Site icon ETHIO12.COM

መከላከያ መቀለ 15 ኪ ዙሪያ፤”ያለፈው ስህተት አይደገምም” መሪዎች

በደቡብ አፍሪካ ነጮቹን በመግለጫቸው (peac talk) የሚሉት የሰላም ንግግር ዛሬ እንደሚያበቃ በገሃድ ከመነገሩ ውጪ በዝርዝር በነግግሩ ወቅት ” ይህ ተባለ፣ ወይም ይህ ጉዳይ ተነሳ” የሚል መግለጫ ንግግሩን ይመሩታል፣ ወይም በተሳታፊነትና በታዛቢነት የመትመራው አሜሪካ የወጣ ነገር የለም። መንግስት ግብ ንግግሩን እግር በግር እየተከተለ ይፋ እያደረገው ይመስላል።

ራሳቸውን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ወይም ትህነግ የሚሉት ክፍሎች ወደ ንግግሩ ሲያቀኑ እንዲሆንላቸው በመመኘት ቅድሚያ የሚሰጡዋቸውን ጉዳዮች ይፋ አድረገው ነበር። ፕሮፌሰር ክንድያ በቲውተር ገጻቸው አስቸኳይ ተኩስ አቁም፣ ያልተገደበ እርዳታ እንዲፈቀድ፣ የኤርትራና ኢትዮጵያ ሃይሎች ከትግራይ እንዲወጡ፣ ወልቃይት ጠገዴ እንዲመለስ … የሚሉት ጉዳዮች የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ጨምረው እንዲሟሉ አስታውቀው ነበር። ቢቢሲን ጨምሮ ሚዲያዎች ይህንኑ ምኞት የፊት ዜና አድርገው ሰንብተዋል።

መንግስት አስቀድሞ “ንግግሩ ህጋዊ ዕውቅና ከሌለው አማጺ ሃይል ጋር ነው” ሲል ትህነግን ቀደም ሲል ከመንግስትነት፣ ቀጥሎ ደግሞ ከክልል መሪነት አውርዶ በአማጺ ስም እንዲሰየም ለዓለምና አህጉር ዓቀፍ ተቋማት፣ እንዲሁም ለአገራት በሰጠው ማሳሰቢያ ” የትግራይ መንግስትና፣ የትግራይ የውጭ ግንኙነት” የሚባል ነገር እንደሌለ፣ ይህን ገለጻ መጠቀም ኢትዮጵያ የምትመራበትን ህገ መንግስት መጻረር፣ ሉዓዊነቷንም መዳፈር ነው” በሚል ከንግግሩ ቀጠሮ በፊት አሳሳበ። ይህን ተከትሎ አፍሪካ ህብረት እርምት አደረገ። አሜሪካን ጨምሮ ሁሉም አስተካከሉ። አንዳንዶችም “የትግራይ ሃይሎች” ሲሉ አዲስ ስያሜ ፈጠሩ።

ራሱን “የትግራይ መንግስት” እያለ ይጠራ የነበረው ትህነግም ” የትግራይ ክልላዊ መንግስት” በሚለው የተፈቀደለት ስም በነበረው የደብዳቤ ይዘት በንግግሩ እንደሚሳተፍ ገልጾ ለአፍሪካ ህብረት ጻፈ። መንግስት ከዚህ አንጻር የተዋጣለት ተግባር መፈጸሙን በርካቶች ” የተጠና አካሄድ” ሲሉ አድንቀውታል።

ንግግሩ ከመጀመሩ በፊትም ሆነ በሁዋላ መንግስት በኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤቱ አማካይነት እለት እለት ፕሮፌሰር ክንድያ ከዘረዘሯቸው የድራጅታቸው ፍላጎቶች ውስጥ እየመዘዘ ” የማይናወጥ አቋም” በሚል መረጃ መስጠት ጀመረ።

