Site icon ETHIO12.COM

በአዲስ አበባ መሬት የግል መሆን አለበት፤ “ሲፈልግ ግለሰቡ ይሽጠው”

በአዲስ አበባ መሬትን አስመልክቶ ለተነሳ ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቢያንስ በአዲስ አበባ መሬት የባለቤቱ መሆን እንዳለበት አመለከቱ። “ሲፈለግ ባለቤቱ ይሽጠው” ሲሉም አመልክተዋል። ለዚህም አካታች ውይይትና የህግ ለውጥ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

” መሬት የደላላና የሹመኞች ነው” ሲሉ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ህገመንግስቱ መሬት የህዝብና የመንግስት ሃብት እንደሆነ ቢያስቀምጥም፣ መሬቱ ግን የደላሎችና የሹመኞች መሆኑንን ከሌብነት ጋር አያይዘው አስታውቀዋል።

መፍትሄው ሁሉንም አካታች የሚያደርግ ውይይት ተደርጎ ቢያንስ መሬት በአዲስ አበባ የግል ሊሆን እንደሚገባ አስተያየት የሰጡት አብይ አሕመድ፣ መንግስት በህገወጥ ደላሎች አማካይነት የሚፈልገውን የልማት ስራ መስራት መቸገሩን ሳይቀር በገሃድ በመግለጽ ከመሬት ጋር ያለውን ችግር ግዝፈት አሳይተዋል። ኢንቬስተሮች ጋርም ችግር መኖሩን በርካታ መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ በርካታ መሬት በሹመኞች እንደሚዘረፍና ደላሎች አየር በአየር እንደሚቸበችቡ በገሃድ የሚታወቅና የዚሁ ዝርፊያ መሪዎችም ስልጣን ላይ የሚታዩ መሆኑንን ህዝብ ፊት ለፊት ሲናገር መስማት የተለመደ ነው።

ከዚህ ብጋር ሳይሆን በሌላ ተምሳሳይ ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሌቦች” ያሏቸውን አንገት የማስደፋት ስራ እንደሚጀመር አመልክተዋል። ግልጽ ያላደረጉትና እንደተቋቋመ የገለጹት ቡድን የማጥራት ስራ እየሰራ እንደሆነ አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ዓመታት በሰንሰለት ሲዘርፉ የነበሩና ከትህነግ ጋር አብረው በሽርክና ሲሰሩ የነበሩ ሰላም ከወረደ ሌቦች ስለሚታደኑ ያላቸውን ሃብት በመበተን በየቦታው በሚታየው ሁከትና ግጭት እጃቸው እንዳለበት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

በዛሬው የምክር ቤት ስብሰባ በስፋት የተጠየቀው የመልካም አስተዳደር፣ የሌብነት ስፋት ከፍተኛ ምሬት እያስነሳ በመሆኑ መንግስት እርምጃ እንዲወስድ የሚያሳስብ ነው።

Exit mobile version