Site icon ETHIO12.COM

እየተገኘ ያለውን ወታደራዊ ድል በፖለቲካዊ ስራ ማፅናት ያስፈልጋል!

እኔና አንዳንድ በተለይም የአማራ ልጆች፤ በዚህ ጦርት ዙሪያ እንዲህ አይነት ምክረ-ሀሳቦችን ስንሰነዝር፤ የብልጽግና አመራ፤ ደጋፊ፤ ወይም ልዩ ተጠቃሚ ስለሆን አይደለም፡፡ በፍጹም አይደለንም፡፡ እኔና መሰሎቸ እንዲህ የምንብከነከነው፤ ወያኔ ተሳክቶለት በዚህ ጦርት አገራችን ከፈረሰች፤ ቲንሽም ብትሆን በየጃችን ያለው ነገር ሁሉ ከንቱ እንደሚቀር በደንብ ስለገባን ነው፡፡ ጦርነቱ የሚያስከትለው አሉታዊ ውጤት በፒፒ ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ቢሆን ኖሮ፤ ይሄንን ያክል ባልደከምን ነበር፡፡ ይሄንን የምለው አንዳንድ ወገኖች ለሀገር ሲባል የሚከፈልን ዋጋ ከቁስ ጥማትና ፍላጎት ጋር ለማያያዝ ስትሞክሩ ስለምታዘብ ነው፡፡ የቁስ ጥማትንም ቢሆን ማርካት የሚቻለው ኢትዮጵያ አገራችን በሰላም ውላ በሰላም ካደረች ብቻ ነው፡፡ ሁላችንም በዚህ መርህ እንመራ፡፡ የኢትዮጵያ ሰላም ውሎ ማደር ትርፍ ባናገኝ እንኳን ቢያንስ በእጃችን ያለውን ሁሉ አያሳጣንም፡፡

Chuchu Alebachew – ነጻ አስተያየት

1. ፈር መያዥያ

አሁን ጦርቱ በደረሰበት ደረጃ ሁነን ነገሮችን ስንገመግም የኃይል ሚዛኑ ተዛብቷል ብሎ መናገር ይቻላል፡፡ ይሄም ማለት ካሁን በፊት በተደጋገሚ ለማለት እደሞከርኩት፤ ባለፈው ጦርነቱ በቆመበት ጊዜ የመንግስትም ሆነ ወያኔ ወታደራዊ ቁመና ከሞላ ጎደል በአቻነት ደረጃ የሚታይ ነበር፡፡ ወያኔም እደዚህ አይነት ግምገማ ስለነበረው ነው 3ኛውን ዙር ወረራ በራያ በኩል የጀመረው፡፡ በነገራችን ላይ ወያኔ በዚይህ ግንባር ጦርነት የጀመረው የመንግስትን እና የህዝብን ትኩረት ለማዛበት እጅ፤ ዋነኛ ግቡ የነበረው ደባር ዘልቆ፤ ወደ ጎንደር አቅንቶ ወያኔ ሲዝት እንደከረመው ጎንደር ከተማን ወደ ታሪክነት ቀይሮ ወደ መተማ እና ወልቃይት በመጠምዘዝ የሁመራን ኮሪደር በማስከፈት ማእከላዊ መንግስቱን ለመጣል የሚያስችለውን ሁለንተናዊ አቅም መገንት ነበር፡፡ በህልም የቀረው እውነተኛው የወያኔ የ3ኛው ዙር የወረራ እቅድ ይህ ነው፡፡

ነገር ግን ወያኔ አንድ በውል ያልገመገመው እውነታ ነበር፡፡ ይሄውም መንግስትና ወያኔ በአቻነት ጦርነቱን አቁመው የየራሳቸውን አቅም ወደ መገንባት በተሸጋሩበት ወቅት፤ የኢትዮጵያ መንግስት መከላከያውንና ሎጅስቲኩን ከማጠናከር አንጻር ከወያኔ በብዙ እጥፍ የተሻለ ነበር፡፡ ሁላችንመ እንደምናስተውሰው፤ ጦርነቱ ቁሞ በቆየባቸው 5/6 ወራት ወያኔ በዘረኛ ፕሮፓጋንዳው አማካኝነት በርካታ የትራይ ወጣቶችን ለውትድርና መመልመልና ማሰልጠን ከመቻሉም በላይ፤ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን በውል ያልታወቀ የመሳሪያና ትጥቅ ድጋፍ አከማችቶ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ የወያኔን ልብ አሳበጠው፤ የተሳሳተ ውሳኔ ላይ እንዲደርስም አደረገው፡፡ አንዳዴ ልብህ ሲደፈን አስቸጋሪ ነው፡፡ ወያኔ እሱ ይሄንን ያክል ሲዘጋጅ፤ ከሱ በብዙ እጥፍ የበለጠ የሰው ኃይልና ሪሶርስ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ከሱ የበለጠ ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚችል እንዴት ለመገምገም እንደተሳነው ይገርማል፡፡

