Site icon ETHIO12.COM

በትግራይ የክልልነት ጥያቄ እየተነሳ ነው

“መንግስት በምርጫ ያልቆመና አማጺ” በሚል የሚጠራው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ እንደሆነ የሚገልጸው ትህነግ እንዳፈናቸው በመጥቀስ የክልልነት ጥያቄ ለማንሳት ዝግጅት እያጠናቀቁ ያሉ የድርጅት አመራሮች መኖራቸው ተሰማ። የፌደሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ምላሽ ያለው ነገር የለም።

የኢትዮ12 የአዲስ አበባ ዘጋቢ ከቅርብ የመረጃ ምንጮቹ ሰምቶ እንደዘገበው ለጊዜው በስም ያልተዘረዘሩ አውራጃዎች በአንድነት የክልልነት ጥያቄ ለመጠየቅ ዝግጅት እያጠናቀቁ ነው። እንደመረጃው በአድዋ ውስን ሃይሎች መበደላቸውን የሚጠቅሱ ናቸው ይህን ጥያቄ ለማንሳት እንቅስቃሴ የሚያደርጉት።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄው ህጋዊ ሆኖ ከመጣና ከፈቀደ፣ ግንባር በፈጠሩት አካላት አውራጃ የሚኖረው ህዝብ ከተስማማ ትህግራይ ለሁለት ትከፈላለች። ምን አላባትም አሁን ምዕራብ የሚባለው ክልል አንድ ክልል ሊሆን ይችላል።

በቅርቡ በቀይ መስመር ፕሮግራም ቀርበው አስተአየታቸውን የሰጡ የራዕይ ፓርቲ መሪ አቲ ሊላይ አካባቢ ጠቅሰው ጨፍጫፊና ተጨፍጫፊ ወገኖችን ዘርዝረው ካስረዱ በሁውላ ” አጼ ዮሃንስ ሃውላታቸው እንዳይቆም ተከልክሏል፤ በቅርቡ የመለስን አፍርሰን የልጃችንን የአጼ ዮሓንስን ሃውልት እናቆማለን” ሲሉ ተደምጠዋል።

በተደጋጋሚ ስፍራ ለይተው እየጠሩ የተፈናቀሉ፣ ንብረታቸውን የተቀሙ፣ የተዋጡና ማንነታቸውን የተቀሙ ወገኖቻቸው ነጻ እንደሚወጡም አስታወቀዋል። የአቶ ሊላይ ንግግር ከክልልነት ጥያቄው ጋር ስለመያያዙ በግልጽ ባይጠቆምም የመረጃ ምንጮቹ ትግራይን ቢያንስ ሁለት ቦታ የሚከፍል የክልልነት ጥያቄ ለማቅረብ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የደረሰው ነገር ስለመኖሩ ለማረጋገጥ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የፓርላማ አባል ” በይፋ የተሰማ ነገር የለም። ግን ጥያቄው አይነሳም ማለት አይቻልም” ብለዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች የክልልነት ጥያቄ እየተነሳ ብጥብጥና ጉዳት ሲደርስ በትግራይ በገሃድ የክልልነት ጥያቄ ቀርቦ አያውቅም። አልፎ አልፎ ከሚነሳው የአውራጃና የዞን ጥያቄ ውጪ በትግራይ አሃዳዊ አመለካከት ነበር።

የትህነግ ደጋፊዎችና አባላቱ፣ እንዲሁም ይህን ዓላማ የሚያራምዱትን ” የብልጽግና ተላላኪ” የሚሉ ወገኖች በጥቅል ይህ ሊሆን የማይችል ቅዠት እንደሆነ፣ ትግራይ አሁን ላይ አሳቧ አገር የመሆን እንጂ የመበጣጠስ እንዳልሆነ ባገኙት አጋጣሚዎች የሚያስተጋቡት አቋማቸው እንደሆነ የሚታወቅ ነው። እንደውም ኤርትራ ደጋማው ክፍልና የወልቃይትን አካባቢ አካሎ “ታላቋ ትግራይ” እንደምትገነባ በዕምነት ሲነገር መስማትም የተለመደ ነው።

Exit mobile version