ንግግሩ ከተጀመረ ሰኞ ጀመሮ ትግራይ መቀለ አካባቢ ያለው የትህነግ አመራር ስለ ጦርነቱና ስለ ተዋጊዎቻቸው አይበገሬነት ሲናገሩ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን በበኩሉ ” የማይነኩ” ሲል መስመር የሚሰመረባቸውን ጉዳዮች እየቀነጨበ ማስታወቅ ጀመረ። መከላከያም “የቀድሞ ጥፋት አይደገምም” በሚል እያላመና እያበጠረ ወደፊት መሄዱን አላቆመም።

አስቸኳይ ተኩስ አቁም

የትህነግ ሃይሎች በአንደኛ ደረጃ ፍላጎታቸው አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲታውጅ ነበር። አሜርካና አውሮፓም ይህንኑ ፍላጎት ፍላጎታቸው አድርገው በከፍተኛ ደረጃ ጫና አድርገዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ጦረንቱ ከመቀለ 160 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው ዘ ኢኮኖሚስትን ለመሞገት ቢሞክሩም ዛሬ በወጣና ዝግጅት ክፋላችን ባርጋገጠው መሰረት ከመቀለ ወጣ ብሎ የሚገኘው የመቀለ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ በመንግስት ሃይሎች እጅ ወድቋል።

መንግስት ” አላማዬ ሰፈርና ከተማ መቆጣጠር ሳይሆን፣ የታገተውን የትግራይ ሕዝብ ነጻ ማውጣት ነው” ሲል በይፋ አስታውቆ ቀጥሎበታል። ነጻ የወጡ አካባቢዎችም የተቋረጠ አገልግሎት እንዲጀመር እይሰራ መሆኑንን፣ ይህም ግፋ ቢል ወር እንደሚፈጅ አመልክቷል። ስለዚህ የአስቸኳይ ተኩስ አቁሙ የሚያበቃው በመንግስት ሰዓት አቆጣጠር መሆኑን ያሳያል።

የኤርትራና የኢትዮጵያ ሰራዊት ከትግራይ ይውጡ

የትህነግ ሃይሎች ይህን ጥያቂ ደጋግመው ቢያቀርቡም፣ መንግስት ቀድሞ ይፋ እንዳደረገው ትህነግ ህጋዊ መሰረትና ማንዴት የሌለው አማጺ ነው። ይህ ሃይል የኢትዮጵያ አካል በሆነችው ትግራይም ሆነ ማናቸውም ክልሎች መንግስት ሰራዊቱን እንዳያሰማራ የመጠየቅ መብት የለውም። በአገሪቱ የምርጫ ህግ መሰረት የተሰጠውን የስራ ጊዜ በህጋዊ ኮንትራት ያላሳደሰው ትህነግ መንግስትን ” በዚህ ግባ፣ በዚህ ውጣ” የማለት ህጋዊ አቅምና ማንዴት ስለሌለው ይህም ጥያቄ ውድቅ እንደሆነ መንግስት ይፋ አድርጓል። የኤርትራ ሰራዊትን በተመለከተ መምግስት ተንፍሶ አያውቅም። ኤርትራም ጭጭ እንዳለች ነው።

በባድመና ዛላንበሳ አቅጣጫ በነበረው የድንበር ይገባኛል ንትርክ አቶ መለስ ዜናዊ አልጀርስ ላይ ሄደው ይግባኝ የሌለው ውል ከፈረሙ በሁዋላ፣ ኢህአዴግ በይፋ ሳይሟሟ የአልጀርሱ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን የተወሰነ መሆኑንን የሚገልጹ፣ ትህነግ በዚህ ጉዳይ አሁን ያለውን መንግስት የመውቀሰ ህጋዊ አቅም ብቻ ሳይሆን ሞራልም የለውም። ከጠየቀም እነ አቶ ገብሩ አስራትን “አሃዳዊ” ሲሉ አባረው ባድመን ለኤርትራ ያስረከቡትን መለስና ጓዶቻቸውን ብቻ ነው። ስለሆነም ይህም ጥያቄ ወደፊት በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል በሚፈጠር የሰላም ግንኙነት ሕዝብንና ማህበራዊ አሰፋፈርን ለይቶ በሰላም መፍትሄ የሚበጅለት ተደርጎ ዕቅድ ይያዝለት ካልሆነ በቀር በደቡብብ አፍሪካው ንግግር ላይ ውሃ የሚያነሳ አጀንዳ አልሆነም።

