Site icon ETHIO12.COM

ስድሳ የአማራ ባለስልጣን ላይ የሙስና ምርመራ ተጀመረ፤ ወደፊት ለመስረቅ የሌላቸውን ንብረት ያስመዘገቡ ተገኝተዋል፤

Stock Photo - ጎንደር አካባቢ ያለ የውሃ ችግር ማሳያ

ሌብነት በኢትዮጵያ አገር የሚንድበት ደረጃ መድረሱ በይፋ ከተነገረ በሁዋላ በፌደራልና በክልል ደረጃ በስፋት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ አማራ ክልል ይፋ እንዳደረገው ስድሳ ባለስልጣናቱን እየመረመረ ነው። በማጣራት ሂደቱ ገና ለገና ወደፊት ሰርቀን እናከማቻለን በሚል አስቀድመው የሌላቸውን ሃብት ያስመዘገቡ ባለስልጣናት መገነታቸውም ተመልክቷል።

በአማራ ክልል ከገቢያቸው ጋር ያልተመጣጠነ ሐብት አከማችተዋል የተባሉ 60 የመንግስት ባለስልጣናትና ሰራተኞች ጉዳይ እንዲጣራ ለፖሊስ መላኩን የአማራ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በይፋ ሲያስታውቅ ተጠርጣሪ የተባሉት አካላት እንዳይሸሹ ምን መከላከያ እንዳበጀ አላስታወቀም።

ኮሚሽነሩ አቶ ኃብታሙ ሞገስ በአማራ ክልል ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ በተደረገ የሐብት ምዝገባ ነው የተጠቀሰው ቁጥር ያላቸው ባለስልጣናት ጉዳይ ወደ ፖሊስ እንዲመራ የተደረገው። ከ60 በላይ የመንግስት ሰራተኞችና ሹመኞች ከገቢያቸው በላይ ንብረት ማስመዝገባቸውን ያመለከቱት ኮሚሽነሩ ክስ መቼና እንዴት እንደሚመሰረት አላብራሩም።

በሐብት ማስመዝገብ ሂደቱ አራት ቤቶች ያለው ሹም መገኘውቱን፣  ሁለት ተሸከርካሪዎች ያላቸውና ፣ እንዲሁም የሌላቸውን ንብረት ወደፊት በስርቆት አገዛለሁ ብለው ያሰቡና ያስመዘገቡ የመንግስት ሰራተኞች በምዝገባ ወቅት እንደተገኙም አመልክተዋል፡፡ ሐብት ቀንሶ ማስመዝገብ፣ ያላግባብ መጨመርና የሌለ ሐብት ማስመዝገብ ሁሉም ወንጀል መሆናቸውንም ኮሚሽነር ኃብታሙ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ እንዲጣራ ተልኳል በሚል እንደ ምሳሌ ያነሱት ሃብት አሁን አገሪቱ ላይ ከተንሰራፋው ሙስና አንሳር እዚህ ግባ የሚባል ባለመሆኑ ጅምሩ ሊጠናከርና ወደ ዋና ሌቦች፣ ባለሃብት ነን በሚል ለከፍተኛ ባለስልጣናት የሚነግዱት ዋና ሻርኮች ላይ ትኩረት እንደሚገባ እየተመለከተ ነው።

ከክልሉ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመልክቱት ህዝብ ጥቆማ እየሰጠ ነው።

Exit mobile version