Site icon ETHIO12.COM

የፌደራል ፖሊስ ለአክሱም ነዋሪዎች ምስጋና አቀረበ-ክብረ በዓሉ በሰላም ተጠናቀቀ

የፌደራል ፖሊስ የአክሱም ጽዮን ማርያም ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የአካባቢው ነዋሪዎች ምስጋና አቀረበ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የአክሱም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የአክሱም ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ምስጋና አቀረበ።

ዓመታዊው የአክሱም ጽዮን ማርያም ክብረ በዓል በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የአክሱምና አድዋ ጸጥታ ዘርፍ አዛዥ ኮማንደር ጌትነት ከበደ ለኢዜአ እንዳሉት ፖሊስ በዓሉን በሰላም ለማክበር ቀደም ብሎ ከሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በዚህም በዓሉ በሰላም እንዲከበር የፌደራል ፖሊስና የአካባቢው ማህበረሰብ በጋራ መስራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም የአክሱም ጽዮን ማርያም ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር ከጸጥታ ኃይሎች በተጨማሪ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ከፍተኛ ሚና ማበርከታቸውን ተናግረዋል፡፡

የእምነቱ ተከታዮች ወደ ቤተክርስቲያን በመምጣት በዓሉን በደመቀ ሁኔታ በሰላም ያሉት ኮማንደር ጌትነት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የአክሱም ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version