ETHIO12.COM

ወሳኙ የኢራን ከአሜሪካ ጨዋታ ጦዟል – የፖለቲካ ፍልሚያ ደርቢ

እስራኤል ኢራን ላይ የሃይል እርምጃ እንድትወስድ አሜሪካን በይፋ በጠየቀች ሳምንታት ውስጥ

ሲጠበቅ ድንገት የሚፈርሰው፣ አደገ ሲሉት የሚርመጠመው፣ ከፍ አለ ሲባል ቁልቁል የሚደፋው የእንግሊዝ ቡድን ከአሜሪካ ጋር ስቃዩን አይቶ ነጥብ ቢጋራም ኢራን ላይ በውሰደው ብልጫና የጎል ናዳ ባገኘው ሶስት ነጥብ ሳቢያ ከጭነቀት ነጻ ነው። ምድቡን በአራት ነጥብ የምትመራው እንግሊዝ ደጋፊዎቿ ከዌልስ አቻዎቻቸው ጋር “ቺርስ” እያሉ መሆኑን ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው። በተቃራኒውና ኢራንና አሜሪካ የሚያደርጉት ጨዋታ ኒኩሌር የማይተኮስበት የጨበጣ ውጊያ ተደርጎ እየተዘገበ ነው።

አሜሪካ ዓለም ላይ እይፈጥረች ያለችው ሁከት፣ ጣልቃ ገብነት፣ የግጭት ምክንያት መሆንና የበላይ ሆና ለመቆየት የሌሎችን አቅም ባለማክበር የምትወስዳቸው አቋሞች የሰላቸው የአብዛኛው ዓለም ሕዝብ ኢራንን እንደም እንደሚደግፍም እየተገለጸ ነው።

የአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢራን ባንዲራ ያለ ኢስላሚክ ሪፐብሊክመለያው ሌጣ አድርጎ በትዊተር በመለጠፉ ኢራን አሜሪካ ከአለም ዋንጫ መታገድ እንዳለባት ጠይቃለች። ከዚህኛው አሁን ከሚካሂደው ብቻ ሳይሆን ከመጪዎቹም ውድድሮች ጭምር።

ዘረኞች፣ የፖለቲካና የርዕዮተ ዓለም ትግል የሚያራምዱበት ፊፋ ሃምሳ አራት አገራት ላስመዘገበችው አፍሪካ ለምርጫ አንዳንድ ድምጽ፣ ለውድድር ግን አምስት ኮታ ብቻ ማስቀመጡ በራሱ ድርጅቱ ዘረኛ መሆኑንን ያሳያል። በነገራችን ላይ ለመጠቆም ያህል እንጂ ዋናው የኢራን ጉዳይና የፊፋ ማመልከቻዋ ምንም ባይባልበትም ነገ ከባላንጣዋ አሜሪካ ጋር የምታደርገው ፍልሚያ የኳታር ዓለም ዋንጫ ትልቅ ዜና ሆኖ እየተራገበ ነው።

የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን በትዊተር፣ በፌስቡክና በኢንስታ ግራም ላይ ከለጠፈው የኢራን ባንዲራ ላይ የአገሪቱ መለያ አርማ እርምት ወስዶ ያላስተካከለው በኢራን ከሚካሄዱ ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ እንደሆነ አመልክታለች።ከጸረ መንግስት ተቃውሞ እንቅስቃሴው ጋር በተያያዘ “በኢራን መሠረታዊ መብቶች እንዲከበሩ እየታገሉ ላሉት ሴቶች ድጋፈችንን ለመግለጽ” ነው የሚል ምክንያት ያቀረበችው አሜሪካ ከሂጃብ አለባበስ ጋር በተያያዘ ታስራ ህይወቷ እንዳለፈ የተነገረላትን የማህሳ አሚን ተቆርቋሪ ለመሆን ዳድቷታል። ለእርስ በርስ ጾታ ጋብቻ (ሰዶማዊነት) በጀት የምትመድበውና መድረክ የምታመቻቸው አሜሪካ የህን ምክንያት ብታቀርብም ኢራን ጥያቄዋ የብሄራዊ ክብሯ ጉዳይ እንደሆነ ነው ያመለከተችው።

