Site icon ETHIO12.COM

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 36 ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ሊያስመጣ ነው


የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያደገ ከመጣው የደንበኞች ፍላጎት ጋር ተያይዞ ተጨማሪ 36 አውሮፕላኖችን ለማስገባት ትዕዛዝ መስጠቱን አስታወቀ::

አየር መንገዱ የመጀመሪያው ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ በረራ የጀመረበት 10ኛ ዓመት አክብሯል። በበዓሉ የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄ፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የቦይንግ ኩባንያ ተወካዮች እና ሌሎች አካላት በተገኙበት ተከብሯል::

በወቅቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለፁት፤ አየር መንገዱ እያደገ ከመጣው የደንበኞች ፍላጎት ጋር ተያይዞ ሁለት ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላንን ጨምሮ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን ሠላሳ ስድስት ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ለማስገባት ትዕዛዝ ሰጥቷል ብለዋል:: ሁለቱ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚገቡም ተጠቁሟል::

አየር መንገዱ 140 አውሮፕላኖች ውስጥም 27 አውሮፕላኖች ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች መሆናቸውን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ተጨማሪ ሁለት አውሮፕላኖች በአንድ ዓመት ውስጥ ሲገቡ የቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን ቁጥር 29 ያደርሳል ነው
https://www.press.et/?p=83808

Exit mobile version