ሰብአዊ ዕርዳታን በተመለከተ

አስቸኳይ ተኩስ አቁም ተደርጎ የትህነግ አመራሮች ገደብ የሌለው እርዳታ እንዲጀመር ስምምነት መድረስ ይፈልጋሉ። መንግስት ንግግሩ ሳይቋጭ ” በትግራይ ሕዝብ ስም የሚገባ ዕርዳታ ከአሁን በሁዋላ ለሽብር ቡድኑ ተዋጊዎች እንዲውል አልፈቅድም” ሲል የትግራይ ህዝብ የድጋፉ ቀጥታ ተጠቃሚ እንዲሆን ራሱ ስራውን እንደሚያከናውነው ይፋ አድርጓል። ይህ ብቻ አይድለም ዕርዳታ ሰጪዎችንም እንደሚቆጣጠራቸው፣ ይህ ለድርድር እንደማይቀርብም አስረግጦ ተባግሯል። ስለዚህ ጦርነት የሚደረገው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ስለሆነ ይህ እስኪከበር መንግስት በመረጠውና ባሻው ሰዓት ህግ እንደሚያስከበር፣ የእርዳታ ተጋርንም እንደ ቀድሞ ተመላክች ሆኖ እንደማያይ ይፋ ማድረጉ በዚህ መልክ በንግግሩ ሊለውጥ የሚችል ነገር እንደሌለ አመላካች ነው።

የስም ማጥፋትና ክፉ ቅስቀሳን ስለማስቆምና ስለ ወልቃይት ጠገዴ

ትህነግ ” አማራና እኛ መካከል ጸብ የለም” የሚል አዲስ ድርሳን ካሰማ በሁዋላ አጥብቆ ከሚጠይቀው ነገር መካከል አዲሱን ስልቱን ለማስቀጠል ይረዳው ዘንዳ አንዱ ሌላው ላይ የጠላቻ ንግግር ማስማት እንዲያቆሙ ስምምነት እንዲደረስ ይፈልጋል። አማራን ለይቶ በመፈረጅ “ነፍጠኛ” ብሎ በኖርባቸውና እትብቱን በቀበረባቸው የአገሪቱ ምድር እንዳይኖር በገሪቱ ብሄራዊ ሚዲያ ያወጀ፣ ለትግራይ ተማሪዎች “አማራ ጠላት ነው” ብሎ የሚያስተምር፣ በማኒፌስቶ አማራን ጠላት አድርጎ ፈርጆ የኖረ፣ ዕቅዱና ትልሙ ሁሉ በአማራ መቃብር ላይ የተቨከለ፣ በውልቃይትና ጠገዴ በገሃድ ንጽሁሃንን በጅምላ የፈጀ፣ ከመኖሪያቸው ያባረረ፣ በአማርኛ እንዳይናገሩ፣ እንዳይዘፍኑ፣ ባንዲራቸውን እንዳያነሱ፣ እስክስታ እንዳይወርዱ የከለከለ፣ በቅርቡ በወረራ አማራ ክልልን ከግድያው፣ ከዝርፊያው፣ ከመድፈሩና ከማሰቃየቱ በላይ ሙሉ በሙሉ ማውደሙ፣ ሌማታቸው ላይ መጸዳዳቱ፣ የራሳቸው ምርኮኞች “አማራን አጥፉ፣ ዝረፉ” ተብለው ስልጠና እንደወሰዱ የመሰከሩበትና ድመት፣ ውሻና የቤት እንድሳሳትን የአማራ ብቻ በመሆናቸው ብቻ የረሸነ፣ ዛፎች አማራ ደጅ ስለቆሙ ብቻ የጨፈጨፈ ድርጅት መሪዎች ዛሬ አማራን ” ፍቅርህ አንዘፈዘፈን” እያሉ ነው።