በአንጻሩ በእነዚያ የእፎይታ ወራት፤ የኢትዮጵያ መንግሰት ከወያኔ በብዙ እጥፍ የበለጠ አቅም ስላለው፤ ከወያኔ የተሻለ ዝግጅት ሲያደርግ እንደከረመ ለመገመት አይከብድም፡፡ የፌደራሉ መንግስት ይሄንን ያደረገው ” ለሁሉም ፌጦ መድሀኒት ነው” በሚል መርህ ተመርቶ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ይሄም ሲሆን በሁለት ምክንያቶች እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው ጉዳይ ከወያኔ ጋር የተጀመረው የሰላ ድርድር ሊሳከ ባይችል ቀጣዩ መፍትሄ ጦርት ስለሚሆን የላቀ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ ነው የሚል እምነት መያዙን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ሁለተኛው ምክያት ደግሞ ከወያኔ ጋር የተጀመረው የሰላም ድርድር ቢሳካ እንኳን፤ ኢትዮጵያ ግዙፍና ጠንካራ የመከላከያ ኃይል እድትገነባ የሚያስገድዷት ውጫዊ ምክንያቶች ስላሉ፤ግዙፍና ጠንካራ ሰራዊት የመገንባቱ አጀንዳ የሚታለፍ አልነበረም፡፡ በመሆኑም ባለፉት የተኩስ አቁም ወራት ኢትዮጵያ ወያኔ ከጠበቀውና ካሰበው በላይ ግዙፍና ጠንካራ የመከላከያ ኃይል መገንት ቻለች፡፡ ወያኔ ይሄንን ጉዳይ በደንብ ሳያጤን በጀብድ ተነሳስቶ ጦርነት በክፈቱ እነሆ በአጭር ቀናት ጊዜ ውስጥ ብቻ ለዚህ በቃ፡፡ ወያኔ ይህ የተሳሳተና ያልተጠና ውሳኔው ምን ያክል ለፀፀት እንደዳረገው የሚያውቁት የውሳኔው ፊታውራዎቹ ጀኔራሎች ናቸው፡፡

ያም ሆነ ይህ ወያኔ የከፈተውን ጦርነት ሲከላከል የከረመው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ ወደ ፀረ-ማጥቃት መሸጋገሩንና ትግራይ ውስጥ ድረስ ዘልቆ በመግባት ቢያንስ የፌደራል ወሳኝ ተቋማትን እንደሚጠብቅ ግልጽ አድርጓል፡፡ ይህ እርምጃ እዛው እንዳለ የትግራይን ህዝብ ከመከራ እደሚያላቅና የተቀላጠፈ ሰብኣዊ ድጋፍ ለማድረግም እንደሚያስችል መንግስት ግልጽ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት ከወዲሁ በርካረታ በወራሪው ኃይል ተይዘው የነበሩ የአማራ አካባቢዎችና አንዳንድ የፕሮፐር ትራይ አካባቢዎች ነጻ መውጣት ጀምረዋል፡፡ ይህ ሁኔታም በቀጣዮቹ ቀናት/ወራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡

2. ወታደራዊ ድሉ በጠንካራ ፖቲካዊ ስራ መደገፍ አለበት፡-

ሁላችንም እደምናስተውሰው በህግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት ትግራይ ውስጥ ከወያኔ ጋር የተካሄደውን ጦርነት በአጭር ቀናቶች ውስጥ ነበር ማጠናቀቅ የተቻለው፡፡ ነገርግን ሰራዊታችን ዋናውን ጦርነት በድል ካጠናቀቀ በኃለም ቢሆን ፤ ትራይ ውስጥ በቆየባቸው 8 ወራት ውስጥ ለአንድም ቀን እረፍት አላገኘም ነበር፡፡ ይህ የሆነው የትግራይን ህዝብ ከመንግስት ጎን ማሰለፍ ባለመቻሉ የመጣ ችግር ነበር፡፡ ይህ በመሆኑም ከ8 ወር በኃላ ሰራዊታችን ትግራይ ውስጥ የገጠመውን ፈተና ሁላችንም አይተናል፡፡ ከ መቶ ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተመድቦ መሰረተ ልማቱን ለመጠገን፤ በመንግስት ድጋፍ የተደረገለት የትራይ ህዝብ፤ የመንግስትን በጎ ስራ ከምንም ሳይቆጥር አብዛኛው በወያኔ ዘረኛ ፕሮፓጋንዳ ተሰልቦ ፀረ-መንግሰት አቋም ወሰደ፡፡ በዚህም በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ትግራይ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዘ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋትና ክህደት በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ተፈጸመ፡፡

