሆናል።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=409493118040816&id=100069403920568

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio

Exit mobile version