Site icon ETHIO12.COM

በሌብት የተጠረጠሩ እየተሰወሩ ነው፤ ከሚፈለጉት የተያዙት ያንሳሉ፤ ዋናዎቹ ሻርኮችስ?

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከያዛቸው ይልቅ ያመለጡት በዝተዋል። የሚፍለጉት ይልቃሉ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቀናት በፊት ባደረጉት ቃለ ምልልስ የማጣራት ተግባሩ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ሚስጥር አሾልከው ያወጡ የኔትወርኩ ሰዎች ተፈላጊዎቹ እንዲኮበልሉ ማድረጉን ተናግረዋል። የፍትህ አካሉና ፍርድ ቤቶች ተመሳጥረው በከፍተኛ ወንጀል የተከሰሱና የተያዙትን እንደሚለቁዋቸው ስምና ጉዳዩን ጠቅሰው አስታውቀው ነበር።

https://ethio12.com//vid_20221126_084423_965-mp4/

የጸረ ሙስና ብሄራዊ ኮሚቴ መቋቋሙን ተከትሎ ከንቲባዋ ይፋ እንዳደረጉት የሙስናው ስር የህግ ከለላ ያለው ይመስላል። ክስ የሚመሰርቱት ክፍሎችም ሰባራ ጉዳይ እያቀረቡ የህግ ከለላ ለሚሰጡ ምነግድ ጠራጊ ናቸው። ከዚህም በላይ በምርጫ 97 ትህነግ አዲስ አበባ ላይ በተሸነፈ ወቅት ከአዲስ አበባ ጠራርጎ ወደ ፌደራል የውሰደው በርካታ የከተማዋ ማንዴቶች አስተዳደሩን ሽባ እንዳደረገው የተገለጸ ነው።

አሁን አገሪቱ ላይ የሚታየውን ስር የሰደደና ዓይን ያወጣ ዘረፋ የሚታዘቡ ” ቀደም ሲል ትህነግ በሰበሰ፣ ከጥሎ አጋሮችና እህት ድርጅቶችን አበሰበሱ፣ ሁሉም ሲደመር በየዘርፉ የከሸፉና የበሰበሱ ተሰግስገው አገሪቱን እያነቀዙ ነው። የሚያስፈልገው አዲስ ንቅናቄና አዲስ ትውልድ በመሆኑ ለውጡ ከአሮጌ አመላከካትና እያዛለሁ ከሚሉ ሌቦች እስካልጸዳ ድረስ የሚታሰበው ለውጥ አይመጣም” ይላሉ።

ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ ጥቆማ እያቀረበ እንደሆነ መረጃዎች በሚወጡበት በአሁኑ ወቅት ጎን ለጎን መንግስት ዋና ዋና ሌቦችን በጉያው መያዙ፣ ሌቦቹን ህዝብ እንደሚያውቃቸው፣ አብረዋቸው የሚሰሩት ደላሎች በገሃድ እንደሚታወቁ፣ ከባለስልታናት ጋር የድብቅ ውል አድረገው እነማን ኢንቨስተርና ሪል እስቴት አልሚ እንደሆኑ በርካታ መረጃ እያለ “የተፈጨ ስጋ ኪሎ ጨምሮ ግዢ የፈጸመ ተከሰሰ” የሚል ዜና ዘመቻውን አንዳችም እልፍ እንደማያደርገው እየተገለጸ ነው። ዋናዎቹን ሻርኮችና በሚዲያ ፕሮጀክት ስም በቢሊዮኖች በየወሩ የማይወራረድ ሂሳብ የሚያመነዥጉትን ተወዛዋዦችና የስም የደህነነት ሃላፊዎችና አጫፋሪዎቻቸው ይዞ መንግስት ” ሙስና ላይ ዘመቻ ጀመርኩ የሚል ቀልድ መቀለድ እየነካካ ውድቀቱን ከማፋጠን በቀር ረብ የለውም” የሚሉ ድምጾች እንደ እነ አቶ ታዬ ደንደአ አይነት የብልጽግና ሰዎች እየተናገሩ ነው።

ከስር የአዲስ አበባ አስተዳደር ያወጣው ዜና ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬት ዝርፍያ ጋር በተያያዘ ሲያደርገው በቆየው የማጣራት ስራ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ  የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ፤የክ/ከተማ በመሬት ጉዳይ ይወስኑ የነበሩ አመራሮች ፤ ባለሙያዎች ፤ ደላሎችና ከህብረተሰቡ ውስጥ በዚህ ድርጊት የተሳተፉትን  ጨምሮ 37 ሰዎችን በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ   እስካሁን ድረስ 12 ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

ቀሪዎቹን ግለሰቦችም ፖሊስ ክትትል እያደረገባቸው ይገኛል፡፡ ተጨማሪ የማጥራት ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል::
በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦችም:-

1.  ለምለም አባይነህ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ  ወረዳ 4 ዋና ስራ አስፈፃሚ

2.  አቶ ከፍያለው አሰፋ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

3.  አቶ ዋሲሁን ሰውነት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

4.  አቶ ኢብራሂም ሀሰን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

5.  አቶ ሃይለየሱስ ደስታ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)

6.  አቶ ዳዊት ከልሌ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ

7.  አቶ ልኡልሰገድ ታደሰ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ

ከመንግስት ተቋማት ውጪ በጉዳዩ ተሳታፊነት በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች

8.  አቶ አየለ ጉቱ

9.  አቶ ጎሳዬ ደሜ

10.  አቶ በፍቃዱ ወንደሰን

11.  አቶ ሮባ ደበሌ

12.  አቶ መታሰቢያ አባተ ናቸው፡፡

Exit mobile version