አሁን ላይ መንግሰት የግድ ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነት አለብኝ በሚል መነሻነት ሰራዊቱን ወደ ትራይ ክልል ማስገባት ጀምሯል፡፡ እንደ አያያዙ ከሆነ ዳግም ትግራይን ለቆ ይወጣል ተብሎ አይገመትም፡፡ በእኔ እምነትም ቢሆን መንግሰት ወይ ሰራዊቱን ወደ ትግራይ ውስጥ ባላስገባ እንጅ፤ ካስገባ በኃላ ዳግም ትግራይን ለቆ መውጣት የሚታሰብ መሆን የለበትም ባይ ነኝ፡፡ አሁን ላይ ሁላችንም አንድ ተስፋ አለን ብየ አስባለሁ፡፡ ይሄውም መንግስትም ሆነ ሰራዊታችን ካለፈው የትግራይ ቆይታቸውና ከገጠማቸው ፈተና አንጻር ብዙ ትምህርት ወስደዋል፡፡ ለዚህ ነው ጦርነቱ የሰከነና የተረጋገ፤ ግረግርና ጩኸት የማይሰማበት ሁኖ እየቀጠለ ያለው፡፡ ስለሆነም አሁን ትግራይ ውስጥ የሚኖረው የመንግስትና የሰራዊታችን ቆይታ እጅግ የሰከነ፤ገርግርና ወከባ የማይታይበት፤ የተሻለ አመራር የሚሰጥበት፤ የትራይ መልሶ ግንባታ በፍጥነት የሚጀመርበት፤የትራይ ህዝብ እውነታውን እንዲረዳና ከመንግስት ጎን ለማሰለፍ ብርቱ ስራ የሚሰራበት፤ በአጠቃላይ ከባለፈው ስህተት ትምህርት ተወስዶ የሚከወን እንቅስቃሴ እንደሚሆን የብዙዎቻን ተስፋ ነው፡፡

ይሁን እንጅ መንግስትም ሆነ መከላከያ ሰራዊታችን ትግራይ ውስጥ ዘልቀው ሲገቡም ሆነ መሰረታቸውን እንደገና ሲያደላድሉ ፤ምንም ያክል በጎ ስራ ቢሰሩ ከብዙዎቹ የምዕራባዊ አገራትና አሜሪካ አንጻር በጎ ምላሽ አይኖርም፡፡ እነዚህ አገራት አላማቸው ሌላ ነው፤ ወያኔ በሂዎት እዲኖር ይፈልጋሉ፡፡ ስለሆነም ይህ ጦርት እንዲቆምና ወደ ድርድር እንዲገባ ብርቱ ግፊት ከማድረጋቸውም በላይ፤ ያልተጠበቁ እርምጃዎችን እስከመውሰድና ማስወሰድ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያዊያንም ይህ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል አውቀን ከወዲሁ በዚህ ልክ መዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ በተለይም አውዳሚ ክሶቻቸውን በማጋለጥና በመመከት፡፡

3. ከኛ ምን ይጠበቃል ?

ተደጋግሞ እንደተነገረው በዚህ ወቅት አገራችን የገባችበት ጦርት የህልውና ጦርት ነው፤ አገርን የማስቀጠል ወይም እንድትፈርስ የሚወስን ጦርነት፡፡ መቸም ቢሆን አንዳድ ፖለቲካዊ ልዩነቶች ያላቸው ወገኖች ቢኖሩም/ አሉም፤ ጤነኛ የሆነ አዕምሮ ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ አገሩ እንደትፈርስ ይፈልጋልለዚህም ይተባራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ስለሆነም አገሩ እንዳትፈርስ የሚፈልግ ዜጋ ሁሉ ከሱ የሚጠበቀውን ሁሉ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ ተነስቸ ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ለሀገራችን ህልውና ስንል፤ በሚከተሉት ነጥቦች ዙሪያ አትኩረን የበኩላችንነ ድርሻ አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል እላሁ፡-

1. የሎጅስቲክ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል፡፡ በተለይም ካሁን በኋላ ትግራይ ውስጥ ህዝቡ ኢኮነሚያዊ አቅሙ እስኪያገግምና ወደ ቀልቡ ተመልሶ ለሰራዊታችን ደጀን እስከሚሆን ድረስ፤ የመሀል አገሩ ሰው ትግራይ ውስጥ ድረስ ዘልቆ በመግባት ሁለንተናዊ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ ይህ ለአፍታም ሊዘነጋ የማይገባው አጀንዳ ሊሆን ይገባል፡፡