ይህ አዲስ ትርክት ከላይ እንደተባለው ተነጻጽሮ እንዳይቀርብ ” ስም ማጥፋት ይቁም፤ ጥላቻን መስበክ ይገታ” የሚለውን አጀንዳ መንግስት በገሃድ መልስ ባይሰጥበትም የመንግስት ሚዲያዎች ግን ትህነግ ላይ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ እሳት እያወረዱበት ነው። ” ከአማራ ይልቅ ሱዳን …” እያሉ ደብረጽዮን የተዛበቱበትን ሕዝብ ዛሬ ሸምቀቆው ሲጠብ ወዳጅ ማለት ” ያለወለድኩት ልጅ ቢለኝ አባ …” እየተባለ ነው። የትግራይና የአማራ ህዝብ አብሮ የሚኖር፣ በሕዝብ ደረጃ ችግር የሌለበት ቢሆንም ትህነግ ይህን ወዳጅነት የማስቀጠል አማራጭ ከቶውንም እንደማይሰጠው እየተገለጸ ነው። በርካቶች እንደሚሉት ትህነግ የመታመንን ፈተና ተፈትኖ በተደጋጋሚ ወድቋል። አይታመንም። “ከአማራና ፋኖ ጋር ጸብ የለኝም” በሚል ጎንደሬን ለይቶ ” የሰሊጥ ፖለቲካ” አራማጃ በማድረግ ወልቃይትና ጠገዴን እንዲሰጡት 360 ዲግሪ ለጀመረው ዘመቻ ስኬት የጥላቻ ንግግርና ክስ እንዲቆም ቢፈልግም አሁን ላይ የሚሆን አይመስልም።

በማብቂያ

ከላይ እንደተባለው መንግስት “አገልግሎት ማቅረብ መንግስታዊ ሃላፊነቴ በመሆን ነግግር አይስፈልገውም እያደረኩት ነው፣ ሉዓላዊነት አስከብራለሁ፣ የትግራይን ህዝቤን ነጻ አወጣለሁ፣ ዕርዳታ ለትግራይ ወገኖች እንዲደርስ ቁጥጥር አደርጋለሁ፣ የተኩስ አቁም ጉዳይ የሚታሰበው በአገሪቱ አንድ ተቋም ብቻ በአገር መከላከያነት እንደተሰየመ አምኖ ትጥቅ ሲፈታ ብቻ ነው ” ብሎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መስመሩን አሳይቷል። አቋሙን ገልጿል።

ጫና እያደረጉ ያሉ አገራትን ስም ሳይጠራ (ይታወቃሉ) ግንኙነቱን ለመመርመር እንደሚገደድና በዕርዳታ ስም የሚጫን ማናቸውን ጫና እንደማይቀበል መራር በሆነ ቋንቋ መንግስት አስታውቋል። ሕዝብ ይህን የመንግስት ውስኔ ደግፏል። ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ እንዲፈጸም እድል ሊሰጠው እንደማይገባ ከየአቅጣጫው ጥሪ እየቀረበ ነው። አማራና አፋር ክልል በየስድስት ወሩ ትንፋሽ እየሳበ በሚያመነዥግ ዘንዶ ዳግም ሊመታ፣ የትግራይ ምስኪን ወንድምና እህቶቭም በማይውቁት የዘነዶው ጥርስ ሆነው እንዳያልቁ ግፊቱ ብርቱ ነው። መንግስትም “ያለፈው ስህተት አይደገምም” ሲል ጦርነቱን ” ድምጽህን አጥፍተህ ምታ” ብሎታል።