ኢራንን በማዕቀብ ሰንጋ የያዘቸው አሜሪካ፣ በኢራን የመንግስት ለውጥ እንዲካሄድ በርካታ ሴራ ብራሴርም ባለመሳካቱ ከፍተኛ ሃብት በማፍሰስ ኢራንን በውስጥ የተቃውሞ ማዕበል ለመብላት በጥብቅ እየሰራች ባለበት በዚህ ወቅት የሁለቱ አገራት የ ” ሰላም” መድርክ በሚባለው ሜዳ ሊፏከቱ የቀራቸው ሰዓታት ብቻ ነው። ዓለምም ከጨዋታው በላይ በሜዳው ላይ ምን ይከሰት ይሁን በሚል በጉጉት እየጠበቀው ነው።

በማህበራዊ ገጾች በተለይ በቲውተርና በቲክቶክ የጦዘው የሁለቱ አገራት ጨዋታ ምን አልባትም በዓለም ዋንጫ ትልቁ ወሬ ሆኖ የመመዝገብ እድል ሊኖረው ይችላል። ትናንት ሞሮኮ ቤልጂየምን በማሸነፏ ብራስልስ በተቃውሞ እንደተናጠችው አሜሪካ ሽንፈት ቢያጋጥማት ምን ሊሆን እንደሚችል የተጠየቁ ” እነሱ ለኳስ ደንታ የላቸውም” የሚሉ ተሰምተዋል።

በሌላ ወገን ግን አሜሪካን አሸንፈው በንዲራዋ ለመቀለድና መሪዎቿን ለማበሻቀጥ የጓጉ በስሜት ኢራን እንደምታሸንፍ ቢመኙም፣ የወቅቱ የኢራን አቋም እዛ የሚያደርስ እንዳልሆነ የሚናገሩ ደጋፊዎቻቸው ጥቂት አይደሉም።

እንደ ጀርመን ያሉ አውሮፓን የወረረው የግብረ ሰዶማዊያን ደጋፊዎች ነቀፌታ፣ በሌላ ጎን ደግሞ አዘጋጇ አገር የሰውን ልጅ መብት ተጋፍታለች በሚል የጀርመንን አቋም በደገፉበት የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሚዛን የደፋው ወሬ ኳሱ ሳይሆን ከኳሱ ጀርባ ያሉ ቲያትሮች ናቸው።

ሴሰኝነት ላይ በሯን የቀረቀረችው ኳታር ማንም ቢንጫጫ ደንታ አልሰጣት ብሎ እያካሄደችው ባለው የዓለም ዋንጫ የነገው “የፖለቲካ ደርቢ” ሌላው መተዋወቂያና በሚዲያ መድመቂያ ውድድር ነው።

“US not feeling the pressure of facing Iran yet, though social media furor has fueled prematch tension” አሜሪካ ንትርኩ ምንም እንዳልመሰላት መግለጿን የሚያትቱ ሚዲያዎች ያሉትን ያህል ኢራኖች ደግሞ “እልህ ምላጭ ያስውጣል” እንዲሉ ያለ የሌለ ሃይላቸውን ተጠቅመው አሜሪካን ለማዋረድ መዘጋጀታቸውን የሚናገሩም አሉ። አንዳንድ ሚዲያዎችም ከአሁኑ አላህን የሚማጸኑና የሚጸልዩ መበርከታችውን ዘግበዋል። እንደውም “የፍትህ አምላክ አሜሪካ ላይ የፍርዳል” ሲሉ ኳሱን ወደ ላይኛው ጌታ የፍርድ ችሎት የገፉም አሉ።

ጨዋታውን ያሸነፈ ወደ ቀጣዩ ጥሎ ማለፍ ስለሚያልፍ በስፖርት ቋንቋም የሞት ውድድር ነው። ኢራን አቻ የሚበቃት ሲሆን አሜሪካ ግን የግድ ማሸነፍ አለባት። አቋቋማቸውን የሚያሳየው ሰሌዳ እንደሚመሰክረው ዌልስ የመረሃ ግብር ማሟያ አጫፋሪ ናት።

Exit mobile version