2. የተሳሳቱና በሀገር ላይ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎችን ማክሸፍ፡- ከሁሉ በፊት አንዳድ የውስጥም ሆኑ የውጭ አካት፤ከገባንበት የህልውና ጦርት ጋር አያይዘው በአገራችን ላይ የሚያነሷቸውን ወሳኝ ውንጀላዎች በውል መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በእኔ እይታ ከገጠመን የህልውና ጦርነት ጋር በተያያዘ በመንግስት/ ሀገር ላይ የሚቀርቡት ክሶች በርካታ ቢሆኑም፤ ዋና ዋናዎቹ ክሶች ግን በሦስት ተከፍለው ሊታዩ የሚችሉ ናቸው እላለሁ፡፡ እነዚህም ትግራይ ውስጥ ”ጀኖሳይድ“ ተፈጽሟል፤ የፌደራሉ መንግስት ”ረሀብን እንደ ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ አውሏል/እያዋለ ነው” ፤ የፌደራሉ መንግስት የኤርትራን ጦር ወደ የኢትጵያ እንዲገባ በማድረግ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት እንዲደፈር አድረጓል፤ስለሆነም፤ የኤርትራ ጦር ከትራይ ይውጣ የሚሉ ናቸው፡፡

በዚህ በኩል ከየራሰችን ግንዛቤ እየተነሳን ለክሶቹ መልስ መስጠት ያለብን መሆኑ እንዳለ ሁኖ፤ በተለይም በመንግስት ደረጃ ደግሞ በደንብ አርቲኩሌት ተደርገው የሚቀረጹ አጀንዳዎች ቢኖሩ የተናበበና የተሳካ አገራዊ ትግል ለማካሄድ ያመቻል ባይ ነኝ፡፡ የእነዚህ ክሶች ተጥዕኖ በገዥው ፓርቲ ፒፒ ላይ ብቻ ታጥረው የሚቀሩ አይደሉም፡፡ ውለው አድረው እንደ ሀገር ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው፡፡ ስለሆነም ሀገራዊ ምለስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ስለዚህ ከሁሉ በፊት የክሶቹን ባህሪና መነሻ በውል መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ቀጥሎ የተናበበና ሀገራዊ ምለሽ መሰጠት ነው፡፡ ለምሳሌ፡-

1. ከጆኖሳይድ አንጻር ለሚቀርበው ውንጀላ፤ እንደ ሀገር መሰጠት ያለበት መልስ ምን መሆን/ መምሰል አለበት?

2. መንግስት ረሀብን እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቅሞበታል/ እየተጠቀመበት ነው ለሚለው ክስ ምን አይነት ምላሽ ነው መሰጠት ያለበት?

3. ከኤርትራ ጋር ተያይዞ ስለሚነሳው ክስስ ምላሻችን ምንድን ነው መሆን ያለበት?

በአጠቃላይ በእኔ እምት እነዚህ ክሶች ወሳኝ፤ ከሀገር ህልውና እና ክብር ጋር የተያያዙ ስለሆነ፤ ምላሻችን የተደራጀና እንደ ሀገር ቢሆን ይሻላል እላለሁ፡፡

በመጨረሻም እኔና አንዳንድ በተለይም የአማራ ልጆች፤ በዚህ ጦርት ዙሪያ እንዲህ አይነት ምክረ-ሀሳቦችን ስንሰነዝር፤ የብልጽግና አመራ፤ ደጋፊ፤ ወይም ልዩ ተጠቃሚ ስለሆን አይደለም፡፡ በፍጹም አይደለንም፡፡ እኔና መሰሎቸ እንዲህ የምንብከነከነው፤ ወያኔ ተሳክቶለት በዚህ ጦርት አገራችን ከፈረሰች፤ ቲንሽም ብትሆን በየጃችን ያለው ነገር ሁሉ ከንቱ እንደሚቀር በደንብ ስለገባን ነው፡፡ ጦርነቱ የሚያስከትለው አሉታዊ ውጤት በፒፒ ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ቢሆን ኖሮ፤ ይሄንን ያክል ባልደከምን ነበር፡፡ ይሄንን የምለው አንዳንድ ወገኖች ለሀገር ሲባል የሚከፈልን ዋጋ ከቁስ ጥማትና ፍላጎት ጋር ለማያያዝ ስትሞክሩ ስለምታዘብ ነው፡፡ የቁስ ጥማትንም ቢሆን ማርካት የሚቻለው ኢትዮጵያ አገራችን በሰላም ውላ በሰላም ካደረች ብቻ ነው፡፡ ሁላችንም በዚህ መርህ እንመራ፡፡ የኢትዮጵያ ሰላም ውሎ ማደር ትርፍ ባናገኝ እንኳን ቢያንስ በእጃችን ያለውን ሁሉ አያሳጣንም፡፡

ድል ለመከላከያ ሰራዊታችን በሱ ስር ለሚመሩት ሁሉም የፀጥታ ኃይሎቻን!

Exit mobile version