ያለፈውን ስህተት አንደግምም

የአገር መከላከያ ሃይል ላይ “ቅጽበታዊና መብረቃዊ” ተብሎ የተሞካሸው የክህደት ቢላ ከተሰነዘር በሁዋላ በውስን አቅም መቀለን የተቆጣጠረው መንግስት ስህተት ሰርቶ ነበር። ስህተቱ ፖለቲካው ላይ በወጉ ባለመሰራቱና ትግራይን እንዲመሩ የተመደቡት ሰዎች ልክስክስነት ዋጋም አስከፍሎ ነበር። የሸሸው የትህነግ ሰራዊት ባለመመታቱ ከተደበቀበት እየወጣ ሲያጠቃ፣ የቤት ለቤት አደረጃጀት ፈጥሮ ዳግም እንዲነሳ በተመቻቸለት የሽግግሩ ጊዜ ሁለት ቢላ ተጠቃሚዎች አሳዛኝ ዋጋ ተከፍሏል።

ይህን በማሰብ መከላከያ የሚመራው ጥምር ጦር እንደቀድሞ በፈጣን ሩጫ እንዲገሰግስ አልተደረገም። ሃይሉ ሸሽቶ ወደ ተዘጋጀለት መመሸጊያ እንዳይገባ ከውርጋጦቹ ወይም መሳሪያ አልባ ህጻናቶቹ ውጪ፣ ዋናው ሃይል መምታትና በቀጣይ ተዋጊ እንዳይሆን ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ኦፕሬሽን በመሆኑ እንደቀድሞው ፍጥነት ሊኖረው እንዳልቻለ የመከላከያ አንዳንድ ሃላፊዎች ፍንጭ ሲሰጡ ተሰምቷል።

“ዓላማችን ትህነግ ወደፊት ስጋት እንዳይሆን ማድረግ ነው” ሲሉ የተደመጡ የመከላከያ መኮንኖች ያሰቡት እንደተሳካላቸውና እንዳልተሳካላቸው አሁን ላይ ካለው የትህነግ ቁመና መረዳት ይቻላል። ” አፍንጫ ይዘን” ባሉ በሳምንት “ያለ ምንም ቅደመ ሁኔታ ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን አወጁ። ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠው እንዳልነበር ተገላቢጦሽ ሆነ፣ ፎጣ ለባሽ በሚል ከምድር ላይ እንደሚያጠፉት ሲዝቱበት የኖሩትን አማራ ” ጫጉላ እንውረድ” አሉት። አፍረት የማያልቅባቸው አሉላ ሰለሞንን የአማራ ወኪል አድረገው በጸዳለ ሞሻሪነት፣ በዶከተር ጫኔ አራጋቢነት አቀረቡ፣ በየት በኩል ወደ ባህር ዳር እንግባ፣ መከላከያ እጅህን ስጥና እንደ ቀድሞ እንበትንሃለን ብለው ሲታበትይ እንዳልነበር ዛሬ … የሚለው የትህነግ ወሬና የአሜሪካ ቃሬዛ ተሸክሞ ማስፈራሪያ ብዙ ይነግራሉ። ለሁሉእም ግን ድርድሩ እንደከሸፈ የመንግስት ኮሙኒከሽን ጽህፈት ቤት አጠር አጠር ባሉ መግለጫዎቹ እየቀነጣጠበ ቀድሞ ይፋ አድርጎታል። ትህነግ መሳሪያ እፈታለሁ ብሎ ባለቀ ሰዓት እንዲቀበል ጌቶቹ ካዘዙት የሚለወጥ ነገር ይኖራል። አለያ ግን መከላከያ መቀለ 15 ኪሎሜትር ላይ ነው!!

Exit mobile version